1

ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ እለምናቸዋለሁ። ሥርጉተ ሥላሴ 21.12.2013

ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ እለምናቸዋለሁ።

ሥርጉተ ሥላሴ 21.12.2013

በሴቶች ስሜት ውስጥ መሆንና በስሜቱ ውስጥ ሴቶችን ሆኖ ማሰብ ከባድ ነው።

እኔን ተብድሬው አላውቅም። እኔንም ተውሼው አላውቅም። እኔንም ሸቅጬው አላውቅም። እኔንም መስዬው ሳልሆን ሆኘው ስለምጽፈው በስሜቴ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ በአብዛኞቹ ሴት እህቶቼ ስሜት ውስጥ እንደሚኖር አስባለሁ። የድምፄ ምት ከማህጸኔ ይነሳል። የመንፈሴ ትንፋሽ ደግሞ የልቤን ክናድ ይንተራሳል። መንፈሴ ሰግሮ ሁነኛ ማረፊያ ወይንም ድልዳል ሲያጣ ትካዜ ሲዋኝበት የኖረ ቢሆንም፤ አሁን ከዘሃበሻ ጋር መታደሙ የመገለው ስቃይ ተግ ብሎለት ህምሙም ታግሶ፤ በስክነትና በቅደም ተከተል ማሰብና ከረመጥ ላይ የበቀለውን ጸጋ ማቆለማመጥ ጀመርኩኝ። ስለሆነም እኔ ራህብ ላይ ሆኜ ሌላ ራህብተኛ ለማስናገድ አቅሜን በሙሉ ቀን መርቆ የሰጠኝ አምላኬ፤ ምክንያት ፈጥሮ የመተንፈሻ ቀዳዳ ለፈቀደለኝ የዘሃበሻ ድህረ ገጽ ምስጋናዬን በሐሴት ጠልፌ ተቀበሉኝ በማለት እነሆ ጀመርኩኝ …sreate1

ሴቶች የመኖር ቋንቋ ናቸው። የኑሮ አይደለም። ኑሮ ቅርንጫፍ መኖር ግንድ። ውድ ወገኖቼ አጠቃላይ የነፃነት ትግሉን የአቅም ግንባታ፣ ጥበቃ፣ ያለውን ሃብት በቋሚነት ማዝለቅ እንዲሁም ስምሪት በተመለከተ ያላችሁበት በመሆኑ እሱን ተወት አድርጌ በዚህ ዙሪያ አንስት እህቶቻችሁ ያላቸውን ልዩ መክሊት አትኩሮት ብትሰጡት ሁሉም አካባቢ ያሉ ክፍተቶችን እንዴት ሊያበጅና ሊያሳምርም እንደሚችል በአላቸው  ዙሪያ  ትንሽ ነገር ለማለት ፈለግሁ።

Sirgute Silasse 21.12.13…… Read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, Social & Culture

Recent Posts

One Response to "ሴቶች ጥሩ ነገር አላቸው ጊዜ እሲኪሰጣቸው ድረስ ጠብቀው ይይዙት ዘንድ እለምናቸዋለሁ። ሥርጉተ ሥላሴ 21.12.2013"

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.