0

ዐማራ   የራሱን   ኅልውና   አስከብሮ  እንዴት  ከሌሎች   ጋር  በመተባበር   የኢትዮጵያን   አንድነት   ማስጠበቅ   ይችላል ??

    ማራ የራሱን ኅልውና አስከብሮ  እንዴት  ከሌሎች   ጋር  በመተባበር   የኢትዮጵያን   አንድነት   ማስጠበቅ   ይችላል?

ዛሬ   በዐማር   ሕዝብ   ላይ   በመዝነብ   ላይ   ያለ    ያላባራ   የዘር   ፍጂት  ዐማራ   በመሆኑ   የመጣ   አይደለም።    ይህ   ሕዝብ   እንደሌሎቹ   ነገዶች   ወደራሱ   ወደ ውስጥ  ተመልካች   ሕዝብ   ቢሆን   ኖሮ   የዚህ   የዘር   ማጥፈት   ሰለባ   ባልሆነ   ነበር።  የሱ   መከራው   የሚመነጨው   ኢትዮጵያዊ   ከመሆኑ  ነው።  

ለዚህ   ኢትዮጵያዊ   ለሆነ   ሕዝብ   እራሱን   ከተሰነዘረበት   እልቂት   ማትረፍ   ማለት ፣  እዚያው   በዚያው   ኢትዮጵያን   መታደግ   ማለት   ነው።   የሁለቱን   ነፃነት   በፍጹም   ለያይቶ   ማሰብ   አይቻልም።   በተቃራኒው   ለቆሙት   ጠላቶቹም   በትክክል   እሱን   ማጥፋት   ማለት   ሀገሪቷን   እንደፈለጉ   ሲሻቸው   ጠቅልለው   ሕዝቡን   በባርነት   ይዘው   የኢኮኖሚው   ባለቤት   የሚሆኑበት፣   ሳይሻቸውም   ከፋፍለውና   በትነው   የየራሳቸውን   የባንቱስታን   ሀገር   ተብዬዎችን   መሥርተው   የሚቀራመቷት   መሆኑን  በሚገባ   የተረዱበት  ነው። 

ዐማራው   ይህ   ባለሁለትዮሽ   ኃላፊነት   ታሪክ   በሱ   ላይ   የጣለው   ሸክም   መሆኑን    የተረዳ   ሕዝብ   ነው።   በመሆኑም   ዛሬ   ባአንድ   በኩል   ለራሱ   እንደ   ሕዝብ   መቆም   ይታገላል   በሌላው   በኩል   ለሀገራዊ   አንድነት   ሲል   የተቀሩትን   የሀገሪቱን   ነገዶች   በማሰባሰብ   በጋራ   ከሱ   ጋር   እንዲሰለፉ   የማድረግ   ተግባር    ይሠራል።   እነዚህ   ሁለት   የተያያዙ   ተግባሮች   በአንድ   ጊዜና   በአንድ   የትግል   ጎዳና   ውስጥ   የሚራመዱ   ሥራዎች   ናቸው።   ዛሬ   አንዱን  ነገ   ሌላውን   የምንለው   አይደለም።   

ለነገዶቹ    የአዐማራን   ኅልውና   የማስጠበቁ   እዳ   የዐማራው   ብቻ  እንዳልሆነ   እንዲረዱት   ማድረግ   የኛ   ሥራ   ነው።   እንሱም   ለዐማራ   ኅልውና   መታገል   ማለት   በተዘዋዋሪ   ለነሱ  የጋራ   ቤት   እውን   መሆንና   መቀጠል   መሠረትና   ዋስትና   ሰጪ   መሆኑን   ግንዛቤ   እንዲኖራቸው   ማድረግ   ይገባል።   የሁሉም   ነገዶች   የአንድነት   ዋልታ   በዚህ   እውቅና   ላይ   የተመሠረተ   እንዲሆን   እንሠራላን  ።   ይህንን   ሥራ  በተገቢ መንገድ ካቀላጠፍንና   ከግቡ   ካደረስን   የኢትዮጵያን   አንደነት   በነበረ መልካም ታሪካችን ላይ ተጨማሪ እርከን  ገነባን ማለት ነው ።    የዐማራ   ኅልውና   ለኢትዮጵያ   አንድነት  ድርጅት  ሲመሠረት   እንደ   ዓላማ   ይዞት   የተነሳው   እነዚህን   ሁለት   የማይለያዩ   አንድነቶችን   እውን   ለማድርግ  ነው። ግቡም    በሰው   ልጅ   ነፃነት እና ዕኩልነት  ላይ   ያጠነጠነ   የነገዶችን   አንድነት   እውን   በማድረግ     እናት   ሀገር   ኢትዮጵያን   ከወደቀችበት   ማንሳት   ነው።

ኢትዮጵያ   በጀግኖች   ልጆቿ  ኅብረት  ከወደቀችበት  ትነሳለች!

ውድ   እናት  ሀገር   ኢትዮጵያ  ለዘለዓለም  ትኑር!!

Filed in: Amharic News, News, Politics & Economics, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.