0

ወያኔ ሀርነት ትግራይ የጥፋት መልክተኛ ነው !!

በቅዳሜው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ለተጎዱ ቤተሰቦች

ዐኅኢአድ የተሰማውን ሐዘኔታ እየገለጸ እግረመንዱንም መሰረታዊ ጉዳዮችን አንስትዋል ….                                                                                                                                                                                                                                                                                                                   

ወያኔ ሀርነት ትግራይ የጥፋት መልክተኛ ነው !!

በዚህ ጨካኝ አረመኔ የሽብር ድርጊት ሕይዎታቸውን ላጡ ገነትን፣ ለቆሰሉና ለተጎዱ ፈውስን፣ የሚወዷቸውን ላጡ መጽናናትን እንዲሰጥልን ፈጣሪያችንን እንለምናለን!!

ትላንት ቅዳሜ ሰኔ ፲፯ ብዙዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በየከተሞች በራሱ አነሳሽነት በሰላም ወጥቶ በተሰበሰበበትና የሰላም እጁን በዘረጋብት፣ የፍቅርና የአንድነትን መዝሙር በሚዘምርበት አደባባይ ላይ ጸረ ህዝቡ ወያኔ የጭካኔ እጁን ዘረጋ። ይህ የጥፋት ድርጅት ይህንን እንደሚያደርግ ፍርሀት የነበረን በመሆኑ በዐማራ ድምፅ ራዲዮ (ዐድራ) አስቀድመን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ምክሮች ተሰጠዉ ነበር። የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) የወያኔ አረመኒያዊ ጭካኔ በዐማራው ህዝብ ላይ እንደ መአት ሲያዘንብበት፣ ከራሱ ከዐማራ ግዛቱ ሲያፈናቅለው፣ ከዱር እንዲያድርና በአውሬ እንዲበላ ሲያደረግ፣ ሌሎችንም በዚህ ግፍ እንዲተባባሩ ሲያሰማራ ተቃውሞውን ሲያሰማና ግፉን ሲያጋልጥ መምጣቱ ይታወሳል። ዐኅኢአድ ድርጅታችን ዛሬም ያልበረደውን የዐማራን ህዝብ ፍጅትና ከርስቱ የመነቀል እኩይ ድርጊት ከማጋለጥ አልቦዘነም።

ይሁንና አብዛኛው ተቃዋሚ ይህንን በዐማራው ላይ ሲዘንብ የነበረ የጥፋት መአት አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ፊቱን ሲያዞርበት የኖረ መሆኑን ሁላችንም የምናዉቀዉ ነዉ። ወያኔ በዚያው በዐማራ ጥፋቱ የሚቆጠብ የመሰላቸዉ እነሆ ባስከፊ ሁኔታ ስቃዩና ጥፋቱ ለሁሉም ህዝባችን በወረፋ እየደረሰው ነው። ይህ እጅግ በጣም ያሳዝነናል። ያስቆጣናልም።  ይህ የወያኔ ሀርነት ትግራይ የጥፋት እርምጃ አድማሱን አስፍቶ ህዝባችንን በአሰላ፣ በድምቢዶሎ፣ በምስራቅ ሀረርጌ፣ በኦጋዴን፣ በአዋሳ፣ በወልቂጤ፣ በጅማና በወለጋ የተከታተለ ጥፈት ድርጅታችንን በእጅጉ አሳዝኗል። የዐማራ ኅለውና ለኢትይጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ ያለ ዜጋ ሁሉ እኩል የምንወድቅለትና እኩል ለመብቱ የምንታገልለት ህዝባችን ነው። ይህ በዚህ እንዳለ የቅዳሜዉ የአዲስ አበባው የግድያ እርምጃ “ሙከራ” ተብሎ የተወረወረዉን ቦንብ ድርጊት በቀላሉ የሚገለጥ አይደለም። ቢሳካ ኑሮ ታላቅ ጥፋት ለማድረስ የታቀደ እንደነበር እናስባለን።

ቢሳካ ኑሮ ታላቅ እልቂትና መተራመስ ይፈጸም ነበር። በዚያ እልቂት ግርግርና ሽፋን ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ከፍተኛ ባለስልጣኖችን ይረሸኑ ነበር። አስከትለውም ራሱ ገዳዩ አጋዚ ወታደራቸውን አዲስ አበባን እንዲወርና የለመደውን ግድያና አፈና እንዲያካሂድ በማድረግ የሰዓት እላፊ አዋጃቸውን ያውጁ ነበር። በመጨረሻም የለመዱትን ወታደራዊ ጁንታ መንግስታቸውን መመስረታቸው አይቀርም ነበር። ባይከሽፍ ኑሮ የጥፋቱ ሂደት ከዚህ ውጪ ሊሆን አይችልም ነበር።

የኢትዮጵያ አምላክ ተጨምሮ በህዝቧ ጀግንነት ግን ሴራዉ ከሸፈ። ለክሽፈቱ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው በወጣት የተሞላው የመስቀል አደባባይ የነቃ ህዝባችን ከሴሬኞች ጋር ግብግብ በመግጠሙና የዉርዉራዉን አቅጣጫ በማስቀየሩ መሆን ስንሰማ ሰማዕታትን አደነቅን።  ህዝቡ ቢሸሽና ቢተራመስ ኖሮ ምናልበትም ከቦንቡ ፍንዳታ በኋላ ብዙ እልቂትን ለመፈጸም የተዘጋጀ ኃይል ገብቶ በህዝቡ ላይ በመተኮስ እርስ በርስ በመተረማመስ እንዲተላለቅ ማድረግ ይችሉ ነበር ።
ህዝቡ ግን ጸጥ ብሉ የቆመበትን መሬት ባለመልቀቁ የትርምስ ሞትን ሊከላከል በመቻሉ የታሰበዉ ትርምስና ፍጅት ሊገታ ችሏል።
እናም ሙከራውን በእንጭጩ አከሸፈው። ምስጋና ለነቃው ታላቅ ህዝብችንና ራሳቸዉን ፈጥነዉ ቤዛ ላደረጉ ወጣቶች!! ምስጋና ለነቃው ወጣት ህዝባችን!! በነዚህ ቆራጥ ወገኖቻችን ኢትዮጵያ ተደግሶላት ከነበር ጥፋት አመለጠች። ምርመራው በእውነት ከቀጠለ ሰፊ የሆነ የሙከራውን ድር የምናየው ይሆናል።
ይሁንና ይህ የመጀመሪያ የወያኔ ጥቃት ሙከራ ነው። ወያኔ የዘረፈውን ወርቅ ያጋበሰው በኃይል በያዘው ስልጣኑ ነው። ያንን የወርቅ ሰገነት በቀላሉ በአንድ ሙከራ ይተዋል ብሎ ማለት ተላላነት ነው።

እናም ገና የተደጋገመ ሕዝብን የማተራመስና ጠቅላይ ሚኒስትሩን የመግደል ሙከራ ያደርጋሉ ። ይህ እንዳይሆን ግን መፍትሄው የህዝባችን በየሚኖርበትና በየሚሰራበት ሁሉ እንቅስቃሴያቸውን ባይነቁራኛ መመልከት ወስኙ የመከላከያ መንገድ ነው። ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስቸኳይ የተቃዋሚ ኃይሎችንና በሀገራቸው ያገባናል የሚሉትን ኃይሎች የሚያካትት የሽግግር ጉባኤ መጥራትና የድሉን ፍሬ በጋራ የመመከት ጉዳይ አንገብጋቢ መሆኑን ሊረዱት ይገባል። ይህም ክቡር ሕይዎቱን ቤዛ ያደረገዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ የለዉጡን ሂደት ይበልጥ እንዲደግፍና ወደ ትክክለኛዉ ዴሞክራሲያዉ ሥርዓት የሚወስደን ብቸኛ መንገድ ከመሆኑንም በላይ የወያኔን የጥፋት ኃይልን አንቅሮ እስከወዲኛዉ ለማትፋት ያስችላል። ወያኔ ላለፉት ፪፰ ዓመታት በሕዝባችንና በአገራችን ላይ የፈጠረዉ ምስቅልቅሉ የወጣ ሕይዎት አሁን እየተባለ ባለዉ የጥገና ለዉጥ ሂደት መፍትሄ የሚገኝለት አለመሆኑን በጽሞና ማሰብና በቆራጥነት ወደ ወሳኙ የሥርዓት ለዉጥ መምጣት የግድ ይላል።

ይህ ሲሆን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በዚች ታላቅ አገራችን ታሪክ ላይ ልዩ የሆነ አሻራቸዉና ከማሳረፍ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ተነፍጎት ለኖረዉ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሥረታ ይበቃል። ታሪክ መሥራት ማለትም ይሄ ነዉና!!
የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት አቋሙ ግልጥ ነው። እንደ ወያኔ ያለን መርዛማና ዘረኛ ቡድን በትረስልጣኑን ጨብጦ ላላፉት ፪፰ ዓመታት የፈጠረዉን ዘረኛና አምባገነናዊ ሥርዓት መለወጥ የሚባቻለዉ በመሰረታዊ ለውጥ እንጂ በጥገና ለውጥ በመቀባባት መሻር አይቻልም ብለን በጽኑ እናምናለን። በተለይም የችግሩ እምብርት የሚያጠነጥነዉ በሕገመንግሥቱ ጭምር በመሆኑ ለዚህ ሁነኛ መፍትሔ በሁሉም ተሳትፎ ይጠይቃል።

ከዚህ ጋር በማያያዝ ቢያንስ ለአጭር ጊዜ እንኳ የወያኔን የጥፋት ሙከራዎች ለማክሸፍ ከዚህ በታች የሚከተሉት ሊደረጉ ይገባል ብለን እናስባለን። ይህ የጥፋት ሙከራ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻው አይሆንምና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አጠባበቅ ይጠንክር። ቤተመንግሥቱን በዉርስ የያዙት የወያኔ ጠባቂዎችና አጃቢዎች ከመለወጥ አስፈላጊነት ባሻገር የጠ/ሚ የዕለት ከዕለት እንቅስቃሲያቸው በሚስጥራዊነት ይካሄድ።

እንዲሁም የዕለት ከዕለት የስራ ፕሮግራሞቻቸው ራሳቸዉን ለጥቃት አጋልጦ የማይሰጥ ይሁን! አሁን የሚታየው የሰባዊነት ሆያ-ሆዬ ሰከን ይበል። በተለይም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚጠበቀው ኃላፊነቶች በወያኔ በዉርስ
የተያዘዉ ፖሊሱን፣ መከላከያውንና ደኅንነቱን ባስቸኳይ ከጠባቦችና ዘረኞች ማጥራት መሆን ይኖርበታል።

የዐማራ ኅልውና መጠበቅ የኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!
እናት ኢትዮጵያን እንታደጋት!!

 

                                                                               በዐኅኢአድ  ልዩ ዕትም ፳፬ ሰኔ ፲፯ ቀን ፪ ሺ ፲ ዓ.ም
Filed in: Amharic News, English News, News, Politics & Economics, መቅደላ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.