0

በልዩነት ላይ የተመሠረተው ሕገ-መንግሥት የአብሮነት ብቻ ሳይሆን ፀረ-ዕድገትና ፀረ-ልማት ነው!

በልዩነት ላይ የተመሠረተው ሕገ-መንግሥት የአብሮነት ብቻ ሳይሆን ፀረ-ዕድገትና ፀረ-ልማት ነው!

ባለፉት 28 ዓመታት “የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት” እየተባለ የሚጠቀሰው ከፋፋይና አናካሽ የሕግ የበላይነትን ሳይሆን በሕግ ስም የተወሰኑ ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ዐማራ የሆኑ ቡድኖችን ፍላጎት በማኅበረሰቡ ላይ ለመጫን ሥራ ላይ የዋለ ሕገ አራዊት ነው::  የአብሮነት  የኢትዮጵያዊነት የዐማራነት እና የኢትዮጵያዊነት የጋራ መገለጫ ዕሴቶች ጠላት ነው::  የዕድገት  የብልጽግና የሰላምና የካፒታሊዝም ሥልተ ምርት አውራ ጠላት ነው::  ይህም በመሆኑ የሕገ-መንግሥቱ ተሙዋጋቾች እንገነባዋለን ለሚሉት ገበያ መር ኢኮኖሚ ወይም ካፒታሊዝም ከኮሚኒዝም የከፋ ጠላቱ ነው:: ምክንያቱም ኮሙኒዝም የመደብ እንጂ የነገድ ጠላት የለውም:: የዓለምን ሠርቶ አደሮች ወደ አንድነት ለማምጣት እንጂ ባንድ አገር ውስጥ ለዘመናት ባንድነት የኖሩትን ሠርቶ አደሮችና አርሶ አደሮች በሚናገሩት ቁዋንቁዋ ልዩነትና በማንነታቸው አይከፋፍልም:: አንድ እንዲሆኑ ይጥራል እንጂ!

የኢፌዴሪ ሕገመንግሥትና በዚሁ ሕገ-መንግሥት መሣሪያነት የተከለሉት ክልሎች ፀረ-ካፒታሊስ ሥልተ ምርት ናቸው:: ይህም ነፃ የገበያ ኢኮኖሚ እገነባለሁ ከሚባለው መነባንባዊ ቃል ፍፁም ተፃራሪ ነው:: ምክንያቱም ካፒታሊዝም ወይም የገበያ ኢኮኖሚ ድንበር የለሽ ነው:: ድንበር አቁዋራጭ ነው:: የካፒታሊስቱ ፍላጎትም ሆነ የካፒታሊስት ሥልተ ምርት ሠፊ ገበያን ፈላጊ ነው:: ገበያው የብሔረሰቦችን ግድግዳ የሚሰባብር እንጂ ብሔረሰባዊ  ወይም ነገዳዊ ግንብ የሚገነባ አየለም:: ባለሀብቱ ካፒታሉን ሊያፈስ ሥራ ሊፈጥር የሚችለው ያላንዳች የማንነት መስፈርት ማነህ? ከየት መጣህ? የነማነህ? ሳይባል ራሱን አገሩንና ወገኑን ሊጠቅም የሚችልበትን አካባቢ መርጦ መሠማራት የሚችልበት ሁኔታዎች መመቻቸትን ይጠይቃል:: ከየትም አካባቢ ተነስቶ በመረጠው ቦታ ባሻው የሥራ ዘርፍ የመሰማራት ነፃነት በሌለበት አገር የገበያ ኢኮኖሚ ሊመሠርት አይችልም:: ሰዎች በሰውነታቸው ሳይሆን በሚናገሩት ቁዋንቁዋና ማንነት የሚመዘኑ ከሆነ ካፒታል ደንበር ተጥሎበታልና የኢኮኖሚ ዕድገት የሸቀጦች ዝውውር የሚታሰብ አይሆንም አይኖርም:: ይህ ከሆነ ደግሞ ፖለቲካዊ ሥርዓቱ ካፒታሊስት ሳይሆን ዘረኝነት ነው:: ዘረኝነት  ደግሞ ፀረ- ነፃ ገበያ ብቻ ሳይሆን የአንድነትና የአብሮነት ቅንቅን ነው::

 እነ አቶ ሌንጮ ለታ እንሞትለታለን የሚሉት የዘር ፌደራሊዝም ፀረ-ካፒታሊስ ሥልተምርት መሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም:: በአንፃሩ የአዴፓ አዲሱ አመራር ሕገ-መንግሥቱ መሻሻል አለበት! ከመግቢያው ጀምሮ የሚያገለውና ሊዋጋው የቆመ የኅብረተሰብ ክፍል አለ:: ይህ ኅብረተሰብ ደግሞ በውስጠ ታዋቂ ዐማራው ነው በማለት ያሰሙት  እና የወሰዱት አቁዋም ለዐማራው ኅልውና ከመቆርቆር አንፃር የተወሰደ  ብቻ እንዳልሆነ ዐኅኢአድ ይገነዘባል::  ይህ አቁዋም ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች ቆመንለታል ለሚሉት የገበያ መር ኢኮኖሚ ዕድገትና ሰላም መስፈን ሲሉ ሊከተሉት የሚገባ ነው:: ምክንያቱም  ይህ ሕገ- መንግሥት የአንድነት የዕኩልነት እና የሰላም ፀር ብቻ ሳይሆን የነፃ ገበያ እና ለተረጋጋ ማኅበራዊ ኑሮ እና ሰላም  ፀር በመሆኑ  ሊሻሻል ይገባል::

ይህ በአቶ ሌንጮ ለታ መነሻ ሀሳቡ ተረቆ በሻዕቢያ በሕወሓት እና በኦነግ የሽግግር ጊዜው ቻርተር  ሆኖ ያገለገለና በመጨረሻም ለኢፌዴሪ እርሾ የሆነው ሕገ-መንግሥት በሚከተሉት ምክንያቶች መለወጥ እንዳለበት ዐኅኢአድ ያምናል:: እነዚህም:-

  1. ፀረ-ኢትዮጵያዊነትና ፀረ-አብሮነት ስለሆነ:

  2. ፀረ-ካፒታሊስት ሥልተምርት ስለሆነ:

  3. ፀረ-ልማትና ሰላም ስለሆነ:

  4. ፀረ-ዐማራ ስለሆነ:

  5. ኢትዮጵያዊ ባለሀብቶች በፈለጉበት አካባቢ ካፒታላቸውን እንዲያፈሱ የማያስችል በመሆኑ:

  6. ሕገ-መንግሥቱ የብጥብጥ መነሻ በመሆኑ በአገሪቱ ሰላም እንዳይሰፍን ዋናው ምክንያት በመሆኑ :

የሕዝቡ ነባር አንድነትና መተሳሰብ እንዲመለስ አብሮነትና የተፋጠነ ዕድገት የሚሹ ወገኖች የነዚህ ሁሉ ፀር የሆነው ሕገ መንግሥት እንዲለወጥ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እንዲያሰሙ ዐኅኢአድ ጥሪውን ያቀርባል::

 

የዐማራው ኅልውና መጠበቅ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበስ ዋስትና ነው!

 

የአማራ ኅልውና የኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፤

Filed in: Amharic News, Politics & Economics, Politics & Openion, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.