0

 

 ለኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ የሚበጀው!

 እንግሊዞች አፍሪካን በቅኝ ግዛታቸው ሥር አውለው ሕዝቡን ባሪያ የተፈጥሮ ሀብቱን የግላቸው መጠቀሚያ ለማድረግ የቀየሱት ቅያሽ ሕዝቡን ከነባር ማንነቱ ባህሉ ዕሴቱ ወጉ  ልማዱና ቁዋንቁዋው በማፋታት የአውሮፓውያንን ባህል ወግና ዕሴት ተከታይ ማድረግ የሚል እንደሆነ ይታወቃል:: በተመሳሳይ ሁኔታ ጣሊያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛቱዋ ሥር ለማዋል የተከተለችው ሥልት ሮማን ፕሮቻስካ በተሰኝ ሰላዩዋ አማካኝነት ተጠንቶ Ethiopia:-The powder Barrel (ኢትዮጵያ :-የባሩድ) በርሚል መጽሐፉ ለጣሊያኑ ሞሶሎኒ ብቻ ሳይሆን ለምዕራባውያን ኃይሎች የሰጠው ምክር ከእንግሊዝ ጋር ተመሳሳይ ነው::

እንዲህ ነው ያለው! ኢትዮጵያዊነት ማለት ዐማራነት ነው:: ዐማራው ደግሞ በቁጥሩ ከሌሎች ትንሽ ነው:: ግን ሌሎችን አሥሮ ይዙዋል:: ዐማራን ከኢትዮጵያ ብናነሳው ኢትዮጵያ የምትባል አገር አትኖርም:: ምክንያቱም ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት:: ከእስሩ ሲፈታ ሁሉም ወዳሻው ይሄዳል:: ይህ እንዲሆን ደግሞ የአገሪቱና የሕዝቡ የአንድነት ምልክት የሥልጣን ምንጭ የሆነውን ዘውዳዊ ሥርዓት  የዘውዱ ርዕዮተዓለማዊ ክንድና የሕዝቡ ሃይማኖታዊ ሰንሰለት የሆነውን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትና በዚህ ዙሪያ የሚደራጀውን ዐማራ የተሰኘ ነገድ ማጥፋት ሲቻል እንደሆነ ጻፈ::

የዚህ ትርክት ግብ ምን እንደሆነ በቅጡ ያልተረዳው ዋለልኝ መኮንን የተባለ ይህን መጽሐፍ እንዳለ በመገልበጥ “ ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት! ባህሉ ያማራ  ልብሱ ያማራ  ወጡ ያማራ ሃይማኖቱ ያማራ” ወዘተ በማለት ሌሎች ነገዶች በዐማራው ላይ በጠላትነት እንዲነሱና የየራሳቸውን ጎጆ እንዲቀልሱ ቀሰቀሰ::

በተለምዶ የ60ዎቹ የሚባለው ትውልድ የዚህ ትርክት ሰለባ ሆኖ ሁሉም በዐማራና በኢትዮጵያዊነት ዕሴቶች ላይ ዘመተ:: ነገዶች በማንነታቸው  ዙሪያ ተደራጅተው ዐማራንና ኢትዮጵያዊነትን በጠላትነት ፈርጅው ከኢትዮጵያ አገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲወጡ ብዙ ርቀት የተጉዋዘ ሥራ ተሠራ:: የሰው ልጅ የዘራውን ይሰበስባልና ዛሬ በአገራችን ውስጥ የምናየው የእርስ በርስ ፍጅት የዚህ ዘር ፍሬ  መሆኑ ግልጽ ነው::

ችግሩንና የችግሩን ምንጭ ከተረዳን ከዚህ እንዴት እንውጣ? ብሎ መጠየቅና አማራጭ ሀሳቦችን ማፍለቅ የትውልዱ በተለይም ለኢትዮጵያ አንድነት ከቆሙ ኃይሎች የሚጠበቅ ነው:: በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በነገዱ ያልተደራጀ የለም:: በእያንዳንዱ ነገድ ስም ከሁለት በላይ ድርጅቶች ተመሥርተዋል:: ሁሉም ሊባል በሚችል ደረጃ የኢትዮጵያዊነት የወል ዕሴቶችን ዐማራ የተሰኘውን ነገድ እና አብሮነትን እንደ ጠላት አምነው የተቀበሉና እንዚህ እንዲጠፉ የሚችሉትን ያህል የሚሠሩ ናቸው:: ይህም የማዕከላዊውን መንግሥት አዳክመው የክልል መንግሥታትና በነገዶች ዙሪያ የተደራጁ ቡድኖች እጅግ አክራሪ እና ጽንፈኛ የሆኑ  አቁዋሞችን በመያዝ ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ይዘዋል:: ይህ ጽንፈኛ አቁዋም ለእልህ መወጫ ካልሆነ ለማንም ይጠቅማል ተብሎ አይታሰብም:: ጥቅም ካልነው የሚጠቅመው ኢትዮጵያ እንድትጠፋ ፕርጀክት ነድፈው ለሰጡን የውጭ ኃይሎች ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጠቀመው በመለያየት ሳይሆን በአንድነቱ ነው:: 

አንድነቱ እንዲጠናከር ደግሞ ለዚህ የቆሙ ኃይሎች ከጽንፈኛ አቁዋም ወጥተው የመሀል አቁዋም ሲይዙ ነው:: ኢትዮጵያን ከገጠማት ወይም ከቆመችበት መስቀልኛ መንገድ የሚያወጣት የመሀል መሥመር ጉዞ ነው:: የወል ዕሴቶችና የአብሮነት ዋስትና ሰጭ ነውና! በአንፃሩ  የግራውም ሆነ የቀኙ መንገዶች አጥፊዎች ናቸው::  ምክንያቱም የወል ዕሴቶችና የአብሮነት ጠንቆች ናቸውና!

ስለሆነም የኢትዮጵያ አንድነት ዘመኑ በሚጠይቀው የአንድነት ማዕቀፍ ውስጥ ተጠናክሮ ለመቀጠል የመሀል መንገዱን መያዝ ግድ ነው:: ምክንያቱ መሀሉ ሚዛናዊ ብቻ ሳይሆን የግራ ቀኙን ኃይሎች ፍላጎትም ፈጽሞ ገፊ አይደለም:: አካታች ነው:: ይህ ዕውን እንዲሆን ደግሞ ሕዝቡ የፖለቲካ ቡድኖችን ዓላማ አጢኖ እና አገናዝቦ መካከለኛው መንገድ የቱ እንደሆነ ለይቶ የሚጠናከርበትን ሁኔታ  ማመቻቸት ይጠበቅበታል::

ሰሞኑን በእያንዳንዱ ክልል የሚታዩት እንቅስቃሴዎች የፍጭው ፈንግጭው እና ባልጠቅም እጎዳለሁ ዓይነት ነው:: ይህ ደግሞ ለአብሮነት ጠንቅ ነው:: አብሮነት ከወየበ ኢትዮጵያዊነት በጽኑ ይታመማል:: ሕመሙ የከረመ ቢሆንም በሽታውን  ያባብሰዋል:: የተባባሰ በሽታ ደግሞ ሕይዎት ይቀጥፋል:: ከቀጠፋው ለመዳን ፍቱኑ መድኃኒት መካከለኛውን መንገድ ማጠናከር ነው:: የአገራችን አብሮነት አስጠብቆ ለመዝለቅ የሚበጀን መንገድ መካከለኛው መሥመር ነው:: 

በዐማራ ኅልውና  ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት እምነት  የኢትዮጵያ የመዳኛዋ ብቸኛው የፖለቲካ ጎዳና ጽንፈኝነትን የሚገራ በውይይትና በመግባባት የሚያምነው የመሀል መንገድ ፓለቲካ ነው ።

 

በትግላችን አብሮነታችን ይታደሳል!

 

 

 

Filed in: Amharic News, News, Politics & Economics, Politics & Openion, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.