0

ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ፦ እንዴት ይረሳል ? መቅደላ ልዩ እትም ቁጥር 11

                                 

                                                     ልዩ ዕትም ፲፩ የካቲት ፲፪ ቀን ፪ ሺ ፲ ዓ.ም      

                    ፍትሕ ለዐማራ ሕዝብ፦ እንዴት ይረሳል?

          እውነት ትደበዝዝ እንደሆነ እንጂ፣ ጭራሽ አትከስምም።   ዘረኞች ከበሮ የደለቁለት የዘር ፓለቲካ ወደ ጥልቁ መቀመቅ
ሊያወርዳቸው ላንቃውን ከፍቷል።  የትግራይ ሽፍቶች ሥልጣናቸውን በያዙበት የጫጉላ ዘመናቸው «ጦርነት እንኳን ማሸነፍ መሥራት እንችላለን»፣   እንዳሉን አንዘነጋውም።    «እንኳን ምድር ላይ ጨረቃ ላይ ብትወጡ አታመልጡንም»  እያሉ
ኢትዮጵያም ሆነች ዓለም እራሷ ከእነሱ ሌላ ጀግና እንዳላፈራች የመጀመሪያዎቹም የመጨረሻዎቹም አልፋና ኦሜጋዎቹ እነሱ
እንደነበሩ መረን በለቀቀ እና ባልተገራ አንደበታቸው ሲያንቧርቁብን እንደነበር አንዘነጋውም።  አሁን አሁን ደግሞ ማጣፊያው እያጠራቸውና እንዳሰቡት ኢትዮጵያን፣ እንዳሻቸው ሊፈነጩባት እንደማይችሉ ሲረዱ፣  ሚሊዮን ብር እያፈሰሱ ከቀጠሯቸው የምዕራባውያንና እስያውያን አማካሪዎቻቸው የሚለግሷቸውን የጊዜ መግዣ ሥልት ተብዬ እየተቀበሉ፣ ባይፈቅዱትም ለማስመሰል ከዚህም ከዚያም ሲራወጡ ይታያሉ። በየቦታው ሕዝባዊ መነሳሳቱ ሲጦዝና ሲንር፣  ውይይት እያሉ ግፊቱን ማለሳለስ ሌት ተቀን ሲዋትቱ ይታያሉ።  ሁኔታው ሰከን ያለ ሲመስላቸው ደግሞ ፣ ሕዝቡን እያፈሱ ወደ ወህኒ ማጋዝ ሥራዬ ብለው ተያይዘውታል።
     በተለያየዩ መገናኛ ብዙኃን መናኘት የያዘው የቅርቡ ጉዳይ ደግሞ፣ ለተፈናቃይ ትግሬዎች ካሣ የመክፈሉ ጉዳይ ነው።  በዐማራና
በኦሮሞ ክልሎች ተብየዎች ሕዝባዊ እንቅስቃሴው አይሎ  በባንዳዎችና የወያኔ ተላላኪዎች ላይ በወሰደው እርምጃ  ለወደመው
ንብረት ካሣ  የእነዚህ አካባቢ መሪዎች ከባጀቶቻቸው ላይ እየቀነሱ እንዲከፍሉ የመታዘዛቸው ጉዳይ እና እነርሱም ትዕዛዙን
ለመፈጸም ያሳዩት ፈቃደኝነት ከማስገረም አልፎ ያሳፍራል። የዚህም ዋናው ምክንያ፣በትረመንግሥቱን ጨምድደው የያዙት
እነሱው (ወያኔዎች) በመሆናቸው  በኢትዮጵያ ጉዳይ ከሰማይ በታች ለሚሆነው ሁሉ ወሳኞቹ እነሱ መሆናቸውንና እነርሱም
ይሉኝታና እሳ ብሎ ነገር ያልፈጠረባቸው መሆኑን ሌላው ማሳያ ነቃሽ ነው።    የየክልሎቹ መሪዎች ትዕዛዙን ሳያንገራግሩ
መቀበላቸው፣ ዘረኞችና ለትግሬ-ወያኔዎች ፍላጎት መሟላት የቆሙ መሆናቸውን ከማሳየቱም አልፎ  የእኔ የሚሉት አቋምም
ሆነ ዓላማ የሌላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የእኛ ጥያቄ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዐማሮች ተገድለውና ተፈናቅለው በሚሊዮን የሚቆጠር ንብረት ባንድ ጀምበር በዘረኞች
ቅስቀሳና ማንአህሎኝነት ማጣታቸው ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ሆኖ ሳለ፣ ስለነሱ ካሣ መጠየቅ ቀርቶ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን
የተቀበለ የብአዴንም ሆነ የሌሎች የኢሕአዴግ እህት ድርጅቶች ተብየዎች አመራሮች አለመኖሩን ስንገነዘብ  ዐማራው እንዲጠፋ
የታወጀበት ነገድ መሆኑን የዐማራው ልጆች ጠንቅቀው ያውቁታል ወይ? የሚለው ነው።   ሕፃናት፣ አረጋውያን ፣ የአካል
ጉዳተኞች ወዘተ ለደረሰባቸው የሥነልቦና እና የአካል ጉዳት ካሳቸው ምን ያህል ይሆን?  ያለዕዳቸው ሕይዎታቸውን ያጡትስ
ዐማሮች ጉዳይ?  በዐማራው ላይ ሆን ተብሎ የተፈጸመውን እልቂቱን አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ወደጎን  ላሉ፣  እራሳቸውንም ለማታለል ለሞከሩና  ለሚመክሩ እነሆ በጨረፍታም ቢሆን ትንሽ አኃዞችን እናስታውሳቸው።

• አቶ ደጀኔ የተባሉ የዐማራው ባለሀብት ለ 40 ዓመታት የደከሙበትና እና ሐረር ውስጥ በጠራራ ፀሃይ የተነጠቁት የደሴ ሆቴል የደረሰባቸውን         ስቃይ እዚህ ላይ ሳናነሳ ማለት ነው።
• በገለምሶ ብቻ የተጨፈጨፉት 10000 ዐማሮች ንብረትስ የት ደረሰ?
• በአርሲ አስተዳደር በአርባ ጉጉ አውራጃ በጀዱ ወረዳ ብቻ የተቃጠሉት 6000 ቤቶችና የተዘረፉት 2500
  የጋማና ቀንድ ከብቶችስ ጉዳይ? በመርቲ ወረዳ በእንደጎቼ ቀበሌ የተቃጠሉት 222 እህል የያዙ ጎተራዎች፤ የተዘረፉ 11115 የቀንድ ከብቶች        እንዲሁም 1077 የተዘረፉት በጎችስ?
• በምሥራቅ አርሲ በአርባጉጉ አውራጃ የተዘረፉት 6203 ከብቶች ፤ የወደሙት 7246 የእህል ክምሮች፤  ከቤት ውስጥ እንዳሉ የተቃጠሉትስ        1200 እንሳሳዎች፤ለቤት መግዣ ተገዝተው የተዘረፉት 12766
  ቆርቆሮዎች በጠቅላላው የወደመው 931782 ቤትና ንብረት ጉዳይ በማን ይሆን የሚዳኘው?መቼስ ይሆን  መልስ የሚያገኘው?
• የጅማው ጉደኛው ጉራፈርዳ፤ የወለጋው፤ የመተከሉ፤ምእራብ ሸዋ፤ በቤን ሻንጉል በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት
  ዐማሮች ባንድ ጀንበር ሲባረሩ የተዘረፉት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረውስ ንብረት ካሣ የሚያገኘውስ መቼ ይሆን?

ይህ የዐማሮች ትልቁ እልቂትና ዝርፊያ ጉዳይ አጣሪ ኮሚሺን ተቋቁሞ የተፈጸመባቸው በደልና ግፍ በዝርዝር ተፈትሾ መቋጫ ካላገኘ፣ መጪው ዘመን ለማንም ብሩኅ እንደማይሆን መታወቅ አለበት። በደልና ግፍ እንዲቆም ኃይል ሕግን እንዳይተካ ድርጅታችን አቋሙን ግልጽ አድርጓል። ፍትሕን ገሸሽ በማድረግ በዐማራው ላይ የተፈፀመው በደል በዝምታ እንዲረሳ ከተሞከረ ግን መዘዙ እሩቅ ሊሆን ይችላልና ለወያኔዎች እና ጋሻጃግሬዎቻቸው ልብ ይስጣቸው።
እነዚህ በወቅቱ አገራችን ውስጥ የተከሰተው የፓለቲካ ቀውስ ያስከተለው ጎርፍ ያመጣቸው የትግራይ መሪ ተብዬዎች ያልገባቸው ነገር ቢኖር፣ ጊዜ የሰጣቸውን አጋጣሚ በመጠቀምና እስከ አፍንጫቸው መታጠቃቸው ልባቸውን አደንድኖት ቢታበዩ፤ ትግራይ ውስጥ ያከማቹት ባሩድ የማያልቅ ቢመስላቸው የጊዜ ጉዳይ እንጂ ፣ሊያጡት እንደሚችሉ አለመረዳታቸው ነው።

ከደርግም የበለጠ ባለመሳሪያ መንግሥት አልነበረም ።  ከዚያም አልፎ የወያኔዎች አባት ሂትለርም ቢሆን ዓለማችንን ጀርመናዊ ሊያደርጋት ያን ሁሉ ጦርና መሳሪያ ይዞ ከዘመተ በኋላ በሌኒን ግራድና ኩርስክ በተባሉ የቀድሞዋ ሶቪዬት ኅብረት ከተሞች ውስጥ አከርካሪው ተሰብሮ፤ ታፍኖ፤ተጨፈላልቆ፤ ነዶና በኖ ግብዓተ መሬቱ ተፈጽሟል።  ካፑት! ሞተ! እንደሚሉት ጀርሞኖች።

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መንገዳቸውን ፈጥነው ያላስተካከሉ ዘረኞች በሰይፍ እንደመጡ በሰይፍ የመጥፋታቸው
ጉዳይ ሳይታለም የተፈታ ነው።

የዐማራ ኅልውና መጠበቅ፣ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Economics, Social & Culture, መቅደላ

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.