0

የአካባቢዉ ተማሪ ስለ ብርሸለቆ ያሰራጨዉ ነዉ!!

ሰላም ወገኖች ይህ ከታች የምትመለከቱት ብርሸለቆ የማነዉ በሚል አንድ የአካባቢዉ ተማሪ 
ስለ ብርሸለቆ ያሰራጨዉ ነዉ!!ልጁ ተማሪ የነበር ሲሆን የወያኔ ጀኔራል ተብዮዎች ወገናችን
የሚያሰቃዩበት የእንግልት ማዕከል ነዉ:ለማንኛዉም ይህን ተመልከቱት!! 
ጉዳዩን ለሚመለከተዉ ሁሉ መሳወቅ ተገቢ ነዉና ሁላችንም የየራሳችን ጥረት እናድርግ!! 
የዐማራ ኅልዉና በየትኛዉም የሀገራችን ክፍል በወያኔ መድሎኛ አስተዳድርና ወረራ ለሚሰቃዩ 
ሁሉ ድምጹን ከማሰማት አይቦዝንም!! ለማንኛዉም ይህን ከታች ያለዉን ተመልከቱት!! 

የብርሸለቆ እርሻ ልማት የማን ነው?የአላህሙዲ ወይስ የቀን ጅቦች?በአላህሙዲ ስም መነገድ ይብቃ (በሃይማኖት አንማው ተጨማሪ ሃሳብ በአሸብር አካልነህ)

☞ብርሸለቆ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የሚገኝ ሰፊ የእርሻ ልማት ቦታ ነው፡፡ብርሸለቆ ቅኝ ግዛት የሠፈነበት ቦታ ነው፡፡ እርሻ ልማቱ ለቅኝ ገዥዎች ሲሳይ፤ብር ሲሆን ለተገዥዎች ደግሞ ሸቆ የሆነ ቦታ ነው፡፡እርሻ ልማቱ ከማንኩሳ ይጀምራል በግምት ርዝመቱ 45 ኪሎ ሜትር የሚገመት ሲሆን ስፋቱ ደግሞ እስከ 7 ኪሎ ሜትር ይደረሳል፤ቦታው በሁለት ሲከፈል ላይ ብር እና ታች ብር ይባላል ታች ብር የመከላከያ ማሰልጠኛ የሚገኝበት ቦታ ነው ሁለቱ በአንድ ላይ ተጠቃለው ሲጠሩ ብርሸለቆ ይባላሉ፡፡ የብረሸለቆን እርሻ ልማት በደንብ ተዋውቂዋለሁ፤ግፈኛ እርሻ ልማት ነው የሠው ደም የሚጠጣ፤በእጅ አዙር የጉልበት ብዝበዛ የሚካሄድበት ቦታ ነው፤በሁለቱ ብሮች በኢትዮጵያ የመጨረሻ ድሃና የዋህ ህዝብ የሚኖርበት ቦታ ነው፡፡ እርሻ ልማቱ በጉልበት ሠራተኝነት ሠወችን ቀጥሮ ያስራል፡፡ ሠራተኞቹ ወዝአደር ይባላሉ በላቡ የሚያድር ማለት ነው የእነሡ ግን ከዚህ በላይ ነው በደሙ የሚያድር ቢባል ይቀላል፡፡ ብረሸለቆ ወዛደር ከሆንክ ስርቶ ማደግ የሚባል ነገር አይታሠብም፤እናቶች በባዶ እግራቸው በዚያ በርሃ እግራቸው በእባብ ተነድፎ ሠውነታቸው በጋሪጣ ተሠነጣጥቆ ያለ ሃኪም ደማቸው ሲፈስ ሲታይ እንዴት ያማል መሠላችሁ ጎበዝ፡ ቦታው ለም አፈር በመሆኑ የሚገኝው ምርት ብር እንደሸለቆ የሚታፈሰብት ቢያደርገው ምስኪኑ ወዛደር ግን የበይ ተመልካች ሆኖ ቀርቷል፡፡ የአካባቢው ተማሪ በመሆኔ እኔም የገፈቱ ቀማሽ ነበርኩ ትዝ ይላችሁ ከሆነ ጓደኞቼ ሌሊት 9 ስዓት ተነሥተን እርሻ ልማቱ 11፡30 በመድረስ ክላስ ከመግባታችን በፊት በቆሎ እና በርበሬ እንድንሰበሰብ ይደረግ ነበር ያልሰበሰበ ደግሞ ወይ ይገረፋል ወይ ካርዱን አያገኛትም፡፡ ወዛደሮቹ በቀን የሚከፈላቸው ገንዘብ ከ5 ብር ያልበለጠ በመሆኑ ቤተሠባቸውን ለመረዳት የቀን ጉርሻቸውን ለማገኜት ይቸገሩ ነበር አሁንም እየተቸገሩ ይገኛሉ፡፡ እርሻ ልማቱ በቂ የመብራት ሃይል ቢኖረውም ሠራተኞቹ በኩራዝ ነው የሚጠቀሙት ቆርቆሮ ቤት መሥራት ክልክል በመሆኑ በሣር ቤት ወይም በላስቲክ ቤት ይኖራሉ፤እንስሳት ማራባት አይቻልም ዶሮም ቢሆን ፡ እንዲህም ሆነው ልጆቻቸውን ለማስተማር ጥረት ያደርጋሉ፡ ግን እርሻ ልማቱ የማን ነው? የሚገርመው አዝመራው ተሠብሰቦ ካለቀ በሇላ ማሣው በእሳት እንዲቃጠል ይደረግና ወዛደሮች የአረረ በቆሎ ካገኛችሁ ፈልጋችሁ ውሰዱ ይባላሉ እነዚያ ምስኪን እናቶች በተለበለበ መሬት ገብተው ቃርሚያ ፍለጋ ሲኳትኑ ሲታዩ እንዴት አንጀት ይቆርጣሉ፡፡
አርሶ አደሮችን ለመከላከያ ማሰልጠኛ ነው ቦታውን ልቀቁ በማለት ከቦታቸው የሚያፈናቅል(በተለይ እኔ በደንብ የማውቀው (የጭይት አርሶና አረብቶ አደር መሬታችንን ተነጥቀናል በማለት ድምፃቸው ሰሚ ጀሮ አጥቶ እስካሁን ድረስ ይጮሃል
በትውልድ ቀያችን ግፍ ይበቃናል፡፡

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር!

Filed in: Amharic News, News, Politics & Economics, Social & Culture Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.