0

ሊያጠፋህ አቅዶ የተነሣ ፣አዳኝህ ሊሆን አይችልም!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ረቡዕ ሚያዚያ ፳፬ ቀን ፪ሺህ፲ዓ.ም. ቅጽ ፮ቁጥር ፱

ሊያጠፋህ አቅዶ የተነሣ ፣አዳኝህ ሊሆን አይችልም!

ከታላቁ የዐድዋ ጦርነት ድል ማግሥት ጀምሮ ዐማራው እንዲጠፋ ተፈርዶበት ፣ የተለያዩ የማጥፊያ ዘዴዎች ተጠንተው
በሥራ ላይ መዋል ከጀመሩ 122 ዓመታት ተቆጥረዋል። በነዚህ ዓመታት ቀስ-በቀስና ደረጃ በደረጃ በአገር በቀል ዐማራና
ኢትዮጵያ ጠል በሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች ትብብር፣ ዐማራውን ብቻውን አቁሞ ለማጥፋት የሚያስችሉ ሥራዎች በታቀደ
መልኩ ሢሠሩ ኖረዋል። ዐማራው በሌሎች ነገዶች ብቻ ሳይሆን፣ በራሱ ልጆች ጭምር እንዲገደፍና እንዲጠቃም የረቀቀ
ሤራ ተሠርቷል። ከሤራዎቹ ዋናው ትውልዱን ዐማራው በአመራር ሰጭነት የሌለበት፣ የዐማራው ጠላቶች የሆኑ የባንዳ
ልጆች የሚመሯቸው የግራ ዘመም ርዕዮት ዓለም አራማጅ የሆኑ ድርጅቶች በማደራጀት፣ ኅብረተሰቡን በጨቋኝና ተጨቋኝ
መደቦች፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ ብሔረሰቦች ብሎ በመከፋፈል፣ በሁለቱም ክፍፍሎሽ ተጠቂው ዐማራ የሆነበት አካሄድ
መከተል ዋናው የዐማራ ማጥቂያ ሥልት ሆኖ በሥፋት ተሠራበት።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ የኢትዮጵያዊነት ቋሚና ዘመን ጠገብ የሆኑ ተቋሞች፣ ማለትም የአንድነት ምልክት፣ የሥልጣን ምንጭ
ሆኖ ያገለገለው ዘውዳዊ ሥርዓት፣ የዘውዳዊ ሥርዓቱ ርዕዮተዓለማዊ ክንድና የማኅበረሰቡ ሃይማኖታዊ ተቋም የሆነው
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እንደ አጥፊና ኋላቀርነት ተቆጥረው እንዲወገዙና እንዲጠፉ በስፋት
ተሰበከ። የነዚህ ተቋሞች መጥፋትና መወገዝ ሊያስከትል የሚችለውን የጥፋት ጎዳና በቅጡ ሳይመረምሩ፣ የዐማራው ልጆች፣
የአጥፊዎቹ መሣሪያ በመሆን ነባር፣ ጥንታዊ የፖለቲካና የሃይማኖት ዕሴቶች እንዲወገዙ እና እንዲጠፉ ብዙ ርቀት የተጓዘ
ሥራ ተሠራ።
ዐማራን ነጥሎ ለማጥፋት በተቀነባበረ ሤራ የተሠራው ሥራ፣በ1966 ዓም «ለፍሬ በቃ»። ዘውዳዊ ሥርዓቱና ኦርቶዶክ
ተዋሕዶ ሃይማኖት በመንግሥት እና በሕዝብ አስተዳደር የነበራቸውን ሚና በአዋጅ እንዲጠፉ ሆነ። ሁለቱ ጥንታዊ የአገር
አንድነት፣ የሕዝብ አያያዥ ሰንሰለትና ሙጫ የነበሩት ተቋሞች በአዋጅ ሲፈርሱ፣ ዐማራው ያለተቋም ብቻውን ቀረ። አሁን
የአንድነት ምልክት እና የሥልጣን ምንጭ የነበረው ተቋም ሲወገድ፣ ሰላምን፣ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መቻቻልን ትሰብክ
የነበረችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሚናዋን እንድታጣ ሲደረግ፣ ሕዝቡ እረኛ የሌለው መንጋ ሆነ።

ይህም ዐማራ ጠላታችን ነው ለሚሉ የውጭና የውስጥ ኃይሎች፣ ዐማራውን ነጥሎ ለማጥፋት ምቹ ሁኔታ ፈጠረላቸው።
በመሆኑም፣ ሁሉም ዐማራን አጥፊ በሆነ መንገድ ፣ባሻውና ባፈተተው መንገድ በመጓዝ ዐማራን መስጊድ እንደገባ ውሻ
አዋከበው። የዐማራን የማጥፋት ጉዞው የታቀደ ነበርና፣ ከዐማራ ውጭ የሆኑ ነገዶች ራሳቸውን በማንነታቸው ዙሪያ
አደራጅተው፤ ዐማራውን ከስብስባቸው ገደፉት። ከመግደፍም አልፈው የጥፋት ክንዳቸውን አነሱበት። በዚህም የተነሳ
የትግሬ-ወያኔ ከሽዕቢያ እና ከኦነግ ጋር በመጎዳኘት ዐማራው ካልጠፋ የትግራይ ሕዝብ ማኅበራዊ ሰላም አያገኝም በሚል
ስሌት፣ ዐማራውን እንዲጠፋ አወጀ።
በአዋጁ መሠረትም ዐማራው እስካሁን ባሉት መረጃዎች መሠረት ከ5 ሚሊዮን በላይ ከምድረገጽ እንዲጠፋ ሆነ።ኢትዮጵያ
አገሩና የሞተላት እንዳልሆነች ተቆጥሮ ተዘዋውሮ እንዳይኖር ተደረገ። ተፈናቀለ። እንዳይዋለድና ዘሩን እንዳይተካ በሕዝብ
ዕድገት ቁጥጥር ስም መካን አደረጉት። የኤች አይ ቪ ቫይረስን በመርፌ በማባዛት ሕዝቡን ታማሚና ሟች አደረጉት።
የመማር ዕድሉን ዘጉት። የሕክምና ተቋሞች እንዳይሳፋፉ፣ ያሉትም አስፈላጊ የሆኑ ግብቶች እንዳያገኙ በማድረግ ፣በቀላሉ
ቁጥጥር ሥር ሊውሉ በሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች እንዲጠቃ አደረጉት። በምድራችን ከፍተኛ የሆነ የጤንነት ጠንክ እና
የተንሠራፋ ድህነት የሚገኝበት አካባቢ የዐማራ ክልል የተባለው እንደሆነ የዓለም መገናኛ ብዙኃን አረዱን።

ይህ ሁሉ ሆኖ፣ የዐማራው ምሑር ራሱን በኢትዮጵያዊነት ካባ ሸፍኖ ለወገኖቹ ድምፅ ለመሆን ጊዜ ፈጀበት። በዚህም
ዐማራው ያላናዳች ሕግ ባይ፣ ከመተከል፣ ከቤንሻንጉል፣ ከአሶሳ፣ ከኢሉባቡር፣ ከወለጋ፣ ከአርሲ፣ ከሐረርጌ፣ ከባሌ፣
ከሲዳሞ፣ ከወልቃይት ፤ከጠገዴ፣ ከጠለምት፣ ከራያ ወዘተ አገርህ አይደለም፣ ውጣ ተብሎ በግፍ ተባረረ። ማባረሩ ካለፉት
10 ዓመታት ጀምሮ በመቀጠል እንደባይተዋርና ወራሪ ኃይል ተቆጥሮ ሀብት ንብረቱን በመቀማት የማፈናቀሉ ተግባር ሥራዬ
ተብሎ በታቀደ መንገድ በተከታታይ ተሠራ። ሰሞኑንም ከመተከል በርካታ ዐማሮች በኃይል ተገደው ከቦታቸው ተፈናቅለው
በባሕዳር ከተማ ለችግር መጋለጣቸውን የብዙኃን መገናኛ ተቋሞች እየዘገቡ ነው። ሕዝቡም የድርሱልን ጥሪ እያቀረበ ነው።
የሕዝቡን ጥሪ ሰምተውም እንድረስላቸው የሚሉ ወገኖች የራሳቸውን ጥሪ እያቀረቡ ነው።
ጥሪው ሰሚ ካገኘ መልካም ነው። የጥሪው ዓይነት ግን የሕይዎት ማቆያና የሕመም ማስታገሻ ከመሆን ባሻገር፣ በሽታውን
ከሥሩ የሚነቅል ፈዋሽ መድኃኒት ማግኘት ወደሚቻልበት አቅጣጫ የሚጓዝበትን መንገድ የመከተል ጉዳይ መሆን አለበት።
የዐማራው ችግር በዕለታዊ፣ ያውም ከውኃ ጠብታ በማታልፍ ዕርዳታ የሚፈታ አይደለም። እንዳውም ዕለታዊ ዕርዳታው
ሕዝቡ ችግርን ቀስ በቀስ እንዲለማመድና የአርባ ቀን እድሌ ነው ብሎ፣ ውርደትን ፣መራብ መቸገርን ፣ መሳደድን እና
መዋረድን፣ እጁን አጣጥፎ አምኖ እንዲቀመጥ በር የሚከፍት እንዳይሆን ሊስተዋል ይገባል።
ዐማራው ችግሩን የፈጠሩት ሰዎች፣ ችግሩን ሊፈቱለት እንደማይችሉ ማወቅና መረዳት አለበት። ሊያጠፉት ቆርጠው የተነሱ
አካሎችና ቡድኖች ሊያድኑት ፈጽሞ አይችሉም። የችግሩ ፈጣሪ፣ የመፍትሔው አካል ምንጊዜም ሊሆን አይችልም።
የዐማራው ችግር ሊፈታ የሚችለው በራሱ በዐማራው ነው። የዐቢይ በኃይለማርያም መተካትም የዐማራውን ችግር
አይፈታም። ባለመፍታቱም ይኸውና ዐቢይ ሥልጣን በጨበጠ በ30 ቀን ውስጥ፣ ዐማሮች ከኢሉባቡር፣ ከወለጋ፣
ከቤናሻንጉል፣ ከመተከል ወዘተ በገፍ እየተባረሩ ነው።
የዐማራው ችግር ሥርዓታዊ አወቃቀር ነው። ችግሩ የሚፈታውም ሥርዓቱ ሲወገድና በሌላ ሲተካ ነው። ጫማ ለማምረት
የተዘጋጀ ፋብሪካ፣ ጨርቃጨርቅ ሊያመርት አይችልም። ፋብሪካው ጨርቃጨርቅ እንዲያመርት ከተፈለገ፣ ፋብሪካው
ፈጽሞ መለወጥ አለበት። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ዐማራን ሊያጠፋ የተዋቀረ ሥርዓት ዐማራ አዳኝ ሊሆን አይችልም። ዐማራው
እንዲድን፣ ከተፈለገ፤ ዐማራን እንዲያጠፋ ሆኖ የተደራጀው ትግሬ-ወያኔአዊ የመንግሥትና የሕዝብ አስተዳደር ሥርዓት
ከሥሩ መለወጥ አለበት።
ይህ ለውጥ እንዲመጣ ደግሞ፣የትግሬ-ወያኔ ወዶና ፈቅዶ ያደርገዋል አይባልም። ለውጡ የሚመጣው የመከራው ገፈት
ቀማሽ የሆነው ዐማራው፣ አዕምሮውን ቆጣ፣ ኅሊናውን ሰብሰብ፣ አሞቱን ኮስተር፣ ክንዱን ፈርጠም አድርጎ፣ ለትግሬ-ወያኔ
ሥርዓት አልገዛም!፣ ለማይወክለኝ መንግሥት አልገብርም!፤ በማለት ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ሲጠናክር ብቻ ነው። መብትና
ነጻነት በልመና ከሰማይ እንደመና ከሰማይ የሚወርድ አይደለም። ነፃነት፣ መብትና ዕኩልነት በውድ ዋጋ የሚገኙ ጣፋጭ
ፍሬዎች ናቸው። ከፍሬዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን፣ በቅድሜ መራሩን፣ ከባዱንና አሰልችውን የትግል ጎዳና በድል መወጣት
ይጠይቃል።
ስለሆነም የዐማራ ልጆች፣ ሰዎች ተፈናቀሉ፣ ተዋረዱ፣ ተሰደቡ ወዘተ በማለት የዕለት ዕርዳታ እናቅርብ ከሚለው ጥሪ
በተጓዳኝ፣ ሕዝባችን ራሱን አደራጅቶ ፤በአሳዳጆቹ፣ በአሳሪዎቹ፣ በአፈናቃዮቹ ላይ አሻፈረኝ ብሎ ባለው ዐቅም ሊታገላቸው
እንደሚገባ ከማስገንዘብ ባሻገር፣ የትግሉ ግንባር ቀደም ተዋንያን እንዲሆኑ ማበረታታት ቀዳሚ ተግባራችን አድርገን
ልንይዘው ይገባል። ለቅሶና ዋይታ ይብቃ! አሳደዱን ማለቱ ይቁም! አሳዳጆቻችንም ያላቸው አንድ ሕይዎት ነው። ኑሮን
ከእኛ ከዐማሮቹ ይልቅ ለእነርሱ ታሳሳለች። እነርሱ ሳይፈሩ፣ እኛ የሚቀርብን ምንም ነገር የሌለን ለምን እንፈራለን? መፍራት
ያለባቸው፣ መጡብን ማለት ያለባቸው፣ ከማጀት እስከ አደባባይ በሀብት ላይ ሀብት ያከማቹት እንጂ፣ እኛ መሆን
የለብንም። በመሆኑም፣ ከእንግዲህ መቅረብ ያለባቸው ዜናዎች አንድ ዐማራ አሥር ወያኔ ገደለ፤ ዐማራው ተደራ ጅቶ
ጠላቶቹን ተቋቋመ፤ ሊያጠፈናውና ሊያፈናቅለው የመጣውን ኃይል መክቶ ወደመጣበት ሸኘው የሚሉት መሆን አለባቸው።
እንዲህ ማለት የሚቻለውም ስንደራጅ ስለሆነ፣ በውስጥም በውጭም ያላቻሁ የዐማራ ልጆች፣ በዐማራ ኅልውና ትግል ዙሪያ
እንድትደራጁ ጥሪያችን አናቀርባለን። ለቅሶና ዋይታ ይቁም ! ሊያጠፋህ አቅዶ የተነሣ ፣አዳኝህ ሊሆን አይችልም እና !

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደግ !!

 

 

 

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion, የሞረሽ ወገኔ መግለጫ Tags: ,

Related Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.