0

ይሄ ሁሉ ሸፍጥ…ለማንም አይበጅ!!

የአማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) ድርጅታዊ መግለጫ 
ቀን፡ ጥቅምት ፳፮/፳፻፲፩  ቁጥር፡ ዐ/ኅ/00፪/፳፻፲፩ 
                                     

የሸፍጥ ብዛት ለተነሱት “የማንነት ጥያቄዎች” መፍትሔ ይሆን ይመስል የትግሬ ወያኔ አሁንም በተካነበት ሸፍጥ መቀጠሉን መርጧል። ለሸፍጡ ማስፈጸሚያ ሆነው እያገለገሉት ካሉ መንግስታዊ ተቋማት መካከል ደግሞ የፌዴሬሽን ምክርቤት የሚባለው በዋናነት ይጠቀሳል። ለዚህም ደግሞ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደ “ዋናው ዐማራ ጠሉ” አቶ ዓባይ ፀሓዬ የመሰሉቱን የፌዴሬሽን
ም/ቤት ጉዳዮች ሚኒስትር አድርጎ በመሾም በዐማራ ነገድ ላይ የተፈጸሙ ባለ ብዙ ፈርጅ የዘር ፍጅትና መሬት ነጠቃ ድርጊቶች ዛሬም ድረስ የሚረሱ አይሆንም።
የትግሬ ወያኔ ከወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ድፍን ራያና በሂደት ደግሞ ከመተከል ጋር በተያያዘ ለፈጸማቸው ወንጀሎች ከአሁን ቀደም በግልጽ የሚታወቁ ሦስት ተደጋጋፊ ሸፍጦችን አከናውኗል። እነሱም፦
፩ኛ/ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ ለምና ሰፋፊ የዐማራ መሬቶችን ለመውረር የየካቲት ፲፱፻፷፰ ዓ.ም ማንፌስቶ ያወጣ መሆኑ፣

፪ኛ/ በተራ ቁጥር ፩ የተጠቀሰውን ማንፌስቶ ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ ከ፲፱፻፸፪ ጀምሮ በዐማራ ነገድ ተወላጆች ላይ ጭካኔ የተሞላበት የዘር ፍጅት፣ እስራት፣ ማፈናቀል፣ የመሬት ወረራና ሀብት ነጠቃ ከመፈጸሙ ጎን ለጎን አዳዲስ ሰፋሪዎችን ከትግራይ በብዛት በማምጣት፣ ከሱዳን ከስደት የተመለሱ የትግራይ ተወላጆችንና ከትግሬ ወያኔ ጦር ተቀነሱ የተባሉ ታጣቂዎቹን ከሙሉ መሳሪያ ትጥቃቸው ጋር በነዚህ የዐማራ መሬቶች ላይ ማስፈሩ፣

፫ኛ/ በተራ ቁጥር ፪ የተፈጸሙትን ባለብዙ ፈርጅ ሸፍጦች “ሕጋዋ ሽፋን ለመስጠት” አስቦ ዐማራ ያልተሳተፈበትን ሕገመንግስት ተብየውን ሊጠቀም ቢሞክርም “የማንነቱ ጥያቄው ይብስኑ ገፍቶ በመምጣቱ ምክንያት” ከማንነት ጥያቄው ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነትና እውቅና የሌላቸውን ግለሰቦች በመመልመል የማንፌስቶው ማስፈጸሚያ ኮሚቴ አካላት አድርጎ ለማቋቋም በፌዴሬሽን ም/ቤት አፈጉባኤ በሆኑት ኬሪያ ኢብራሂም መገለጹ ሌላው ዐይን ያወጣ አራተኛው ሸፍጥ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ይህ የትግሬ ወያኔ ዐይን ያወጣ ተከታታይ ሸፍጥ በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ባለብዙ ፈርጅ ጥቃት በሚገባ የሚታወቅ ሆኖ ሳለ አሁን ደግሞ የየካቲት የማንፌስቶ ፈጣሪዎችና የመሬት ነጠቃው ዋና መሓንዲሶች የነበሩትና አሁን የትግራይ ትብብር ለብሔራዊ ዴሞክራሲ (TAND) ም/ሊቀመንበር ናቸው የሚባሉት አቶ ግደይ ዘራፂዮን “የራያ ጉዳይ በሕገ-መንግስቱ መሰረት
ሊታይ ይገባል” ማለታቸው እጅግ በጣም ያሳዝናል። ምክንያቱም የማንነት ጥቃቄው የተነሳባቸው አካባቢዎች ትግሬ ናችሁ ተብለው ፍዳቸውን እያዩ ያሉት በየካቲቱ ፲፱፻፷፰ ዓ.ም ባወጡት በራሳቸው ማንፌስቶ መሰረት እንጅ “የተሰነይ ሰነድ” የሚባለው ሕገ-መንግስት ጭራሽ እንደማያውቃቸው በሚገባ ይታወቃልና ነው።

እርግጥ ነው የዚሁ የትግሬ ወያኔ ድርጅት መስራችና ሊቀመንበር የነበሩት ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ስለ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ጉዳይ ከኢሳቱ ሲሳይ አጌና ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የዐማራ መሬቶች የተያዙበት ዋናው ምክንያት “ወደ ሱዳን መውጫና ከሱዳን መግቢያ አስፈላጊ ስለሆኑ እንጅ” በማለት የባለቤትነቱ መብቱ የማን እንደሆነ እውነቱን በአደባባይ መናገራቸው ይበል የሚያሰኝ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ያስፈልጋል።

በመሆኑም የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) አቋምን ከወዲሁ በድጋሜ ግልጽ ማድረግ የግድ በመሆኑ የማንነቱን ጥያቄ ካነሱት የወልቃይና ድፍን ራያ ወገኖቻችንና በዐማራ ነገድ ዙሪያ ከተደራጁ የዐማራ ድርጅቶች ጀርባ ሆኖ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ኬሪያ ኢብራሂም አማካኝነት የሚቋቋም ኮሚቴም ይሁን ጉዳይ አስፈፃሚ አካል ለተነሳው የማንነት ጥያቄ ተገቢ መፍትሔ ሊያቀርብ የማይችል መሆኑ ከወዲሁ ታውቆ ይህ ዓይነቱ አግላይና ሌላ ዙር ሸፍጥ የተሞላበት አካሄድ እንዲቆምና ወደ ትክክለኛው የመፍትሄ መንገድ ሊመጣ ይገባል ብሎ በጽኑ ያምናል።  ይህም፦

፩ኛ/ የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ መንግሥት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከፍተኛ ቦታ በመስጠት በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ድፍን ራያና እንዲሁም በመተከል “ሰላምና መረጋጋት ሊፈጥር” የሚያስችል በቂ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአስቸኳይ መመደብ፣

፪ኛ/ ዘመናዊ ትጥቅ ይዞ የጦርነት ከበሮ በመደለቅ ግድያና አፈና እያካሄደና ሰላማዊ ወገኖቻችንን እያሸበረ ያለው የትግሬ ወያኔ ልዩ ኃይልና ስውር ታጣቂ እነዚህን አካባቢዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳ ለቆ እንዲወጣ ማድረግ፣

፫ኛ/ በትግሬ ወያኔ ከቀያቸው የተፈናቀሉ የየአካባቢ ተወላጆች ወደ መሬቶቻቸውና ቤቶቻቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱ እንዲደረግና እንዲሁም በተለያዩ የማሰቃያ ጉድጓዶችና እስር ቤቶች ያሉ የየአካባቢው ተወካጆች ከማሰቃያ ጣቢያዎች በአስቸኳይ ተለቀው በተመሳሳይ ሁኔታ በቀያቸው ሰላማዊ ሕይወት እንዲጀምሩ ማድረግና እነዚህን ከላይ የቀረቡትን አስቸኳይ የመፍትሔ ተግባሮች ተከትሎ የተነሳው የማንነት ጥያቄ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው አካሎችና በዐማራ ነገድ ዙሪያ ከተደራጁ ድርጅቶች ጋር በውይይትና በመግባባት ተገቢው መልስ የሚያገኝበትን ሕጋዊ አካሄድ መከተል ናቸው።
በመጨረሻም የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) የትግሬ ወያኔ የተለያዩ ሸፍጦችን በመጠቀም በሕገወጥነት መንገድ የወረራቸውን የዐማራ እርስቶች/መሬቶች እስኪመለሱ ድረስ መሬታቸው ከተወሰደባቸው ወገኖቻችን ጋር በመሆን እስከመጨረሻው ድረስ በጽናት አብሮ የሚቆም መሆኑን ለሁሉም ግልጽ ማድረግ ይፈልጋል።

የዐማራ ኅልውና መጠበቅ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!! 

የአማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ)

 

Filed in: Amharic News, Politics & Economics, Politics & Openion, Social & Culture, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.