0

በሲያትል የጎንደር ማህበር የንብረት ውዝግብ የፍርድ ቤት ውሳኔ አገኘ

በሲያትል የጎንደር ማህበር የንብረት ውዝግብ የፍርድ ቤት ውሳኔ አገኘ

በአዱኛ፡አ. ዉቤ

 የህዝብ ንብረት ለህዝብ እንዲመለስ ተወስኗል

ለሦሥት ዓመታት ያህል በሕግ ተይዞ የነበረው በስያትል ከተማ የጎንደር መረዳጃ ማህበር እና የጎንደር የንግድ ማሕበር በውስጣዊ አሰራር ችግር በተነሳው አለመግባባት ግጭት፣ ችግሩ ለፍ/ቤት ቀርቦ ውሳኔ አግኝቷል።

ወገኖቸ፥ ይህን የፍርድ ውሳኔ በግልጽ የምናቀርብበት ምክንያት በፍርዱ የረኩትን ወይም የተከፉትን ለሌላ ትችት ለማበርከት ሳይሆን ከሕብረተስብ ህሊናና ከሕጋዊ ሥራ በመራቅ በማን አለብኝነት የማህበረሰብን ንብረት ለግል ማድረግ ውጤቱ በፍርድ የሚቀለበስ ቅጣትም የሚያስከትል እንደሆነ ለማሳያ ነው። ስለዚህም የተከላካይ ስሞችን ከመግለጽ ተቆጥበን ጉዳዩን በግልጽ የማወቅ መብት ላለው ማህበረሰብ ይሄው ብለናል።

ጥሩ ሥራንና የፍርድን/ ፍትሕን የመጨረሻ ውጤት አክብረን እንድናይና እንድንገነዘብ ይህ ጉዳይ ትምህርት ይሆናል። ይኽ አይነቱ ሁኔታ በማንም ኢትዮጵያኖች ሕብረተሰብ የሚደገም እንዳይሆን ለማሳሰብም ነው። ማንንም ዝቅ ለማድረግ ሳይሆን በፍርድ ቤት የሚገኘው ዶሴ የሚያመለክተው ጉዳይ ስለሆነ፣ አሁንም ዓላማችን ሕብረተሰባችን መሳቂያ እንዳይሆንና የብዙ ንጹሕና ሰላማዊ ወገን ስም እንዳይበከል እንዲህ ያለውን የዝርፊያ ስራ ማውገዝ እንደሚገባንና ከዚህ በተሻለ ጠባይና ባህሪ እንድንገኝ ለማሳሰብ ነው። በዚህ ከተማ ታላቅ ስራ ለወገኖቻቸው ሰርተውና መልካም ቅርስ እንዳቅማቸው ለተከታዩ ትውልድ ያሳለፉ ወገኖች ነበሩ፤ አሁንም አሉ። የነሱን አርአያና ፈለግ መከተል ይኖርብናል። ከመካከላችን አንዳንድ አስነዋሪ የሆነ ሥራ የሰሩም አሉ። እነሱም ሲያፍሩ ሲወድቁና ሲሸማቀቁ ለማየት በቅተናል።

 የችግሩ መነሻ

የጎንደር ዕድርና መረዳጃ ማሕበር የተቋቋመው በ1994 ዓ/ም ሲሆን፣ አመሰራረቱም እንደ በጎ አድራጎት ድርጅት ነበር። ይኽም ማለት፣ ድርጅቱ በማናቸውም መልክ የሚያገኘውን መዋጮ ለተቋቋመለት አላማ ያውለዋል ተብሎ ነበር። ከዚህ ውጭ የሚሆን የሚያስጠይቅና  ሕጋዊ  እርምጃን የሚያስወስድ ይሆናል። ይኽም ጥያቄ በማንም ሰው ሊነሳ ይችላል።  በ1999 ዓ/ም ሁለተኛውና ለትርፍ/ለጥቅም የሚሰራ የጎንር ንግድ ማሕበር ተብሎ ተቋቋመ። ለንግድ ተብሎ የተመሰረተው ሥልሳ የሚሆኑ  አባሎች  ነበሩት።

የንግዱ ድርጅቱ ክፍል በ2000 ዓ/ም $101,620.00 በማዋጣት አንድ ቤት ገዛ። ድርጅቱ በቂ ዋስትና ስለሌለው፣ አምስት  ብቁ ክረዲት ያላቸው ሰዎች በመፈረም ንብረቱ ተገዛ።ከተዋጣው ገንዘብ ላይ ለቤቱ ግዥ የመጀመሪያ ክፍያ የዋለው $51,706.57 ብቻ እንደነበር የባንክ መዝገቡ ያሳያል። የግምጃ ቤት ሂሳብ ማሳየት የነበረበት ቀሪውን $49,913.43 ሲሆን፣ ይኽ ገንዘብ ባንክ የሌለና የት እንደደረሰ አልታወቀም። ይሕ ጉዳዩ ገና በሕግ ተይዞ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የአምስቱ ሰዎች ኃላፊነት በሸፍጥ ተነስቶ በሁለት ሰዎች ተጠቃሎ፣ የንግዱ ድርጅቱ በአንድ ሰው ሙሉ ተቆጣጣሪነት እየተካሄደ ተገኘ። ይህንንም ቤት ለሕዝብ ሳያሳውቁ በምስጢር አሁን በቅርብ በ2016 ሸጠውት ተገኝቷል። ቤቱ በ 2000 ዓ/ም የተገዛው $322,000 ዶላር ሲሆን፤ አሁን በ2016 የተሸጠው $1,035,000 ዶላር ነው። የጎንደር ዕድርና መረዳጃ ማሕበሩም ሒሳብ እንዲሁ በአሁን ጊዜ የሚያሳየው $14.10 ብቻ ነው (ከታች በፍርድ ሂደቱ እንመለስበታለን)። ወገኖቻችን የተፈጸመው ግፍና ጥቃት ቀላል አይደለም። እንኳን በአሜሪካ በማንኛውም ሀገር የማይደረግ ዘረፋ ተፈጽሟል።

 ሕጋዊ ሂደት

ይኽን ሁኔታ ለማስተካከል ሰፊ ጥረት ቢደረግም፣ (በአቡኑና/ በአገር ሽማግሌ) ቤቱን በሰላም እንዲመልሱ ተጠይቀው ውጤት አልባ ሆኖ ስለቀረ የድርጅቱ ባለቤቶች/ ከሣሾች ቤቱን በግላቸው ባደረጉት ሁለት ሰወች ላይ (ከነባለቤቶቻቸው) የሕግ ክስ በፍርድ ቤት ከፈቱ። ይኼም ክሥ የተመሰረተበት ምክንያት

፩ኛ. ሁለቱ ግለሰቦች በራሳቸው ሥም ያዛወሩትን የሕዝቡን ንብረት ለንግድ ማሕበሩ አንመልስም በማለታቸው

፪ኛ. ሕዝብ የመረጣቸውን የሥራ አመራሮች የቤቱን ቁልፍ ቀይረው በገዛ ቤታቸው አትገቡም በማለታቸው

፫ኛ. አንዱን ብልህና ቅን የሆኑትን የማህበሩን አባል ያለአግባብ ከሕግ ውጭ በደብዳቤ በማገዳቸው ነው።

ክሱ ተጀምሮ ሳለ፤ ዳኛው ለመረዳጃው ማህበርና ለአባሎቹ ሲባል ዕርቅ እንዲደረግ አስታራቂ አዘዙ። ከስምንት ሰዓት ውይይት በኋላ ሳይሳካ ስለቀረ ክርክሩ ቀጠለ። ክርክሩ እየተካሄደ ሳለ በህግ አግባብ ያልሆኑ ተግባሮች በዋናው ተከላካይ ሰውና ሌሎች ሁለት አጋሮቹ ሆነው፣ ፍርዱን ለማጨናገፈ ንብሩቱን ለመሸጥ ተዋውለው ተገኘ። በተጨማሪም፣ የድርጅቱ ባንክ ሂሳብ ያለአግባብ ተዘግቶ ተገኘ። ይህ ድርጊት አስቀድሞ ፍ/ቤቱ ያገደውን ትዕዛዝ የሚጥስ ነበር።

ሶስቱ ተከላካይ/ተከሳሾች የሕዝቡን ንብረት ለማስመለስ የሚታገሉትን ከሳሾች የድርጅቱ አባሎች እንዳልሆኑና እንዲወገዱ የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ጠየቁ። ፍ/ቤቱ ሳይቀበላቸው ቀረ።

ፍ/ቤቱ እነዚህ ግለሰቦች፣ የንግዱ ድርጅት አባሎቹ የሆነውን ንብረት ለግላቸው ጥቅም ከማዋላቸውም በላይ ወደ ግል ስማቸው በማዞር የራሳቸው ንብረት ማድረጋቸው ሕጉን የሚሰብር ስለሆነ፣ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከሳሾች በሕግ ተገደው በ 03/26/2015 ቤቱን ለሕዝቡ/ ለንግድ ማህበሩ አስረከቡ/ መለሱ። እንደገና በፍርድ ቤቱ ትዕዛዙ መሰረት ለጊዜው የንግድ ማሕበሩን ንብረት ለመከላከል ከሣሾቹ ባስመደቡት የፍርድ ቤቱ ተወካይ ቤቱን ተረክበውት ይገኛሉ።

በዚህ ክስ ምክንያት የተረዳነው እጅግ አሳፋሪ ችሎታን ያንጸባረቁም ነበሩ። አንዱ ድርጅቱን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮት የነበረው ግለሰብ ቃል እንዲሰጥ ተጠይቆ፣ “ለምን የገንዘብ አያያዝህና የዓመቱ አወራረድ እጅግ ቅጥ ያጣና ፈጽሞ የገንዘብ አያያዝ ሥነስርዓት የጎደለው ሆነ?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ የሰጠው መልስ፣ “እኛ አሰራራችን እንደ አፍሪካ እስታይል ነው፤ የሂሳብ አያያዝ አንችልም፣ በዕምነት ነው የምንሰራው” በማለት መልሷል።

ሌላው ተጠያቂ ግለሰብ ደግሞ “ለምን ለሕዝብ ሳታስታውቁ የሕዝብ ንብረት በሚስጢር ልትሸጡ ወሰናችሁ?” ተብሎ ሲጠየቅ በድንጋጤ የሰጠው መልስ ከተሸጠ በኋላ “በመጨረሻዋ ቀን እንነግራቸዋለን ብለን ነው” ሲል ገልጿል።

የጎንደር ዕድርና መረዳጃ ማሕበር የበጎ አድራጎት ድርጅት የተቋቋመው ከ1997 በፊት የነበሩት አመራሮች ሲቀየሩ ለተተኪው ተመራጭ ያስረከቡት ሂሳብ ከ$25,000 ብር በላይ ነበር ። ይሕ በሆነ ከ18 ዐመት በኃላ በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መሰረት ዕድር ማሕበሩ የባንክ መዝገቡን እንዲያቀርብ ተጠይቆ ሲታይ ባንክ ሰነዱ ከወጭ ቀሪ የሚያሳየው የገንዘብ ልክ $14.10 ብቻ ነበር። እንዲህ ያለ ተጠያቂነት የጎደልው የሚያሳዝን ዋልጌነት በግልጽ ተገንዝበናል።

መጀመሪያ ለመግለጽ እንደሞከርነው ሕብረተሰባችን በዚህ በበለጸገው ሀገር ሲኖር በምናደርገው በሕግም ሆነ በባህል አንጻር የበለጠ ሆኖ እንዲገኝ እንጂ እጅግ በሚያስወቅስና ምግባርን የሚያንቋሽሽ ተግባር እንዳንሠራ ለማድረግና ምግባራችንን ከፍ ለማድረግ እንድንጥር ለማሳሰብ ነው። ድርጅቶች በዚህ ሀገር እጅግ የረቀቀ የአሰራር ጥበብ ይሻሉ። ስለዚህ ለዚህ ስራ የምንመርጣቸው አመኔታ የሚጣልባቸውና ብቃት ያላቸውን በሐላፊነት ማስቀመጥ ጠቃሚ ነው።

 የፍርድ ቤት ውሎና ውሣኔ

ጥቅምት 7/ቀን 2016 ዓም በዋለው የከሳሽና የተከሳሽ ክርክር በዕለቱ ለፍርድ የተቀመጡት ዳኛ ውሳኔ ፍርድ አሳልፈዋል። ክሡን በተሳካ ሁኔታ ከግብ ላደረሱትና አስረግጠው ለረቱት ከሣሾች(ባለቤቶች) ለጠበቃ ያወጡት ገንዘብና ቀሪ ሂሳቡን ጨምሮ ሙሉ ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ወስነዋል።

ፍ/ቤት ሰውን ያጸዳል። ድርጅትን ይጠብቃል። ሕብረተስብ እንዲያድግና በሰላም እንዲኖር ውሳኔና ትዕዛዝ ይሰጣል። በፍ/ቤቱ ውሣኔ መስረት አሁን የጎንደር ዕድርና የንግድ ድርጅቱ አባሎች ሕግን አውቀው በጋራ እንዲበለጽጉና እንዲያድጉ በሰላምም እንዲኖሩ ተደርጓል።

ይህ በቀላሉ አልተፈጸመም። እጅግ የሚያኮሩ ተቆርቋሪ ወገኖች ለራሳቸው ሳይሆን፣ ለመላው ወገናቸው ጥቅም በመቆም፣ የማንንም አፍና ወቀሳ ሳይፈሩ በራሳቸውና በሌሎች እንደነሱ ቆራጥ ልብና መንፈስ ባላቸው ድጋፍ የሚያኮራ  ስራ ሠርተዋል። መከበርና መመስገን ይገባቸዋል። አርእያው እንዲሰማና እንዲታወቅ ሌላውም ኢትዮጵያዊ ወገናችን ከዚሕ ትምሕርት እንዲያገኝ እንመኛለን።

ንብረቱን በሕግ ለሕዝቡ ያስመለሱ መንፈሠ ጠንካራ የጎንደር/ በጌምድር ተወላጆችና የድርጅቱ አባሎች የሚከተሉት ናቸው።

፩ኛ/ አቶ አዱኛ  ዉቤ፤                                ፭ኛ/ አቶ አሰፋ ቢያድግልኝ

፪ኛ/ አጋፋሪ ፀጋው አምባው፥                         ፮ኛ/ አቶ ታከለ አማረ

፫ኛ/ አቶ ፈንታሁን አጋዚ                              ፯ኛ/ አቶ መርዕድ አየለ

፬ኛ/ አቶ አበበ ምትኩ                                 ፰ኛ/ እራሱ የንግ

 

 

Filed in: News

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.
%d bloggers like this: