0

“ታጥቦ የተሰጣ ልብስ ባየው ቁጥር ባንዲራ እየመሰለኝ ስቸገር ነው የኖርኩት” እንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ያሉት ነው፡፡

ይህ ጽሑፍ፡-
#1ኛ ለአብይያውያኖች (ለአብይ አህመድ ተከታዮች፤አምላኪዎች)
#2ኛ ‘በሞቀበት ለሚፈሉ’ አቋም የለሾች 
#3ኛ የአማራን የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ለሚኮንኑ ነው፡፡ 

የሰው ልጅ ከሌሎች እንሰሳት ከሚለዩት ባህሪያት አንዱ እና ዋናው ’አቋም’ ይባላል፡፡በሌላ አነጋገር አቋም የሌለው እና ’ወደ ነፈሰበት የሚነፍስ’ ሰው ፤ የሰውነትን መስፈርት አያሟላም ማለት ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ት.ህ.ነ.ግ’ን (ወያኔን) በመቃወም እና ’አንድ ኢትዮጵያ/ኢትዮጵያዊነት ብቻ’ በማለት የሚታወቁ ፖለቲከኞች ነን ባዮች፤ለማንም ጫት ቃሚ ዱርዬ ሲያሸረግዱ ባየዋቸው ጊዜ አፈርኩ፡፡አብይ አህመድ በጅማ ዞን፤ጎማ ወረዳ ተወለዶ ያደገ የአጋሮ ጩሉሌ ነው (እኔ ከተወለድኩበት ቦታ 42 ኪ.ሜ ራቅ ብሎ)፡፡አጋሮ የጎማ ወረዳ ዋና ከተማ ናት፡፡አበይ አህመድ በብዙ በሚዘገንኑ ወንጀሎች ጥንብ-ዕርኩሱ የወጣ ሰው ሲሆን ከነ ሙክታር ከድር እና አህመድ አባ ጊሳ ጋር ቡድን ፈጥረው የት.ህ.ነ.ግ’ን አላማ ሲያስፈጽም የነበረ ሰው በመሆኑ ዛሬ ለደረሰበት ቦታ በቅቷል፡፡ (ሙክታር ከድር ማለት በአንድ ወቅት የጅማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የነበረ እና እስከ ኦሮሚያ ክልል (የነሱን ቋንቋ ተውሼ ነው ክልል ያልኩት) ፕሬዝዳንትነት የደረሰ፤ከዛም የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ ነበረ ሰው ነው፡፡አህመድ አባ ጊሳ ደግሞ የጌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ (የእኔ የትውልድ ስፍራ) ከዛም በአንድ ወቅት የጅማ ከተማ ከንቲባ የነበረ ሰው ነው)፡፡ የእነዚህን ማፊያ ቡድን ወንጀሎች ከብዙው በጥቂቱ በሌላ ርእስ ይዤ የምመጣ ስለሚሆን ወደ ዛሬው አጀንዳዬ ልመለስ፤ ስለ ‘ለአብይያውያኖች (የአብይ አህመድ አሸርጋጆች፤ተከታዮች፤አምላኪዎች)’፡፡ለመሆኑ እነዚህ አሸርጋጆች እውነት ኢትዮጵያን ያውቋታልን? ስለ ኢትዮጵያ ታሪክስ ሁለት ገጽ አንብበው ያውቃሉን? የመለስ ዜናዊን ወያኔ እየተቃወሙ የአብይ አህመድን ወያኔ እስከ መደገፍ እና ማምለክ ያበቃቸው ምክኒያት ምን ይሆን? እስኪ በመለስ ዜናዊ ወያኔዓዊ ስረዓት ውስጥ የነበረችውን ኢትዮጵያ እና በአብይ አህመድ ወያኔዓዊ ስረዓት ውስጥ ያለችውን ኢትዮጵያ አይናቸውን ባፈጠጡ፤ጥርሳቸውን ባገጠጡ አንኳር ነጥቦች በትንሹ እናነፃፅር፡-

ኢትዮጵያ በዘመነ መለስ ወያኔዓዊ ስረዓት-

1) አበው በደማቸው ዳር ድንበሯን አስከብረው የሰጡን ቅድስት ኢትዮጵያ ከአካሏ ተቆርሶ ተሸጠ (ኤርትራ)፡፡ 
2) ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ትሆን ዘንድ ቀን ከሌት ተሟግተው Land Locked አርገዋት አረፉ፡፡ 
3) የነፃነት አርማችን የሆነው እና ስንት መስዋትነት የተከፈለበት ባንዲራችን የሰይጣን ምልክት 666 (ኮከብ) ተደርጎበት ተቀየረ፡፡መላው የጥቁር ህዝብ የሚንበረከክለትን ባንዲራችን በሰይጣን ተመሰለ፡፡ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች ከነፃነታቸው ቡሃላ የኢትዮጵያን ባንዲራ እንደ የነፃነት ምሳሌያቸው አርገው በመውሰድ ባድራቸውን ቅርፁን በመቀያየር አረንጓዴ፤ቢጫ፤ቀይ አርገው ይታያሉ፡፡
4) ኢትዮጵያ ለዘጠኝ ተበጣጥሰች፤ብጥስጣሾቹንም ክልል ብለው ጠሯቸው፡፡
5) እንዚህ ዘጠኙ ብጥስጣሾች እያንዳንዳቸው 2 ባንዲራ (1 የክልላቸው፤1 የደርጅታቸው.ለምሳሌ ኦሮሚያ እና ኦ.ህ.ዴ.ድ) ሲኖራቸው ባጠቃላይ 18 ባንዲራ፡፡እዚህ ለይ ባለ ኮከቡ የወያኔዎች ባንዲራ ሲታከልበት 19 ሆነ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ይታያቹ ለ አንድ ቅድስት ለነበረች ሀገር 19 ባንዲራ፡፡ በነገራችን ለይ ብዙ የማይተወቁ ባንዲራዎች እንደሚኖሩ ገምታለውና የባንዲራው ቁጥር ከዚህም እንደሚበልጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡ለዚህ ነው ሰውዬው “በየ መንገድ ዳሩ ታጥቦ የተሰጣ ልብስ ባየው ቁጥር ባንዲራ እየመሰለኝ ስቸገር ነው የኖርኩት” ያለው፡፡እንዳትፈርዱበት፡፡
6) እንዚህ ዘጠኙ ብጥስጣሾች፤እያንዳንዳቸው በፈለጉበት ግዜ እና ባሻቸው ሰዓት እንደ አንድ የምስራቅ አፍቃ ልዑዋላዊ ሀገር መሆን እንደሚችሉ እና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከካርታ ለይ ልትጠፋ እንደምትችል በተፃፈ ህግ ተደንግጓል (ህ/መ አንቀጽ 39)፡፡ለዚህም ኢትዮጵያን ከካርታ ለይ ማጥፊያ ስራ፤የሚፈጀው ግዜ 2 ዓመት እንደሆነም በንዑስ አንቀፁ ተፅፎ ተደንግጓል፡፡
7) ቋንቋን መሰረት ባደረገ መልኩ ለ 9 የወጡት ብጥስጣሾች እርስ በርስ ይጠፋፉ ዘንድ የውሸት ታሪክ እየተፈጠረ የጥላቻ ሀውልቶች ቆሙ (አኖሌ ለይ ፤ጨለንቆ ለይ፤ ወዘተ.)፡፡
8) ቋንቋን እና ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያን ለ 9 ያወጡበት ህጋቸውን ጥሰው ወልቃይት፤ራያ፤ወዘተ.አማራነት ማንነታቸው እና ቋንቋቸው ተደፍጥጦ ይገኛል፡፡

#ኢትዮጵያ በዘመነ አብይ ወያኔዓዊ ስረዓት-

1) አበው በደማቸው ዳር ድንበሯን አስከብረው የሰጡን ቅድስት ኢትዮጵያ ከአካሏ ተቆርሶ እንደተሸጠ ነው (ኤርትራ)፡፡ 
2) ኢትዮጵያ ወደብ አልባ (Land Locked) ናት አሁንም፡፡ 
3) የነፃነት አርማችን የሆነው እና ስንት መስዋትነት የተከፈለበት ባንዲራችን የሰይጣን ምልክት 666 (ኮከብ) ተደርጎበት እንደተቀየረ ነው፡፡መላው የጥቁር ህዝብ የሚንበረከክለት ባንዲራችን በሰይጣን ምልክት እንደተቀየረ/እንደረከሰ ነው፡፡ 
4) ኢትዮጵያ ለዘጠኝ እንደተበጣጥሰች ናት፡፡
5) እንዚህ ዘጠኙ ብጥስጣሾች እያንዳንዳቸው 2 ባንዲራ (1 የክልላቸው፤1 የደርጅታቸው.ለምሳሌ ኦሮሚያ እና ኦ.ህ.ዴ.ድ) ሲኖራቸው ባጠቃላይ 18 ባንዲራ፡፡እዚህ ለይ ባለ ኮከቡ የወያኔዎች ባንዲራ ሲታከልበት 19 ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህም እንዳለ ነው፡፡
6) እንዚህ ዘጠኙ ብጥስጣሾች፤እያንዳንዳቸው በፈለጉበት ግዜ እና ባሻቸው ሰዓት እንደ አንድ የምስራቅ አፍቃ ልዑዋላዊ ሀገር መሆን እንደሚችሉ እና ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ከካርታ ለይ ልትጠፋ እንደምትችል በተፃፈ ህግ ተደንግጓል (ህ/መ አንቀጽ 39)፡፡ለዚህም ኢትዮጵያን ከካርታ ለይ ማጥፊያ ስራ፤የሚፈጀው ግዜ 2 ዓመት እንደሆነም በንዑስ አንቀፁ ተፅፎ ተደንግጓል፡፡ይህን ህግ ነው አሁንም አቢይ እየመራው እና ለተፈፃሚነቱ እተጋ ያለው፡፡
7) ቋንቋን እና ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያን ለ 9 ያወጡበት ህጋቸውን ጥሰው ወልቃይት፤ራያ፤ወዘተ.የአማራነት ማንነታቸው እና ቋንቋቸው እንደተደፈጠጠ ይገኛል፡፡ 
8) ቋንቋን መሰረት ባደረገ መልኩ ለ 9 የወጡት ብጥስጣሾች እርስ በርስ ይጠፋፉ ዘንድ የውሸት ታሪክ እየተፈጠረ የቆሙት የጥላቻ ሀውልቶች (አኖሌ ለይ ፤ጨለንቆ ለይ፤ ወዘተ.) ዕንዳሉ ናቸው፡፡
.
(ከ 8ቱ ነጥቦች ውጭ ሌሎች በርካታ ያለጠቀስኳቸው አንኳር ነጥቦች እንዳሉ ልብ እንድትሉልኝ ፈልጋለው)
.
ስለዚህ የተወሰኑ ጥያቄዎች ልጠይቅ፡-
#1ኛ ለአብይያውያኖች (ለአብይ አህመድ ተከታዮች፤አምላኪዎች)
“አብይ ለኢትዮጵያ ከሰማይ የተላከ መልዐክ ነው” እያላችሁ ስትዘፍኑ የሰነበታችሁበትን ምክኒያት ብታስረዱኝ? 
አብይ ገና ነው ግዜ ያስፈልገዋል፤ቀስ እያለ ስራ ሊሰራ ይችላል የምትሉን ካላችሁ፤ከላይ ለንፅፅር ካቀረብኳቸው ነጥቦች ስንቶቹን እና የትኞቹን መስራት/መቀየር ይችላል? 
(ከላይ ለንፅፅር ያቀረብኳቸውን ነጥቦች ከልባቹ ሁናቹ ካነበባቿቸው ቡሃላ የሚመለስ ነው) “ ስኖር ኢትዮጵያዊ፤ስሞት ኢትዮጵያ ነኝ“ ያላትን ዲስኩር ከቁምነገር እንደማትቆጥሯት ተስፋ አደርጋለው፡፡ምክኒያቱም በዚህ የህዝብ አመጽ ስረዐቱን ሊዉጠው በተቃረበበት ሰዓት ዐይደለም አብይ፤ደብረጽዮን ወይም አባ ጸሀዬም እድሉን ቢያገኙ ይሉታል፡፡

#2ኛ ‘በሞቀበት ለሚፈሉ’ አቋም የለሾች : 
በመጀመሪያ አቋም ማለት ምን ማለት ነው? ምክኒያታዊ አና መሬት የረገጠ የማያወላውል አቋምስ ምትይዙት መቼ ነው? ወደ ነፈሰበት መንፈስ እስከ የት ያደርሳችኋል? አቋም የለለው መሀል ሰፋሪ (noncommittal) ሆናችሁ ከሰው ተራ ወጥታቹ እስከመቼ? በንፋስ ሀይል ከመጓዝ ይልቅ በመመርመር፤ትንሽ ግራ እና ቀኝ በማየት፤በምክኒያት የተደገፈ ሀሳብ ይዛችሁ ብትጓዙ መልካም ነው፡፡ ያለበለዚያ ከመንገዳችን ለይ ዞር በሉልንና ትምህርታችሁን ጨርሱ ካቆማቹበት (ጀምራቹ ከነበረ ማለቴ ነው) ፡፡

#3ኛ #መልዕክት– የአማራን የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ለሚኮንኑ መልእክት ብጤ ናት፡-
በኛ በአማራዎች እምነት በሁኑ ሰዐት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም፡፡ካርታ ለይ ካለሆነ በስተቀር፡፡ከጠፋች 27 አመት ሆኗታል፡፡በአለም ለይ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ ያለው ሀገር የለም፡፡እቺ ታሪካዊ፡የነጻነት አርማ እና የተከበረች ገናናዋ ኢትዮጵያ በዐማራው ቁመት ልክ ተሰፋችዋ ናት (ከዛሬ 50 አመት በፊት የነበረችዋን ኢትዮጵያ ማለቴ ነው)፡፡የመንደር ዱርዬዎች እና የበታችነት ስሜት ተጠቂዎች ከነበረችበት ከፍታ ለይ አውርደው እንደፈጠፈጧት እያያቹ ነው፡፡ኢትዮጵያን ያለ አማራው ማሰብ አየር ማረፊያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው፡፡የአማራው መደራጀት የኢትዮጵያ ትንሳዔ መቅረብ ነው፡፡አማራው ከተደራጀ አይደለም ለራሱ፤ዐይደለም ለኢትዮጵያ፤የአፍሪቃን ፖለቲካ መዘወር ይችላል፡፡አቅሙ አለው፤ችሎታው አለው፤ጥበቡ አለው፡፡ምንም ያጣው ነገር የለም፡፡ስለዚህ 
የምር ኢትዮጵያን የሚወድ ሁሉ ከአማራው የብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ጎን መሰለፍ ብቻ ነው አማራጩ፡፡ሌላ ምንም ምንገድ የለም፡፡

የአማራው የብሔርተኝነት አደረጃጀት ይቀጥላል፤ ይጠናከራል!
አማራ ታሪኩን ያድሳል ፤ ርስቱን ያስመልሳል!
አንድነት ጉልበት ነውና አንድ እንሁን!
#የጅማ#አማራ

 

Filed in: News

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.