0

በቆራጥ ትግላችን የዐማራው ኅልውና ይረጋገጣል፤ ማንነቱ ይከበራል !!

ዐርብ ግንቦት ፳፭ ቀን ፪ሺህ፲ዓ.ም. ቅጽ ፮ቁጥር ፲

በቆራጥ ትግላችን የዐማራው ኅልውና ይረጋገጣል፤ ማንነቱ ይከበራል!

 

የዘመናችን የትግሬ ወያኔ ቅኝ ገዢ ቡድን በ1968 ዓ.ም. ባወጣው ማኒፌስቶ ላይ የዐማራው ሕዝብ ቀንድኛ የትግራይ ሕዝብ ጠላት መሆኑን በይፋ አረጋግጧል። ይህም በመሆኑ ዐማራው
መጥፋት አለበት በሚል የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ቅጥረኛ ና ዓላማ አስፈጻሚነቱን ለማረጋግጥ ዕቅድ ነድፏል።

ይህንኑ የጥፋት መልዕክትኛነቱን ዕቅድ ከዳሩ ለማድረስ በጫካ  በነበረበት ጊዜ የጎንደርና የትግራይ ክፍለ ሐገር የተፈጥሮ ድንበራቸው የሆነውን የተከዜ ወንዝ
በመሻገር በተፈጥሮ ሐብት ክምችት የበለፅገውን የቃፍታ፤ ሁመራ፤ የጠገዴና የጠለምት እንዲሁም በሰሜንና ሰሜን ምስራቅ ወሎ ክፍለሐገር ለም መሬት የሆኑትን የራያና ቆቦ፤
አላማጣ፤ እንዳመሆኔ አፍላና ኮረም ወረዳዎች ወደ ትግራይ በመከለል ካርታ ነድፎ ቆይቷል። በ1983 ዓ.ም. በጠመንጃ ሀይል ሥልጣን ላይ እንደወጣም ፤ ከሕዝባችን ፍላጎት ውጭ ሀይልን
ተጠቅሞ በንድፈ ካርታ ያስቀመጣቸውን መሬቶች ወደትግራይ በማጠቃለል በተግባር ተረጉሞታል።

እላይ በተጠቀሱት ሥፍራዎች ቀደምት ነዋሪ የሆኑት የዐማራ ተወላጅ፤ ይህንኑ የመሰፋፋት ቅኝ ገዢነት በግንባር በመቃወምና በመታገል አያሌ ወገኖቻችን የሕይወት መስዋእትነት
ከፈለዋል።  ብዙዎችም ለእስራት እና ለዕንግልት ተዳርገዋል። ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።  ሃብት ንብረታቸውን ተቀመተዋል። የትግራይ ፋሺሽታዊ ሥርዐት በከፍተኛ ደረጃ በታቀደና በተደራጀ
ሁኔታ ላለፉት አርባ ዐመታት የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዐማራው ሕዝብ ላይ እያካሄደ ይገኛል።  የዐማራው ሕዝብ ሕልውና ማንነቱና ሰብአዊ ነጻነቱ ተገፎ፤ በእንደዚህ በሀይል በተያዙ መሬቶቹ
ላይ የትግራይ ፋሺሽታዊ ሥረዐት ባካሄደው ከፈተኛ ወንጀል ባህላቸውን፤ ቋንቋቸውን እና ማንነታቸውን በመጻረር በሀይል አስገደዶ ትግራዊነትን እንዲቀበሉ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ወገኖቻችን በግፍ የተጫነባቸውን ትግራዊነት በመቃወም ቋንቋችን አማርኛ ነው፤ ተውፊታችን፤ ባህል፤ ወግ፤ ልምዳችን ና ሥነ ልቦናዊ ዘይቤአችንም የዐማራ ነው፤ ባለፉት ሺ ዓመታት ዐማራ
ነበርን አሁንም ዐማራ ነን ወደፊትም ዐማራነታችን ይቀጥላል በሚል የዐማራ ማንነት የሕልውና ጥያቄ በማንሳት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።  ይህም አቋማቸው እንደ እሣተ ገሞራ
በመፈንዳትና እንደ ሠደድ እሣት በመቀጣጠል የዐማራ ብሔረተኛነትን በመላ ኢትዮጵያና በውጭ አገር በሚገኙ የዐማራ ተወላጆ መካከል እየጎመራ እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል።
የዐማራ ሕዝብ ለአገሩ፤ሉዓላዊነትና ለዳር ድንበሩ መከበርና መጠበቅ ለብዙ ሺህ ዓመታት ከፍተኛ መስዋእትነት እንዳልከፈለ ሁሉ፤ ዛሬ!  አገር የለህም እየተባለ በአስቦት፤ በአርባ ጉጉ፤
በአሶሳ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒሻንጉልናጉምዝ፤ በጋምቤላ በወለጋ፤በአዲስ አበባ ከተማና አካባቢው እንደ ባየታወር መጤ ተቆጥሮ ተፈናቀለ፤ ሀብት ንበረቱን ተቀማ ፤ተገደለ፤ ታረደ
በአንዳንድ ቦታዎች እስከህይወቱ እየተመተረ ተበላ። በቅርቡም በቤኒሻንጉል ጉምዝ አበጠር ውርቁ የተባለ የ14 ዐመት ልጅ ብልቱን ቆርጠው ዐይኑን አፍርጠው በሞትና በህይወት መካከል
ይገኛል። በዚህ ልጅ ላይ ይህ ሁሉ ግፍና መከራ የደረሰበት ዐማራ በመሆኑ ብቻ ነው።  የወያኔ ፋሺዝምና የአፓርታይድ ሥርዓት በዐማራው ሕዝብ ላይ ብቻ ባካሄደው የዘር ማጥፋትና የዘር
ማጽዳት ጭፍጨፋ እና የወረርሺኝ በሽታ ገበቷል በሚል ሳቢያ በኤች፣ አይቪ የተበከለ ደም ከመድሃኒት ጋር በመቀላቀል በዐማራው ክልል ባካሄደው ክትባት ከ5 ሚሊዮን በላይ
ተወላጆቻችን አልቀዋል።

ይህ ግፍ መከራና ጭፍጨፋ በዐማራው ሕዝብ ላይ ሲፈጸም፤በጣት ከሚቆጠሩት በስተቀር ለኢትዮጵያዊነት ቆመናል፤ ሕብር-ብሄራዊ ነን የሚሉ በሀገር ውስጥና በውጭ የፖለቲካ
ድርጀቶችም ሆኑ ንቅናቄዎች እንዲሁም የሲቭክ ማህበራት አንዳችም ፋይዳ ያለው ተግባር አልፈጸሙም።  ሌላው ቢቀር እንኳን እንደዜጋ ቆጥረው ብሶቱንና እየደረስበት ያለውን አደጋ
ለማሳውቅ አልጣሩም።ጆሮ ዳባ ብለው አልፈውታል። አሁንም እያለፉት ነው ። የዐማራ ተወላጆች ሆነው በወገናቸው ላይ እየደረሰ ያለውን ጭፍጨፋ፤ የዘር ማጽዳት፤
መፈናቀል፤ ሀብትና ንብረት መዘረፍ ወዘተ በዝቅተኛ ደረጃ ለዓለም ህብረተሰብ በማሳወቅ፤ በከፍተኛ ደረጃ ወገኔ ብሎ መመከት ሲገባቸው ዐማራነታቸውን ክደውና ማንነታቸውን
ረስተው፤ ከጸረ ዐማራ ሀይሎች ጋር የተሰለፉ ሁሉ ነገ ከዐማራው ሕዝብና ከታሪክ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ ከወዲሁ ሊገነዘቡት ይገባል።

በቅርቡም የወያኔ ሥርዐት ቁንጮ ሆኖ የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኮሎኔል ዶክተር ዐብይ አህመድ በየቦታው እየሄዱ ለህዝብ ከሚያደረጉት ያፍዝ-ያደንግዝ ዲስኩሮች አንዱ ከእንግዲህ
ወዲህ በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል ደም አይፈስም : መፈናቀል አይኖርም የሚል ነው። ዲስኩሩ ቢነገርም፤ አሁንም በዐማራው ህዝብ ላይ የሚደረሰው ግፍና ሰቆቃ እየቀጠለ ነው።
ይህውም በቤኒሻንጉል ጉምዝ ፤ በምዕራብ ሸዋ ፤ በጅማ ፤ በደቡብ ኢትዮጵያና በተለያዩ ቦታዎች የዐማራ ሕዝብ መፈናቀልና መገደል፤ በነአበጥር ወርቁ ላይ የደረሰው አሰቃቂ ግፍ በቂ ማስረጃ
ነው።  በመሆኑም ዐማራው እንደ ነገድ ቀጣይነቱንና ህልውናውን ለማስጠበቅ መደራጀት መታጠቅ አለበት።

ከ45 እስከ 50 ሚሊዮን የሚገመተው ሰፊው የዐማራ ህዝብ ተደራጀቶ ህልውናውን ያስጠብቃል ፤ በህዝብ ብዛቱ የተነሳ ጠንካራ የኢኮኖሚ፤ የፖለቲካ፤የሶሻልና ወታደራዊ ሐይል
ሆኖ ለሌሎችም ጠለላ ይሆናል። ደህንነታቸውን ያስጠብቃል። የተደራጀ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያለው ሕዝብ ምን ጊዜም ቢሆን አሽናፊ መሆኑን ታሪክ ይመሰክራል። ዐማራውም ይህንኑ
በመራራ ትግሉ ያረጋጋጣል።  በሃያሉ ዐማራ ፊት የሚቆም ሀይል አይኖርምና።  ዐማራው ለማዳን እንደራጅ!

የዐማራው ድርጀት በድቡሽት ላይ የተሰራ አይሆንም !!
ዐማራው ተደራጅቶና ታጥቆ ህልውናውን ያረጋግጣል፤ ማንነቱንም ያስከብራል !!
ፈለገ አሥራት መመሪያችን ነው።

Filed in: Amharic News, News, Politics & Openion, Social & Culture, የሞረሽ ወገኔ መግለጫ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.