0

ሞረሽ ወገኔ፦የሣምንቱ ድርጅታዊ ወቅታዊ መግለጫ “የየካቲት ፲፪ ሠማዕታትን ስናስብ”

moresh-logoMWAO_V2No11_ረቡዕ የካቲት ፲፪ ቀን ፪ሺህ፮ ዓም_(Wed 19 Feb 2014)_የየካቲት ፲፪ ሠማዕታትን ስናስብ ………….. የየካቲት ፲፪ ሠማዕታትን ስናስብ የካቲት ፲፪ ቀን ፋሽስት ኢጣሊያ ጦር በአዲስ አበባ እና በሌሎችም ዋና ዋና የኢትዮጵያ ከተሞች በ፲ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በአሠቃቂ ሁኔታ የጨፈጨፈበትን ድርጊት የምናስታውስበት ዕለት ነው። ልክ የዛሬ ፸፯ (ሰባ ሰባት) ዓመት፣ በዕለተ-አርብ በአዲስ አበባ ከተማ የገነተ-ልዑል ቤተመንግሥት ቅፅር ግቢ (የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኑቨርሲቲ ዋናው ግቢ)፣ በኢጣሊያን ፋሽስቶች የጦር መሪ ጄኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ትዕዛዝ፣ በሦሥት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ፴ሺህ የማያንሱ ንፁሃን ኢትዮጵያውያን የተጨፈጨፉበት ድርጊት የተጀመረበት ነበር። ዘወትር ስለጭፍጨፋው አጀማመር ሠበብ ተብሎ የሚቀርበው ኤርትራውያኑ አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ግራዚያኒ በአደባባይ ቆሞ ኢትዮጵያውያንን ሲዘልፍ እና ሲያጣጥል ተበሣጭተው ቦንብ በመወርወራቸው እንደሆነ ተደርጎ ይቀርባል።………Read in PDF

Filed in: Amharic News, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.