0

የዐማራ ኅልውና ለምን? የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) መግለጫ

የዐማራ ኅልውና ለምን? የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (ዐኅኢአድ) መግለጫ

May 1, 2017 More

  ሚያዚያ 22 ቀን 2009 ዓ.ም.  ቅጽ 1፣  ቁጥር 1

የዐማራ ኅልውና ለምን? ( pdf )

እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በወርሃ መጋቢት 2009 ዓ.ም መሠረቱን አገር ቤት ያደረገ፣ “የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት” የተሰኘ የፖለቲካ ድርጅት በኅቡዕ መመሥረቱንና ይህን ተከትሎ የዚህ አዲስ ድርጅት ዓለም አቀፍ ድጋፍ አሰባሳቢ አካልም በውጭ ሀገር መቋቋሙን የብዙሓን መገናኛዎች መግለፃቸው ይታወቃል።

ከስሙ ለመገንዘብ እንደሚቻለው የዐኅኢአድ ተቀዳሚ ዓላማ ከማንም በተለየ ሁኔታ ዘሩ በግፍና በዕቅድ እንዲጠፋ የተፈረደበትን የአማራን ሕዝብ ኅልውና በአስተማማኝ ሁኔታ ማስከበር ይሆናል። በመቀጠልም ድርጅቱ እንደግብ አድርጎ ያስቀመጠው የኢትዮጵያን ሉዐላዊነትና አንድነት ዕውን ማድረግ መሆኑን ገላጭ በሆነው ስሙም ሆነ በፕሮግራሙ ላይ በማያሻማ ሁኔታ አንፀባርቋል።

ይሁን እንጂ፣ አንዳንድ ወገኖች፣ የተመሠረተው አዲስ የፖለቲካ ድርጅት ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል ከሆነ ለምን ማኅበራዊ መሠረቱን በዐማራ ነገድ ዙሪያ ላይ አደረገ የሚል ጥያቄ ሊያነሱ እንደሚችሉ ይታመናል። በሌላ አገላለጽ ለኢትዮጵያ አንድነት የሚታገል ከሆነ ለምን ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን አያሰባስብም? የሚልም ጥያቄ ሊሰነዘር እንደሚችል ይጠበቃል። እርግጥ ነው ጥያቄው መሠረታዊና ተገቢ ጥያቄ ነው።

ለዚህ ተገቢ ጥያቄ ተገቢ መልስ ያሻዋል። ዐማራው በዐማራነቱ እንዲደራጅ ግድ ያደረጉ መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ። እነሱም አንዱና ዋናው ዐብይ ጉዳይ የዐማራው ኅልውና ከማንም በተለየ ሁኔታ እጅግ አደጋ ላይ በመሆኑ ነው። የዐማራው ነገድ ለእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ሉዐላዊንት ቀናኢ በመሆኑና ባለው ጽኑዕ የሀገር ፍቅር ምክንያት በማንነቱ ተነጥሎ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በወያኔና ተከታዮቹ እጅግ በጣም በከፋ ሁኔታ እየተፈጸመበት ነው። “ራስ ሳይጠና ጉተና” እንደሚባለው፣ አማራው አደጋ ላይ ያለውን የራሱን ኅልውና በአስተማማኝ ሁኔታ ሳያስጠብቅ ኢትዮጵያን አድናለሁ ቢል ከዕውንታው የራቀ አጉል ምኞት ነው የሚሆንብት። በመሆኑም ይህ ኅልውናው አደጋ ውስጥ ያለው የዐማራ ነገድ ከምንም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥቶ የራሱን ኅልውና ማስጠበቅ ግድ ብሎታል።

በእርግጥ ለሀገር አንድነት ሲል በአርቆ አስትዋይነትና በሆደ – ሰፊነት ቻለው እንጅ አማራውን ለማጥፋትና ለማግለል የተጀመረው ሴራ አሁን ሳይሆን ቀደም ብሎ ነው።  የጎሳ ፖለቲካ ሰይፍ በግራ ዘመሙ የፖለቲካ ርዕዮት ተሸፍኖ በኢትዮጵያ ወጣትና ቀለም ቀመስ ትውልድ አዕምሮ ሁነኛ ቦታ ከያዘ ጊዜ ጀምሮ አማራው ሆን ተብሎ በተከታታይ በገዥ መደብነት፣ በነፍጠኝነት፣ በጨቋኝ ብሔርነት፣ ወዘተ ተፈርጆ በቡድንና በተናጠል ከንብረት ነጠቃ እስከ ጅምላ ግድያ የተፈጸመበት መሆኑ ያደባባይ ሚስጢር መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል።

ከሁሉም በላይ ደግሞ ዘረኛው  የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን “በጎሳ ፖለቲካ ፕሮግራሙ” ዐማራን ቀንደኛ የትግራይ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ስሎ፣ “ዐማራ ሳይጠፋ ትግራይ ማኅበራዊ ሰላም ልታገኝ አትችልም” በማለት፣ ትውልዱን/ተወላጁን በፀረ-ዐማራነት አደራጅቶ ባለፉት 26 የአገዛዙ ዓመታት ብቻ ከ5 ሚሊዮን በላይ ዐማራ ከምድረ – ገጽ ሲያጠፋ፣ በኅብረብሔራዊም ሆነ፣ በብሔር ከተደራጁ ድርጅቶች ውስጥ ይህንን ጥፋት በአርምሞ ከማየት በስተቀር ዐማራው ተደራጅቶ መብቱን እንዲያስከብር ያደረጉት ጥረት አልታየም። አንዳንዶቹማ ይባስ ብለው የጥፋቱ ተባባሪ በመሆን ዐማራውን በተገኘበት እንዲገደል፣ እንዲሳደድ፣ ንብረቱ እንዲነጠቅ አድርገዋል።

በዚህም የተነሳ ዐማራው የሚያደርገው ትግል እንደሰው የመቆጠር፣ እንደሰው በአገር ላይ የመኖር፣ እንደሰው ልጅ ወልዶ የመሳምና ዘር የመተካት፣ እንደ ክፉ አውሬ እየታደኑ ለዕርድ ያለመቅረብ እና በአጠቃላይ መሠረታዊ የሆነ የማንነትና የኅልውናው ትግል ነው። የኅልውና ትግል ደግሞ ፋታ የማይሰጠውና ይዋል ይደር የማይባል ትግል ነው።  በመሆኑም ከማንም ተነጥሎ በዕቅድ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በተቀነባበረ ሁኔታ እየተፈጸመበት ያለው የአማራ ነገድ ራሱን ከመጥፋት ለመከላከል ወይም ኅልውናውን ለማትረፍ የሚያደርገውን ትግል ተፈጥሮአዊውም ሆነ ሰው ሠራሹ ሕግ ይደግፈዋል። እንኳን የሰው ልጅ፣ እንሣትና እፅዋትም ቢሆኑ ሕይዎታቸው አደጋ ላይ ሲህን ራሳቸውን የሚከላከሉብት የራሳቸው የሆነ ዘዴና ስልት አላቸውና!

ለዐማራው መደራጀት ሁለተኛው ምክንያት፣ በዐማራው ነገድ ላይ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበትና እየተፈጸመበት ያለው ዐማራ በመሆኑ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ በፅኑዕ ስለሚያምንና የኢትዮጵያን ሉዐላዊንት አላስደፍርም በማለቱ ጭምር እንጅ። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ደግሞ  ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለውንና ለኢትዮጵያ ሉዐላዊንት በግንባር ቀደምነት ዘብ የቆመውን ወገን ቀድሞ ማጥፋት የፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ዋና ዓላማ ነው። ስልዚህ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊትን ለመታደግ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ከልብ የሚያምነው ዐማራው ተደራጅቶ ራሱን በአስተማማኝ ሁኔታ ካዳነ በኋላ፣ ከሌሎች ለኢትዮጵያ ቅን ከሚያስቡ ነገዶችም ሆነ ድርጀቶች ጋር በመሆን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከጥፋት ለመታደግ ብቸኛውና አስተማማኙ መንገድ ተደራጅቶና ጠንክሮ መገኝት በመሆኑ ነው።

ስልዚህ ስም ተግባርን ይገልጻል እንዲሉ፣ የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት የአጭር ጊዜ ግቡ ዐማራውን ከጥፋት ማዳን፣ ማንነቱንና ኅልውናውን ማስጠበቅ ሲሆን፣ ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር በአንድ ላይ ሆኖ  የኢትዮጵያን አንድነት ማስቀጠልን እንደመድረሻ ግቡ ያደረገ ድርጅት ነው።  የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት በዐማራው ወጣት፣ ጎልማሳ፣ ሽማግሌ፣ ሴት ወንድ፣ ተማሪ፣ አስተማሪ፣ ገበሬ ነጋዴ የታቀፈና ማኅበራዊ መሠረቱ የሠፋ ድርጅት ነው።

የዐማራ ኅልውና ለኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ዓላማ ግቡን ይመታ ዘንድ፣ የጥቃቱ ሰላባ የሆነው ሁሉም የዐማራ ልጅ የሚችለውን ድጋፍ እንዲቸረው ጥሪ ቀርቦለታል። ይህንን በነገዳችን ላይ የተጋረጠውን አስከፊ አደጋ ለማስወገድ ከእያንዳንዱ የአማራ ልጅ ቀና ምላሽ የጠበቃል። ሆኖም ግን ድጋፍ ማድረግ ባንችል እንኳን እንቅፋት ከመሆንና የባንዳነት ተግባር ላለመፈጸም ለራሳችን ቃል መግባት ይኖርብናል። ይህ ካልሆነ፣ የዐማራው ኅልውና ታጋዮች የዐማራውን ኅልውና ለማረጋገጥ በሚያደርጉት የሞት ሽረት ግብግብ ሂደት ውስጥ፣ የመጀመሪያ የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት ከመንገዳቸው ላይ ቆሞ ለእንቅስቃሴአቸው መሰናክል በሆነ በማንኛውም ሰው ላይ መሆኑን እያንዳንዱ ኅሊናውን ሸጦ የአማራው ዋና ጠላት የሆነውን ወያኔን የሚያገለግል አማራ ሁሉ ከወዲሁ ሊያውቀው ይገባል። አማራውን በዋና ጠላትነት ፈርጆ እያጠፋው ካለው ወያኔ ጋር ወግነው ዐማራን በሚያጠቁና በሚያስጠቁ ባንዳዎች ላይ የዐማራው ኅልውና ኃይሎች የማያዳግም እርምጃ እየወሰዱ ወደፊት የሚገሠግሡ መሆኑን ጎቤ መልኬን በማስገደል በተባበረው እና በሰሜን ሸዋ ሁለት የዐማራ ታጋዮችን ባስገደሉ ከሃዲዎች ላይ የወሰዱት አፋጣኝ እርምጃ ትምህርት ሰጪ ነውና ልብ ያለው ልብ ይበል።

የዐማራው ኅልውና መጠበቅ፣ ለኢትዮጵያ አንድነት መጠበቅ ዋስትና ነው!!

E-mail: aseuoirp@gmail.com

 

Filed in: News

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.