0

የዐማራ ኀልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(ዐኀኢአድ) የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን አደረገ !!

 
 
“የዐማራ ኀልውና ለኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት/ዐኀኢአድ የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን ያደረገው በባህርዳር ከተማ መስከረም 13/2011ዓ.ም በዐማራ ብድርና ቁጠባ መስሪያ ቤት ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ሲሆን የድርጅቱን ጥሪ ሰምተው ከተገኙ የባህርዳር ና አካባቢው ነዋሪዎች፣ አባላት እና ደጋፊዎች በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡ውይይቱን በንግግር የጀመሩት የዐኀኢአድ ከፍተኛ አመራር አቶ ተክሌ የሻው ሲሆኑ ለተሳታፊው ራሳቸውን ፣ የድርጅት ጓዳቸው አቶ ተስፋዬ መኮነንን ስራ ና ኃላፊነት ካስተዋወቁ በሗላ የድርጅታቸውን የአገር ውስጥ ህቡዕ እንቅስቃሴ ጨምሮ “ከሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት” ሲቪክ ድርጅታዊ ጅማሮ እስከ የፖለቲካዊው ድርጅታቸው ዐኀኢአድ አጠቃላይ  ቁመና አጭር ማብራሪያ ከሰጡ በሗላ መድረኩን ለተወያዮቹ ክፍት በማድረግ ከተሳታፊዎች ለሚቀረቡ አስተያዬት፣ና ጥያቄዎን በመቀበል እንዲሁም ምላሽ ሲሰጡ ቆይታ አድርገዋል፡፡ከውይይቱ ተሳታፊዎች ለቀረቡት ጠንካራ ህዝባዊ ጥያቄዎች ሁሉቱ የዐኀኢአድ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊዎችን ባረካ መልኩ መልስ ሰጥተዋል፡፡ከተሳታፊዎቹ የቀረቡት አንኳር ጥያቄዎች መካከል ስለ ድርጅቱ ዓላማ፣መርሕ፣ግብ ና ከሌሎች የዐማራ ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶችም ሆነ ከሌሎች የአገሪቱ ፖርተመዎች ጋር ያለው አንድነት ና ልዮነት፣ስለ ሚከተለው ርዕዮት፣ስለ ድንበር፣ወሰን ና የማንነት ይገባኛል ጥያቄዎች ዐኀኢአድ እንዴት ይመለከታቸዋል!? ድርጅታዊ መዋቅሩ ጥንካሬ በግለሰብ ላይ የተንጠለጠለ ነው ወይስ? የሞረሽ መስራች ና ሊቀመንበር የፖለቲካ ፖርቲው ሊቀመንበርም አቶ ተክሌ እንደሆኑ ጠቅሰው ድርጅቱ በአንድ ሰው ጫንቃ ላይ የተንጠለጠለ እንዳይሆን በሚል ስጋት አዘል ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ 

የዐኀኢአድ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው፣የድርጅቱን አጠቃላይ ቁመና ከመነሻ እስከ መዳረሻ ዘርዝረው ለተሳታፊው ሲገልፁ “ዐኀኢአድ መነሻው ዐማራነት መዳረሻው ኢትዮጲያዊነት ነው”በማለት ተናግረው ድርጅቱ በጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ እንደ “ሙጃ ገርጅፎ በመታዬት ነገ የሚጠፋ ሳይሆን እንደ ወይራ ተክል ስር ሰዶ ና ጥንካሬውን ይዞ ዘመን የሚሻገር ህዝባዊ ድርጅት እንደሆነ ጠቅሰው ህዝቡ ሙሉ በሙሉ የወሳኝነት መብቱን እንዲጠቀም ማስቻል የትግላችን አቅጣጫ ነው ብለዋል፡፡አቶ ተክሌ ስለ ዐማራ ድርጅቶች መብዛት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ዐማራ ተገፍቷል ዐማራ፣በደል ደርሶበታል፣ና ከጥፋት ራሱን ተደራጅቶ ይከላከል ብሎ ሲጮህ የነበረ አካል ዛሬ ዐማራ ዐማራ የሚል ድርጅት በዛ ብሎ መቃዎም ልክ አይደለም፣ከዚህ በተጨማሪ የዐማራን ትግል እኔ እኔ አቀጣጠልኩት እኔ ጀመርኩት የሚል ግብግብ መኖሩንም እያዬን ነው፣ይህ ወደፊት ይገለጣል ከፕ/ር አስራት ወልደዬስ ቀጥሎ የዐማራን በደል በመናገር እና ዐማራ ተሰባስቦ ከጥፋት ራሱን እንዲከላከል ከሰሜን አሜሪካ፣አውሮፖ አውስትራሊያ፣እና የመሳሰሉ አገራት በመዞር ዐማራው እንዲደራጅ ከማድረግ ጀምሮ በዐማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጥፋት የሚያሳይ 1972-2007ዓ.ም ድረስ የተፈፀመውን የዘር ማጥፋት ና ፅዳት  የሚያሳይ657 ገፅ ያለው”ምፅዓተ ዐማራ የተሰኘ መጽሃፍ አሳትሞ በዓለም ላይ ባሉ ዋና ዋና ቋንቋዎች አስተርጉሞ ለ”ተባበሩት መንግስታት ድርጅት” ማቅረብ ከመቻሉም በላይ በሞረሽ ድርጅት ስር “የዐማራ ድምፅ”የሚሆን ሬድዮ አቋቁሞ አገልግሎት እዬሰጠ እንደሆነ ጨምረው አሁን በሚመሩት የፖለቲካ ድርጅት ልሳን “መቅደላ”የተሰኘ በዬ 15 ቀኑ የሚታተም የኢንተርኔት ጋዜጣ  እንዳለው አክለው በመግለጽ ድርጅታቸው  በርካታ እንቅስቃሴዎችን አከናውኗል ሲሉ አስታውቀው፡ዐማራው ከተቃጣበት ጥቃት መዳን የኀልውና ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡አቶ ተክሌ ቀጥለው ያነሱት ነጥብ “ፍፁም ትክክል ፍፁም ስህተት ነገር የለም” ስለሆነም አሁን የተፈጠረውን ና በህዝቡ ትግል የተገኘውን ውጤት ና ውጤቱ እኔዲገኝ አስተዋፅኦ ያበረከቱ የ”ኢህአዴግ”ባለስልጣናት ማመስገን አስፈላጊ ነው፣በትንሹ ያላመሰገነ በትልቁ ሊያመሰግን አይችልም፣እና በርካታ እስረኞችን እንዲፈቱ ላደረጉ ሰዎች ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባ ተናግረው፣የህዝቡን ብሶት አዳምጠው “እኛን ከስደት እንድንመለስ ና ከናነሸ፡፡ከናንተ ጋር እንድንገናኝ ላደረጉ አካላት ክብር መስጠት ና ማበረታታት ተገቢ ነው በማለት ከተናገሩ በሗላ ተሰብሳቢውን ዛሬ ይች ሀገር የእኛም የእናንተም ናት ነገ እናንተ ናት ስለሆነም ዛሬ የጋራ የሆነች አገራችን የተሻለች ለማድረግ የእኛ ና የእናንተን ትብብር፣ልምድ ልውውጥ ና ምክክር አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ተክሌ የዐማራ ኀልውና ለኢትዮጲያ አንድነት ድርጅት” ከስሙ ተነስተው ዐማራው አባቶቹ በሰሯት አገር የመኖር፣የመስራት የመንቀሳቀስ፣በማንነቱ የመኩራት መብቱ ተነፍጎ፣በሐረርጌ፣በባሌ፣በወለጋ፣በኢሊባቡር፣በመተከል፣ብቻ አይደለም በጎንደር የመኖር ዋስትናውን ተነፍጎ የህልውና አደጋ የተጋረጠበት በመሆኑ ትግሉ የመኖር ያለመኖር ጥያቄ እንጅ ባህሌን ተጫኑት ዴሞክራሲ ጠፋ የሚሉ ጉዳዮች ለዐማራው ቅንጦት እንደሆነ ጠቅሰው ትግሉ የህልውና ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ስለዚህ ዐማራው የራሱን ኀልውና አስጠብቆ የኢ/ያን አንድነት ለማረጋገጥ ጠንክሮ ይታገላል ካሉ በሗላ ኢትዮጲያን ከዐማራነት ነጥለን ማዬት ለእነ ወያኔ ከነቡድኑ ና ምዕራባዊያን ጠላቶቻችን በቀደዱልን ቦይ መፍሰስ ነው፣ዐማራን ለማጥፋት ሌት ተቀን የሚሰሩት አካላት ዐማራ በመሆኑ ብቻ አይደለም ኢትዮጲያዊ ስለሆነ እንጅ፣ዐማራ ለኢ/ያዊነቱ ቀናዒ ጠንካራ አቋም ስላለው ነው፡፡የዐማራ ጠላቶች ኢትዮጲያን የሚያጠፉት ዐማራን ካጠፉ እንደሆነ የዘመናት ህልማቸው መሆኑን እንዳይዘነጋ ያስፈልጋል፣ዐማራን በአውራ ጠላትነት ፈርጄው ነፍጠኛ፣ትምክተኛ፣እያሉ ጥፋቱን ሲደግሱ መኖራቸውን እያስታወሱ፣ኢ/ያዊያን በልዮነታችን ላይ ትኩረት አድርገን እንጅ አንድ በሚያደርገን መደራጄት አለመደብንም፣በማለት ከ1960ዎቹን ወደሗላ ተመልሰው የመደብ ና የብሔር ጭቆናዎች አሉ በሚሉ ጎራዎች ተከፍለው በዝባዢ ና ጨቋኝ በሚል ተፈርጆ ለእልቂት የተዳረገው ዐማራው ነው፡፡ቀጥለው ከ27ዓመታት ወዲህ ደግሞ በትግሬ ወያኔ ሴራ እንዲጠፋ የተደረገው ዐማራ ነው፣አባይ፣ፋሲል ግንብ፣አፄ ንብለደንግል ሀውልቶች ላይ ተሰቅለው የነበሩትን መፈክሮች፣የእነ ለገሰ ዜናዊን “ዐማራ ሲልመን ማዬት ደስታው፣ዐባይ ና ጠናን አድርቆ፣የከብት መዋያ እንደሚያደርገው የተናገራቸውን በማስታወስ በአሁኑ ሰዓት በአፍሪካ ከፍተኛው ድህነት የተመዘገበው በዐማራ ነው በማለት ጨምረው ገልፀው በዐማራ ላይ እዬተደረገ ያለውን ደባ በቁጭት ለስብሰባው ተሳታፊ አስገንዝበው፣”ተገድሎ ተገዳድሎ የማያልቅ ተነቅሎ የማይደርቅ” በሚል የታተመውን “ምፅዓተ ዐማራ” መፅሃፍ በኢንተርኔት አማዞን በተባለው ድህረ ገፅ ላይ ፈልጎ ማንበብ እንደሚቻል ጠቁመው ወደ ፊት የገንዘብ አቅም ፈጥረው አገር ውስጥ እንዲታተም ጥረት ይደረጋል ብለዋል፡፡የዐማራው ኀልውና ተረጋገጠ የሚባለው፣ ዐማራው እንደማንኛውም ኢ/ዊ በኢ/ያ ምድር እንደፈለገው ተንቀሳቅሶ የመኖር፣የመስራት፣በፈለገው ስራ የመሰማራት ዕድሉ ሲጠበቅ፣ይህ እንዲሆን ደግሞ ከፋፋይ ና በታኝ የሆነው ህገ-መንግስት የዜጎችን ማንነት የነፈገው፣በግለሰብ ነፃነት ላይ የተመሠረተ ኢ/ዊያን የአገራቸው ባለቤት መሆናቸው የሚያረጋግጥ ህገ መንግስት ሲኖር እና ዐማራው በዚህ  ህገመንግስት የራሱን አሻራ ማኖር ሲችል እንደሆነ እና ይኸ ሲሆንም የግለሰብ ነፃነት ተጠብቆ የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ዐማራው በፈለገው የኢ/ዊ ምድር ያለ አንዳች ከልካይ የሚኖርበት ሁኔታ ይጠበቃል ብሎ እንደሚያምን አስረግጠዋል፡፡በዚህ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ያደረጉት አቶ ተስፋዬ መኮነን ስለ ድርጅቱ እና ስለ ዐማራው መደራጄት አስፈላጊነት ማብራሪያ ሰጥተዋል፣አቶ ተስፋዬ ድርጅት ሀይልን አሰባስቦ ለአንድ አላማ ና ግብ አቅዶ የሚሰራ የአስተሳሰብ አንድነት ፈጥሮ  በህብረት የሚጓዝ ለመጓዝ የሚመሰረት ነው ካሉ በሗላ ዐማራ ካለበት አስቸጋሪ ጊዜ መደራጄት ኀልውናውን ለማስጠበቅ የሚጠቀምበት መሳሪያው ነው ብለዋል፡፡የዐኀኢአድ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ተስፋዬ አያይዘው የዐማራን መደራጄት ማገዝ ማበረታታት፣ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው አብይ ጉዳይ ነው ካሉ በሗላ ይህን የለውጥ ጭላንጭል ከማንኛውም ጊዜ በላይ መጠበቅ ያለበት በአንድነት የሚያምነው አካል በተለይም ዐማራው መሆን አለበት ብለው በክልል መታጠር ና የጠባብነት አስተሳሰብ የዐማራው መገለጫ መሆን አይገባውም፣ዐማራነት ዐቃፊነት፣አሰባሳቢነት፣ጠባቂነት፣አስተዋይነት፣ቻይነት ና ታጋሽነቱን አጠናክሮ የአባቶቹ የእነ አፄ ምኒልክን ቴዎድሮስን፣በላይ ዘለቀን ጀግንነታዊ ውርስ አስጠብቅ መቀጠል አለበት፣ብለው አሰባሳቢነት፣የትልቅ ህዝብ ና የሰፊ ህዝብ ተግባር ነው፣ብለው ጀርመንን፣ኢንግላንድን(እንግሊዝን)፣ፐርሽያን እና የመሳሰሉ አገራትን በምሳሌነት ጠቅሰው ዐማራ ኀልውናውን አስጠብቆ ኢ/ያን በአንድነቷ ፀንታ እንድትቀጥል የማድረግ ሀላፊነት አለበት ብለው፣በክልል ታጥሮ፡ከተቆጠረው ህዝብ ብዛት በላይ በሌሎች የኢ/ያ ግዛቶች ውስጥ ያለው ዐማራ ቁጥር እንደሚበልጥ ጠቁመው ይህንን ሰፊ የዐማራ ህዝብ በአለበት ፀንቶ በማንነቱ ኮርቶ አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲጓዝ ማድረግ የዐማራ ኀልውና ለኢ/ያ አንድነት ድርጅት አላማ እንደሆነ እና ከሌሎች የአንድነት ሃይሎች ጋር በመወያዬት ህብረት፣ትብብር፣ግምባር ከተቻለም ውህደት በመፈፀም እንደሚሰራ አስታውቀው፣ዐማራ ባለበት ቦታ ፀንቶ መቆዬት እንጅ መሸሽ በፍፁም እንደማይገባ እና ድርጅታቸው ዐኀኢአድም በሌሎች አካባቢዎች በመዘዋወር ከዐማራ ና ከሌሎች የአገሪቱ ነገዶች ጋር ምክክር እና ውይይት፣እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ዐኀኢአድ የመጄመሪያ ህዝባዊ ውይይቱን ሲያደርግ ሰፊ ጊዜ የተሰጠው ተሳታፊ፣የሚሰማውን በነፃነት ሲጠይቅ አስተያዬቱን ሲሰጥ የቆዬ ሲሆን ከተነሱት አንኳር ጥያቄዎች ውስጥ” የወሰን፣የማንነት፣የብሔርተኝነት፣የድርጅት የትግል ስልት፣ ና የፋይናንስ አቅም ጉዳዮች ተነስተው በሁለቱ የዐማራ ኀልውና ለኢ/ያ አንድነት ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች፣ ተሳታፊዎችን ባረካ መልኩ ምላሽ እንደተሰጠባቸው ከተሳታፊዎቹ ከተገኘ ግብረ መልስ ለመረዳት ተችሏል፡፡
“ዐኀኢአድ በመጭወቹ ተከታታይ እሁዶች በተለያዬ ዐማራዊ ከተሞች ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶችን እንደሚያደርግ ከተያዘው መረሐ ግብር ለማወቅ ተችሏል፡፡
 
 
 
 
Filed in: Amharic News, News, Politics & Economics, Politics & Openion, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.