0

ከሁሉም በፊት የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [አብን] በመመስረቱ የተሰማንን ደስታና ኩራት እንገልጻለን ::

 

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ሰኞ ሰኔ ፬ ቀን ፪ሺህ፲ዓ.ም. ቅጽ ፮ቁጥር ፲፩                   የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዐብን) በመቋቋሙ የደስታ መግለጫ!

 

ከሁሉም በፊት የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [አብን] በመመስረቱ የተሰማንን ደስታና ኩራት እንገልጻለን::

የዜጎች መብት በማይታወቅባት፣ በተለይም የዐማራው ህልውናና ማንነት ባልተከበረባት፣  የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ በእርግጠኝነት የዐማራወን ዕጣ ፋንታ በእኩልነት ለመወሰንና
ለማስተናገድ የሚያስችል ጠንካራ የዐማራ ነገድ ኃይል ይሆን ዘንድም ጽኑ ፍላጎታችን ነው:: ለሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መመሥረት መሠረታዊ ምክንያቱ የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ
በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከተቆናጠጠበት ጊዜ አንስቶ በዐማራው ነገድ ላይ በታቀደ፣  በተጠናና በተቀነባበረ መንገድ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት
ተግባር ነው።

በተለይም በ2004 ዓ/ም በደቡብ የኢትዮጵያ ክፍል፣ በማጅ ዞን፣ ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን፣ አገራችሁ አይደለም ብሎ በዘራቸው ብቻ፣ ከሌሎች ነገዶች
ነጥሎ፣  ቁጥራቸው በብዙ አስር ሺዎች የሆኑትን በአንድ ጊዜ ቤት ንብረታቸውን ነጥቆ የማባረሩ እና ይህም የዘር ማጽዳት ሂደት የዐማራ ክልል ተብሎ ከተከለለው ጭምር በልዩ
ልዩ ምክንያቶች ዐማራው የተባረረና መባረሩ የማይቀር መሆኑ በውጭ የሚኖሩ የዐማራው ነገድ ልጆች ዘግይቶም ቢሆን በመገንዘባቸው፤ ይህን ለመቋቋም የዐማራው ነገድ መደራጀት
አለበት ብለው ቁርጠኛ ውሣኔ ላይ በመድረሳቸው ነው፡፡ በነዚህም ዓመታት ውስጥ ዐማራው የራሱን እውነተኛ ታሪክ እንዲያውቅ፣ የተጋረጠበትን የህልውና አደጋ እንዲገነዘብ፣ ተደራጅቶ
ማንነቱን እንዲያስከብርና የራሱ እጣፋንታ ወሳኝ እንዲሆንና ባጠቃላይ የተረጋጋ ህይወት እንዲመራ የሚያስችለውን የዜግነት መብቱን በትግሉ እንዲያመጣ ሞረሽ ወገኔ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ ማድረጉን እያስታወስን፤  ዋና ዋናዎችን ለመጥቀስ ያህል ፥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወቅታዊውን ሁኔታ የቃኙና አስተማሪ መግለጫዎችን አውጥቷል፣ በትግራይ ወያኔ ፖሊሲ
ተቀርጾ በዐማራው ላይ የተፈጸመውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት የሚጨምሩ ወንጀሎችን አስጠንቷል፣ እንደታሪክ መድብል ሊያገለግል የሚችል ምጽአተ ዐማራ የተሰኘ መጽሐፍ
አዘጋጅቶ ለንባብ አብቅቷል፣ የዐማራው የማንነት ጥያቄ በኮለኔ ደመቀ ዘውዴ እና ወገኖቹ ሲፋፋም፣ ዐማራው ያራሱ ድምጽ እንደሚያስፈልገው በመገንዘብ የዐማራ ድምጽ ራዲዮ
ተቋም አቋቋሟል።
ዐማራው በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ እንደሌሎቹ ነገዶችና ጎሳዎች ሁሉ፣ ኅልውናው ተጠብቆ፣ በማንነቱ እየደረሰበት ያለው መገደል፣ መሳደድ፣ ታሪኩን ማጉደፍ፣ ንብረቱ
እየተዘረፈ ከቀየው መፈናቀል ቆሞ፣ በፈለገው ቦታ፣ባሻው የሥራ መስክ የመኖርና ተንቀሳቅሶ መሥራት ሁለንተናዊ መብቱና ክብሩ ተከብሮና ተጠብቆ ማዬት፤ እና የሕዝባዊ የዜግነት
መርሆዎች/ሲቪክ ናሽናሊዝም/ የተሰኙት የወል የዜግነት መገለጫ የሆኑ ዲሞክራሲያዊ ሥራዓትና የሕግ የበላይነት አንድነቷ በተጠበቀ ኢትዮጵያ አገራችን ሰፍኖ ማዬት፤ የሚሹ
ኃይሎች ሁሉ የሞረሽ ወገኔን ራዕይ የሚጋሩ ስለሆነ ቋሚ አጋሮች ናቸው፤ አብሮም ለመታገል ሞረሽ ወገኔ ምንጊዜም ዝግጁ ነው:: በመሆኑም የዐማራውን ሕዝብ ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ
በማድረግ የትግል ውጤት ለማስመዝገብ ሲባል እንኳንስ ከወገኖቻችን ጋር ቀርቶ ከባዕድ ጋርም ቢሆን መስራት ስለሚያስፈልግ የዐማራው ሕዝብ ጥቅም ተጠብቆ የትግሉ ራይና
ተልዕኮ እንዲሳካ ሰኔ ፪፣ ፳፲ ዓ፨ም በባሕርዳር ከተማ ከተመስረተው የዐማራ ብሔራዊ ንቅናቄ [ብዐን] ጋር ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት በአጋርነት የሚቆም መሆኑን እናረጋገጣለን::
ታላቁ የዐማራ ሕዝብ ሊመራው የሚችል ጠንካራ ኃይል ካገኘ ጠላትና ወዳጁን አበጥሮ የሚለይ አስተዋይና ብልህ ሕዝብ ነው:: ስለዚህ ትግሉ አምጦ የወለደው ይህ ንቅናቄ
በዐማራው ሕዝብ ልብ ተቀባይነት እንዲያገኝ የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግ ዐማራውን ከፈጽሞ ጥፋትና ጽዳት በተባበር የአንበሳ ክንድ እንደምንታደግ ጽኑ እምነት አለን::

ፈለገ አሥራት የትውልድ ቃል ኪዳናችን ነው!
የዐማራው ሕልውና መጠበቅ ለእትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

Filed in: Amharic News, Politics & Economics, Politics & Openion, Social & Culture, የሞረሽ ወገኔ መግለጫ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.