0

ውሸትን እየደጋገሙ እውነት በሚያስመስሉ ሃይሎች እየተሰረሰረና ክፉኛ እየተጎዳ ላለው —ለአዲስ አበባ ህዝብ!

ትኩረት

በአዲስ አበባ ፷(60%) የሚሆነው ነዋሪ ብሄረ ዐማራ ፣ 19.2% የሚሆነው ኦሮሞ ፣ 7.64% የሚሆነው ትግሬ ሲሆን ወደ ፩፫(14%) የሚሆነው ደግሞ ደቡብ (አብዛኛው ከሰባት ቤት) ነው። በአዲስ አበባ ፺(90%) የሚሆነው የአማርኛ ቐንቐ ተናጋሪ ፣ ፲(10%) የሚሆነው የኦሮምኛ ቐንቐ ተናጋሪ ፣ ፰(8%) የሚሆነው የጉራገኛ ቐንቐ ተናጋሪና ፬(4%) የሚሆነው ደግሞ የትግረኛ ቐንቐ ተናጋሪ ነው። በሃይማኖት ረገድም የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ፰፪(84%) ፣ የእስልምና እምነት ፩፪(12%) ፣ የኢትዮጲያ ሙሉ ወንጌል (3.2%) ሲሆኑ የኢትዮጲያ ካቶሊክ እምነት ደግሞ 0.8% ናቸው። ነገር ግን ወለጋ ፣ አርሲና ሚኒሶታ ያሉ አክራሪ ኦሮሞዎች የአዲስ አበባ ህዝብ ኦሮምኛ ተምሮ እርስ በእርሱ በኦሮምኛ መነጋገር አለበት ይላሉ። ይህን ፍትሃዊ ያልሆነ ጥያቄ በሃሰተኛ ስሜታዊነትና ልዘዛ እሚያራግቡት በናዝሪት፣ ደብረዛይት ፣ ጅሩ ፣ ጅማና ወዘተ ያሉ 70% የሚሆኑት የአማርኛ ተናጋሪዎች በቐንቐቸው የመተዳደር ፣ የመምረጥና የመማር ስነ-ዜጋዊ መብት ላይ ለማፌዝ ነው። ስለዚህም የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአስቸኴይ እነዚህን በናዝሪት ፣ ደብረዛይት ፣ ጅሩ ፣ ጅማና ወዘተ የተወሰዱ መብቶች ያክብር! የአዲስ አበባ ጉዳይ ደግሞ የከተማው ነዋሪ ካለው ማህበራዊ ፣ ናሙናዊና ፍላጎታዊ አግባብ አንፃር ነዋሪዉን ማዕከል ባደረገ መልኩ ብቻና ብቻ ይወሰናል ።

የአዲስ አበባ ህዝብ በአማካኝ ቆዳ ስፋት ከፍተኛ የሆነ የግብር ገቢ ለኢትዮጲያ መንግስት ቢያስገባም በጤና ፣ በትምህርት ፣ በአካባቢ ጥበቃና በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች አንፃራዊ በሆነ መልኩ ሲታይ ሲበዛ ተጎጂ ነው።

በአዲስ አበባ ከሚገኙ ታሪካዊ የነበሩ ማንነቶችና ማህበረስቦች አመላካች ጭብጦች ውስጥ የዋሽ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን አበይት ነው። የቤተ ክርስትያን አባቶች እንደሚሉት ከሆነ የዋሽ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን በአራተኛው(4AD) ክ/ዘመን በአበው ፋና ወጊነት የተጠበበ ሲሆን የታሪክ ተመራማሪዎች ደግሞ ወደ ፩፩ኛው(11AD) ክ/ዘመን ያደረሱታል። በተለይም ከአስራ ስድስተኛው ክፍለዘመን መለስ ለረዥም ጊዜ በተከታታይ ከተከናወኑት የኦሮሞ ፍልሰቶችና መስፋፋቶች ቦሃላ የሴማውያን ማህበረሰቦችና ቐንቐዎች በአዲስ አበባም(በዚያን ጊዜ በራራ) እንዲጠፉና በጉዲፈቻ እንዲቀየሩ ተደርጎ ነበር።
በራራና ፊንፊኔ የከተማዋ የሩቅና የቅርብ ጊዜ ታሪካዊ ስሞች ነበሩ። ፊንፊኔ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፍላጎት ዉጪ ከምርጫ ፱፯(97) ክፍተት ቦሃላ በሰርጎ ገቡ የአዲስ አበባ የበቀል አስተዳደር የተጫነ ስም ነው። ኦህዲድ በአዲስ አበባ የራስ ገዝ አስተዳደር ላይ ምንም ስልጣን ባይኖረውም ሎቢ ማድረጉ ትክክል አይደልም። ከንቲባ ድሪባ ኩማም የራስ ገዝ አስተዳደር ከንቲባ ሆኖ ለኦህዲድ በቀጥታ እሚሰራ መሆኑ ከፍተኛ ግርታን ፈጥሯል። አብዛኛው የከተማው ነዋሪም ለምን <በራራ> ወይም <ዋሽ ሚካኤል> የትይዩ ስም እንዲሆን ሃስብ አልተነሳም ሲሉ በንዴት ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ የበቀል አስተዳደር

ከምርጫ ፱፯ ቦሃላ አ.አ ህዝብ ላይ የተጫነው አሰትዳደር ህዝቡን የማይወክል የበቀል አስተዳደር ነው። የከተማውን ነዋሪ ለመጉዳት የተጫነ የበቀል አስተዳደር ነው። ጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ሲነሳ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ፖሊሶች ሰልፉን ለመቆጣጠር እንደማይላኩ ፤ ከምርጫ ፱፯ ቦሃላም የአ.አን ህዝብ ለመቆጣጠር የተላከው(የተጫነው) አስተዳደርም በከተማው ህዝብ በጣም የተጠላ ፣ ለከተማው ህዝብ ጥቅም የማይደራደር ፣ የከተማውን ህዝብ ክፉኛ የጎዳ የበቀል አስተዳደር ነው። የዚህ እኩይ የበቀል አስተዳደር ጊዜም ያለቀ ቢሆንም በከተማው ህዝብ ላይ የሚሰራው ስርነቀል ደባ ስላላለቀ ምክኛት በመፍጠር እድሜውን ለ፩ ዓመት አራዝሞታል።

አዲስ አበባ ከትግራይ ክልል የበለጠ የህዝብ ቁጥርና የሃገር ውስጥ የግብር ገቢ አሃዝ ቢኖረውም በኢፌዴሪ ምክር ቤትና በኢህአዲግ ማዕከላዊ ኮሚቴ ምንም ድምፅ የለውም። ብዙዎች እንደሚሉት ከሆነ አዲስ አበባ ህዝብ ላይ የሚደረገው ነገር ሁሉ < በተለይ ዐማራና ጉራጌ ላይ የሚደረግ ህገወጥ መንግስታዊና መዋቅራዊ ወንጀል ነው።> በአሁኑ የኢህአዲግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአዲስ አበባ ራስ ገዝ አስተዳደርና የሱማሌ ክልል በኢህአዲግ ምክር ቤት ሊኖረቸው ስለሚገባው ቀጥተኛ ውክልና ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከሚካኤል አራጌ
argawmichael@gmail.com
Filed in: Amharic News, News, Politics & Economics, Politics & Openion, Social & Culture

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.