1

የሥርጉተ ሥላሴ የመንፈስ ሰብል።

የሥርጉተ ሥላሴን የብዕር ዘር ይፈልጋሉን? እንግዲያውስ አጠቃላይ መረጃዎችን እንሆ ከታላቅ ኢትዮጵያዊ አክብሮት ጋር …..

ከ600 በላይ የግጥም እርእሶችን የያዙ የአዋቂዎች የሥነ  ግጥም (ቅኔዊዎችንም አክሎ) ሦስት መጸሐፍት በራሷ መንገድና አቅጣጫ የተሰሩ፤ ሁሉንም የህይወት ዘርፎች በአግባቡ የሚዳስሱ፣ እንዲሁም አብዛኞቹ በንድፍ የተሰሩ …. ። እርግጥ ነው በውስጣቸው ለመኖር ተመላልሶ መጎብኘትን፤ በስክነት መፈተሽን ይጠይቃሉ – በአጽህኖት – የየአሰራር ዘይቢያቸው ሆነ አቀራረባቸው ለዬት ያሉ በመሆናቸው ስዕላዊ ናቸው። ሥነ – ሥዕላቸው ልክ እንደ ፎቶ በመንፈስ ሰሌዳ ላይ ይቀረጻሉ። ሥርጉተ ሥልጡኑን የጸጋዬ ቤት( የኢትዮጵያን)  ሃይኮ ( የጃፓን) ሌይሪክ (የጀርመን) ሶኔት

(የእንግሊዝ) መንገድ አልተከተለችም። ከወል ቤት የተወሰኑ ልምዶችን ወስዳ አያንቀሳቅሰኝም በማለት የአብዬ ለማን ጥበቅ የሥነ ግጥም ህግጋትን ለዛሬ ተወኝ በማለት በእሸት ፈጠራ ነው የተቃኘቻቸው ….  ሥራዎቿ  ከተለመዱ የአስራር መንገዶች ያፈነገጡ  ወጣ ያሉም ናቸው።  ስለሆነም በቂ ጊዜ ሰጥቶ መመርመርን ይጠይቃል። ቁልቁለት – ዳገት – ሸሎቄ – ለጥ ያለ — ሊማሊሞ —- ብዕሯ በዜማ እያነበበ ስለ ከተበው እርሰዎም አብረው እየተጓጓዙ ይታደሙ ዘንድ በአክበሮት ተጋብዘዋል። በድምሩ 6መጸሐፍቶችን አሳትማላች። በመጸሐፍቶቿ ጀርባ ሽፋን ላይ ያስተላለፈቻቸው መልክቶች እንዲህ ይላሉ ….

shf ሀ. ለአዋቂዎች

 

1.„ተስፋ“

 

„ምን ያህል እንደተጓዝኩ አላውቀውም። ምን ያህል እንደሚቀረኝም አላውቀውም።

አለማወቄን ስጠይቀው አለማወቁን ገለጸልኝ። ተስፋን እጠብቃለሁ“

  • ሥርጉተ ከፊደል „ተን“ ከቃል ደግሞ „ተስፋን“ እወዳለሁ ትላላች።

ስለሆነም ነው ሆም ፔጇ ላይ አንዱ መምሪያዋን   „ተስፋ“ ያለችው። መጸሐፍት ማሳተም ስትጀምርም „ተስፋ“ የመጀመሪያው መንገድ – ጠራጊ መጸሐፏን እንዲሆን ፈቀደችለት።

2 „መክሊት“

 „እራስን መሆን እንዳለ ሁሉ መተላለፍም ይኖራል። ከሁሉ የሚከፋው ግን እራስን ማንበብ ሲሳን ነው። እኔ „ለእኔ“ ካልሆንኩ እኔ „እኔን“ ማሰናበት አለበት። ይህ ደግሞ የመንፈስ የቁም ቀብር ይመስለኛል።

  • መክሊትም ከሆም ፔጅ መምሪያዎቿ ውስጥ አንዱ ነው።

 3.    „ውል“

 

„እኔ „እኔ“ ነኝ የምለው፤ እኔ „እኔን ሳይዘል በውስጤ አልፎ፤ ለነፃነቴ ሲታገል ብቻ ነው።  ነፃ                                                መውጣቴን የማረጋግጠው ደግሞ፤ ዛሬ የማላያትን                                                         የሐገሬን ጸሐይ ማዬት ስችል ብቻ ይሆናል“

ለ. ሁለት የልጆች መጸሐፍት

 

4. “እንካ ሥላንትያ“

 „የልጅነት ጊዜ ሁልጊዜም ተናፋቂ፤ ለምንጊዜም ተወዳጅና ፈጽሞም የማይረሳ ልዩ የህሊና ጌጥ ነው።

       ሲያስታውሱት እንኳን ያልተፋቀ ፍቅርን ይለግሳል። አዘውትሮም ሐሤትን ይመግባል“   

 

በኢትዮጵያዊነት፤ በማንነት፤ በታሪክ፤ በባህል፤ በወግና በልማድ ላይ ያተኮረ እያዝናና፤የሚያስተምር  የልጆችን የማሰብ ችሎታ እንደ አባት አደሩ ትውፊቱን በሞራል በጥያቄና በመልስ ለማሳደግ ለመነሻ የተዘጋጀ።

5. „ፊደል“

      „እህ! ሳቅ የደስታ መንፈስ ብሩህ ህብረ ቀለም ነው። የሳቅ ውስጠ – መንፈስ ፍጹም ቅኔ ነው።

     ችግሩ በስደት ሀገር ከእውነተኛው ደስታ ጋር መገናኘት ተራራ ከመሆኑ ላይ ነው።

     ማለትም የፆም ውሃ ነው። ይህም በመሆኑ የአንጀት ሳቅ እንዲህ እንደ መስቀል ወፍ

      በዐመት አንድ ቀን ብቅ ሲል ጤና ነው። እባካችሁን?! እንደ ብርቅና ድንቅ ካዬሁት

                          ሳቅ ጋር ውስጤን ዳስሱት“

 

„ፊደል“ 89 ግጥሞችን ያያዘ የልጆች የሥነ ግጥም መጸሐፍ ሲሆን „የእንካ ሥላንትያ“ ጭብጦች በአቻነት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ውጪ ሀገር ረጅም ጊዜ ለቆዩ አወቂዎችም የትውስታ – የሽውታ – የእንጀራ ሀገራችነን የኢትዮጵያ ጠረን አብሶ የልጅነት ጊዜን ኮልኮል እናት ሀገርን በትዝታ እያፍለቀለቀ —- ያሰቃኛል።

 

 

ሐ. ለወላጆች

 

6. „የተስፋ በር“

 

„ውበት እንደ አካባቢው ይተረጎማል የሚል አንድመታ ቢኖረኝም፤ ተፈጥሯዊ የውበት ማመሳከሪያ

ቤተ መዘክር አምክንዮ አለው። እሱም እሸት ነው። እሸቱ አሽቶ ሲታይ ያ ውበት ነው ለእኔ።

እሸት ደግሞ የጮርቃ፣ የለጋ፣ የቀንበጥ፣ የዕንቡጥ – መንፈስ  ጸዳል ፈክቶ የሚገኘው በልጆች

ላይ ብቻ ይሆናል። አዎን! ውብ የምለው እኔ ውስጥን ነው። ውስጣቸው ቅዱስ፤ ንጹህ፤ ቅን፤

 ሳቅ፤ ፍካት፤ ሰላም፤ ኑሮ፤ ማዬት፤ ማስተዋል፤ እውነት፤ ቸር፤ የጽድቅ ጉዞ፤ ገነት፤ ተስፋም።“

 

 

የተስፋ በር ለወላጆች የተዘጋጀ ሲሆን፤ ወላጆች የልጆቻቸውን ተስፋ፤ ራዕይ፤ የወደፊት የህይወት አቅጣጫ፤ የቀንበጦችን ለጋ የተስጥዖ ፍላጎት ፈልጎ ከማግኘት ጀምሮ የዘመን ግጭት እንዳይኖር አስማምተው በመልካም አያያዝ እንዴት ማሰደግ እንደሚችሉ በጣምም ታስቦበት፤ የልምድ ጭማቂ የምክር አገልግሎት መጸሐፍ ነው።

 

  • „እንካ ሥላንትያ፤ ፊደልና የተስፋ በር“ ለሦስቱም መጸሐፍቶች የቃላት መፍቻ ሲኖር፤ „እንካ ሥላንትያ“ ላይ ለልጆች በጥቂቱ አጣቃላይ ሁኔታዎችን ያስማማ ጠቋሚ የምክር አገልግሎት አለው።
  • ለልጆች የሠራቻቸው መጸሐፍት ሥርዓት ቢቀያዬር፤ የውስጣቸው ዕሴት ሳይቀንስ፤ ዋጋቸውን ጠብቀው እንዲኖሩ ሰላማቸውን በመሸለም እጅግ በጥንቃቄ የተሰራ፤ እኛ ባለፍንበት ትርምስ ሳይሆን ፍቅርን ብቻ ያደመጡ፤ የከበከቡ መጸሐፍት ናቸው። የእውነት ብዙ የተደከመባቸው፤፡

 

ስለሆነም — ስለ እያንዳንዱ መጸሐፍት ዝርዝር መረጃ፣ ዋጋና እንዴት ሊላክለዎት እንደሚችሉ በኢሜል አድራሻዋ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ። የሰብል ሰብሎች ግጤሜና ልኬ ናቸው ካሉ ይግዙና ናፍቆቶዎትን ያውጉት።

 

አድራሻ ሥርጉተ ሥላሴ  mekletee@yahoo.com

ተጨማሪ መረጃ …..

 

1.   ድህረ ገጽ           www.tsegaye.ethio.info

2.   ራድዮ ፕሮግራም  www.lora.ch.tsegaye በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ በዕለተ ሃሙስ እ.ኤአ. ሰዓት አቆጣጠር ከ15.00 እስከ 16.00 ሰዓት በልጆችና በአዋቂዎች ራዲዮ ፕሮግራሟ ድምፆዋን ማግኘት ይችላሉ፤ ወደ አርኬቡን ጎራ ሲሉም ቀደምት ሥራዎቿን ማግኘትም ይችላሉ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የዘሃበሻምና የኢትዮ ሚዲያ አምደኛ ሆናለች።

 

  • ፎቶ –~~~–  በወ/ሮ ምስራቅ መንገሻ።

 

 

ለመላ ቅናዊ ትሁት ትብበረዎት እናመሰግናለን።

 

 

ኢትዮጵያ አምላክ አላት። አምላኳ አያንቀላፋምና ለዘለዓለም በክብር ትኖራላች!

Filed in: Amharic News, News, Politics & Openion

Recent Posts

One Response to "የሥርጉተ ሥላሴ የመንፈስ ሰብል።"

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.