1

ልጓሙን የበጠሰው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የስድብ ፈረስ፣ በዳኛቸው ቢያድግልኝ

 

በ ዳኛቸው ቢያድግልኝ

ፕሮፌሰሩ በጽሁፎቻቸው እንዲህ ብለውናል

“…በዓለም ሕዝቦች መሀከል ውድድር ቢደረግ ያለጥርጥር አበሻ አንደኛ ከሚወጣባቸው ነገሮች አንዱ ልመና ሳይሆን አይቀርም፤ ለአበሻ፣ ልመና የኑሮ ዘዴ ነው……” http://www.goolgule.com/abesha-and-begging-1/

“…አዳም አበሻ ሳይሆን አይቀርም፤ ሁሉንም ነገር ብላ ከተከለከለው በቀር ብሎ ያስቀመጠው ይመስላል፤ በላባችሁ ወዝ ብሉ ተብለው አዳምና ሔዋን መረገማቸውን አበሻ ገና አልሰማም፤ አበሻ የተፈጠረው ገነት ውስጥ ቁጭ ብለህ ያለውን ሁሉ ብላ በተባለበት ጊዜ ነው፤ እግዚአብሄር አበሻን ሁሉንም ብላ ሲለው ምናልባትም በጆሮው ጭራሽ አታስብ ብሎት ይሆናል …….” (ሰረዝ የተጨመረ)

እስከናካቴው “ሆድ” የሚባል ቃል ከአበሻ ቋንቋ ፈጽሞ ቢሰረዝ ቋንቋው ብቻ ሳይሆን አበሻም ጉድ ይፈላበታል። አዕምሮ ፣ ሕሊና የሚባሉትን ቃላት አበሻ አያውቃቸውም፤ ተግባራቸውንም ሁሉ ለሆድ ሰጥቶታል። (ሰረዝ የተጨመረ) http://www.zehabesha.com/amharic/archives/9015

ልጻፍ ልተው… ምናልባት… እንዲያው ምናልባት በዚሁ የሚያበቁ ከሆኑ አይቶ እንዳላየ ማለፍ ይሻል ይሆናል ስል ልጓሙን የበጠሰው የስድብ ፈረሳቸው በማንአለብኝነት ጋለበብን። ባእዳን አበሽ እያሉና እየሰደቡ ይገድሉናል። የራሳቸው ታሪክ በረሀብ ቸነፈርና ስደት የተሞላ እንዳልሆነ ሁሉ በመዝገበቃላታቸው ውስጥ ኢትዮጵያን የረሀብ ምልክት አድረገው የሚያዋርዱን በርካታዎች ናቸው። ፕሮፌሰሩ በአንድ ወቅት ሲሉ እንደሰማሁዋቸው ወያኔዎች ከዱር ወደከተማ ሲገቡ ህዝቡን ፈሪ ለማድረግና የሚያከብረው ምልክት ለማሳጣት በየቀዬው በህብረተሰቡ ዘንድ የሚከበሩትን እያፈላለጉ በአደባባይ ፂማቸውን ይዘው በመጎተት ያዋርዱዋቸው ነበር። ይህን መሰሉ የወያኔዎች ተግባር በሚያሳዝን ሁኔታ በፕሮፌሰሩም ላይ በተደጋጋሚ ደርሶባቸዋል። የወያኔዎች ኢትዮጵያዊነትንና ኢትዮጵያን የማዋረድ ዘመቻ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ታዲያ ይህ ባለበት ሁኔታ የእውቀት ጣርያ ላይ ደርሰዋል የሚባሉት አዛውንቱ ፕሮፌሰር መስፍንም በአሮጌና ያለአግባብ በተደረደረ ምሳሌ ይህን መከራ የበዛበትን ህዝባችንን በሚሸነቁጥ የጅምላ ስድብ መቀጥቀጣቸው ግር የሚያሰኝ ሆነብኝ። ይህ ወቅትና ሁኔታን ያላገናዘበ መፍትሄ የመጠቆም፣ የማስተማር አቅምም የሌለው ኢትዮጵያዊነትን የሚያዋርድ ጅምላ ስድብና ሽሙጥ በተከታታይ ሲወርድብን አይቶ እንዳላየ ማለፉ ክብራችንን ለማጉደፍና ለማዋረድ ኢትዮጵያችንን ለማንቋሸሽ ለሚተጉት ዱላ ማቀበል ይሆናል። እናም ይህ ጥያቄ ይከነክነኝ ገባ። እውን አበሻ ሥራ ጠል፣ ለማኝና ሆዳም ነውን? በምን ጥናት በማንስ ትንታኔ?

እድሜአቸውን ሙሉ ሀገራችንን አገልግለዋል ሲባል መስማቴ ብቻ ሳይሆን በባህላችን አዛውንት ይከበራልና ክብራቸውን የሚያጎድፍ ትችት ማቅረብ አልፈልግም። ቢሆንም ታድያ የሰሞኑ ማቆሚያ ያጣው የስድብ ጅራፍ ዘላቂ ጉዳቱ ከፍተኛ ነውና አክብሮቴን ሳላጎድል እባክዎን የስድብ ፈረስዎን ልጓም ያዝ አድርጉልን እላለሁ።
በሀገራችን አዋቂ ነን የሚሉ ሰዎች ከነሱ የተለየ ሃሳብ ይዞ የሚመጣን ተወያይቶ የተሻለውን ሃሳብ ከመደገፍ ይልቅ ለየት ያለ ሃሳብ ያቀረበውን አንገት የሚያስደፋ የስድብ ናዳ ማውረድ ይቀላቸዋል። ይህንን በመፍራት አዋቂዎቹ ግዙፍ ስህተት ሲፈጽሙ በዝምታ ማለፍ ለሌላ ስህተት በር መክፈት ይሆናል። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ጽሁፍን በይዞታው ሳይሆን በጸሃፊው ማንነት እየመዘኑ ጸሀፊው በግልጽ ያስቀመጠውን ሃሳብ ወደጎን ትተው ያልተባለውን መልካም ሃሳብ ፍለጋ እየማሰኑ የራሳቸውን ትርጓሜ ይሰጣሉ። ሰአሊ በስህተት የረጨውን ቀለም “አብስትራክት” ነው ብለው በምናባቸው ውብ ስዕል እንደሚሰሩት አይነት ከስድብ ጀርባ ሙገሳ መፈለጉ ከንቱ ነው።

የፕሮፌሰር ተከታታይ ጽሁፎች የተጻፉት ኢትዮጵያን በስፋት በማያውቅ ሰው፣ ሀሳብን ለህዝብ ለማቅረብ ምን አይነት ጥንቃቄ የተመላበት የምርምር ጥበብ አስፈላጊ እንደሆነ በማያውቅ ሰው ቢሆን፣ ሀሳብን የማስፈር ዓላማና ግብን መረዳት በማይችል የእውቀት አድማሱ ያልሰፋ፣ በሌሎች ሀገራት የሚኖሩ ሰዎችን አኗኗር በተመለከተ ምንም ግንዛቤ በሌለው ሰው ወይም እንዲያው ለፌዘኛ የመሸታ ቤት ቀልድ ሲባል ለተወሰኑ ታዳሚዎች የቀረበ ቢሆን ምንም ትኩረት መስጠት ባላስፈለገ ነበር። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ግን አለምን ተዘዋውረው የጎበኙና ያልኖሩበትን ዘመንና ያልጎበኙትን አገር ህዝብ አኗኗር በምርምርና በንባብ ጠንቅቀው የተረዱ እድሜ የጠገቡ ምሁር ናቸውና በምንም ጥናታዊ መረጃ ባልተደገፈ መንገድ የአንድን ጥንታዊና ታሪካዊ ሀገር ሕዝብ በዚህ መልኩ ማሳነስና ከሌላ ፕላኔት የመጣ ሰንካላ ፍጡር ማስመሰል እድሜያቸውንና እውቀታቸውን አይመጥነውም። የአንድ ሀገር 90 ሚሊየን ሕዝብ በአንድ ቅንፍ ውስጥ “አበሻ” ብለው ከተው እንኳን የሰው ልጅ ቀርቶ ማንኛውም ማህበራዊ እንስሳ የሚያደርገውን ተሳስቦ፣ ተዛዝኖ፣ ተካፍሎ መኖርን በዚህ መልክ አሳንሶ ኢትዮጵያዊነትን ማዋረድ ታላቅ ስህተት ….Re

Filed in: Amharic News, eMedia, Politics & Openion

Recent Posts

One Response to "ልጓሙን የበጠሰው የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የስድብ ፈረስ፣ በዳኛቸው ቢያድግልኝ"

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.