0

የአኖሌ ሐውልት ጉዳይ … «አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል» እንዳይሆን

moresh-logoበቅርቡ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በሚቆጣጠረው የቴሌቪዥን ጣቢያ አንድ ዝግጅት ቀርቦ ነበር (ምንጭ፦ http://www.youtube.com/watch?v=ejucti17fAU)። የዝግጅቱ ትኩረትም «የዳግማዊ አፄ ምኒልክ ሠራዊት በአርሲ እናቶች ላይ በፈፀመው የጡት መቁረጥ ግፍ» መታሠቢያ የሆነ ሐውልት ስለመቆሙ ነበር። «ነገርን ከሥሩ ፣ ውኃን ከጥሩ» ይባላልና ለመሆኑ የዚህ አዲስ ሐውልት ባለቤቶች እነማን ናቸው? በሐውልቱስ መቆም ማን ምን ፋይዳ ያገኝበታል? ብሎ መጠየቁ ተገቢ ይሆናል።
ከታሪክ እንደምንገነዘበው ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው ነገሥታት ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ታሪካዊ ተግባሮችን ያከናውኑ ከሚባሉት ጥቂቶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። የኢትዮጵያን አንድነት በማጠናከር ረገድ ከአፄ አምደጽዮን ወዲህ የተነሡት ትልቁ አገር ገንቢ ናቸው። በዚህ አኳያ የላቀ ድርሻ ያላቸው ምናልባትም ከዚያ በፊት እነ አፄ ካሌብ እና አፄ ኢዛና (አብርሃ) ናቸው። ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ደረጃ ኮትኩተው ካሣደጓቸው ከዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ የላቀ ስኬት ለማስመዝገብ ብልህነቱም ሆነ መልካም አጋጣሚው ነበራቸው። ከሁሉም በላይ በጥቁር አፍሪቃ ብቻ ሣይሆን በዓለም ደረጃ «ደካማ» የሚባሉ የዓለማችን ዜጎች «ጠንካራ» በሚባሉት ቅኝ ገዢዎች ላይ አንፀባራቂ ድል ማስመዝገብ እንደሚችሉ እርሣቸው የመሩት የዐድዋው ድል ሕያው ምሥክር ነው። ስለዚህ እኒህን ሁሉ ታላላቅ ተግባሮች ባከናወኑ ንጉሠ ነገሥት ላይ ይህ ሁሉ ውርጅብኝ እና ስም ማጉደፍ በእነማን ፣ ለምን ተብሎ እንደሚካሄድ አብጠርጥሮ ማሣወቅ ያስፈልጋል።
ለመሆኑ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ማን ነበሩ? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የሸዋው ንጉሥ የኃይለመለኮት ሣህለሥላሤ እና የወይዘሮ እጅጋየሁ ለማ አድያቦ ልጅ ናቸው። በአባታቸው ወገን ኢትዮጵያን ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ያስተዳደረው የሰለሞናዊው ሥርወ-መንግሥት ደም ያላቸው ሲሆን እናታቸው ደግሞ ከጉራጌ ነገድ የሚወለዱ ናቸው። በእናታቸውም ሆነ በአባታቸው ወገን ያለው ዝርዝር የትውልድ ሐረጋቸው በደንብ ቢጠና ከሁለት በላይ ከሆኑ ነገዶች ቅይጥ ዘር እንደሚኖራቸው እሙን ነው። በዚህ ጽሑፍ ደረጃ ለማስተላለፍ የሚፈለገው ሃቅ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ቢያንስ ከሁለት የኢትዮጵያ ነገዶች የተገኙ እንጂ የዘመኑ ዘባራቂዎች በሐሰት እንደሚደልዙት «የዐማራ ንጉሠ ነገሥት» አልነበሩም። እርሣቸውም በየትኛውም አጋጣሚ ራሣቸውን በእንደዚህ ዓይነት መጠሪያ ገልፀው አያውቁም።MWAO_V2No7_አርብ ታኅሣሥ ፲፰ ቀን ፪ሺህ፮ ዓም_(Fr 27 Dec 2013)_የአኖሌ ሐውልት ጉዳይ-አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል-እንዳይሆን Read in pdf.

Filed in: Amharic News, eMedia, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.