0

ብአዲንና ኦሕዲድ በወያኔ የሚጋለቡ ሰጋር በቅሎዎች ናቸው፣ ከመሰረት ቀለመወርቅ

ብአዲንና ኦሕዲድ በወያኔ የሚጋለቡ ሰጋር በቅሎዎች ናቸው
መሰረት ቀለመወርቅ
ወቅቱ የአማራውና የኦሮሞው ሕዝብ ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀበት በወያኔ አልሞ ተኳሽ ትግሬዎች ግድያ ከፍተኛ የዘር
ማጥፋት ወንጀል እየተፈፀመ የምንገኝበት ዘመነ-ጥፋትና ዘመነ-ምፅት ላይ ነን። ይኸው ነፍሰገዳይ ቡድን ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ
በአገሩ ተከብሮ እንዳይኖር ለረጅም ዘመናት ከደደቢት እስከ ቤተመንግስት ያሴረው ተንኮል ተዘርዝሮ አያልቅም። ወያኔ
የአማራውንና የኦሮሞውን ማሕበረሰብ አጥፍቶ ለመጥፋት ወስኖ ሰላማዊ ነዋሪውን ሕዝባችን በሚኖርበት ትውልድ ቦታው
ነፍሰ-በላው አጋዚ የተባለውን የትግሬ ሚሊሻ በማሰማራት ወረራ ፈፅሞ ወታደራዊ ቀጠና አድርጎታል።
አሁን የሚያደርገውን ሰይጣናዊ ድርጊት በመፈፀም ሕዝቡን ለማጥፋትና ለማፅዳት የደፈረው ለዘመቻው መሳካት ከአገር
ውስጥም ሆነ ከአለም አቀፍ አጋሮቹ ጋር የጋራ ግንባር ፈጥሮ ነው። አገሩንና ሕዝቡን አጥፍቶ ሐብትና ንብረቱን ዘርፎ የጥቂት
ምርጥ ትግሬዎች መንደላቀቂያና በቅጥረኝነት ላሰለፉት ቅኝ ገዠዎች እጅ መንሻ ለማድረግ ከተጠቀመባቸው ሴራዎች ውስጥ
አንዱ ከተጎጅው አማራና ኦሮሞ ማህበረሰብ መካከል መልምሎና አሰልጥኖ እንደፈለገ የሚጋልባቸው ሰጋር በቅሎዎችን
ለመፍጠር መቻሉ ነው። ከነዚህ ሰጋር በቅሎዎቹ ውስጥ ዋንኛዎቹ የመንግስትነት ስልጣን ቀርቶ የሚገዙት ሕዝብና መሬት
የሌላቸው ብአዲንና ኦሕዲድ የተባሉት አሻንጉሊቶቹ ይገኙበታል። ነፍሰ-በላው ወያኔ ለሚጋልባቸው ሰጋር በቅሎዎቹ የስራ
አፈፃፀም ያመች ዘንድ የረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ የካድሬ ስልጠናዎችን በመስጠት ያሰልፋቸዋል።
ከካድሬው ስልጠና በፊት ምልመለው ቀዳሚ በመሆኑ ጥብቅ ጥንቃቄ ተደርጎበት የካድሬ ምልመላው ይከናዎናል። በምልመላው
ወቅት ከሚጠቀምባቸው መመዘኛዎች ውስጥ፦
1 ኛ. አማራውና ኦሮሞው በተፈጠሩበት አካባቢ አብሮ የኖረ በአባቱ ወይም በእናቱ የትግሬ ዘር ያለው
እንዲሆን ይፈለጋል።
2 ኛ. አማራ ወይም ኦሮሞ ሆኖ አስተሳሰቡ ካለበት ማህበረሰብ እጅግ የወረደ ደካማና በቀላሉ የሰጡትን
የሚቀበል በሆዱ ብቻ የሚገዛ መሆን ይሮርበታል።
3 ኛ. በሚኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ከፍተኛ ቁርሾ ኖሮት የተፈጠረበትን ማህበረሰብ አማራውን ወይም
ኦሮሞውን የሚጠላ መሆኑ ይፈለጋል።
4 ኛ. እምነትን ምክንያት በማድረግ በእምነት ተቋማት ውስጥ ገብቶ የካድሬነት ስራ መስራት የሚችል መሆኑ
ይረጋገጣል።
ከምልመላው መጠናቀቅ በኋላ ስልጠና በመሆኑ ሁሉም ካድሬ የብአዲንና የኦሕዲድ የፖለቲካ ድርጅቶች አባል ተብለው
ይሰየማሉ። ነገር ግን ብአዲንም ሆነ ኦህዲድ የነሱ የሆነና ለተፈጠሩበት ማህበረሰብ በሚጠቅም መልኩ የተቀረፀ የፖለቲካ
አጀንዳ የላቸውም። እንዲያውም የተጠቀሱት ድርጅቶች መስራቾች ናቸው የተባሉት ሳይቀር የወያኔው የምልመላ መመዘኛዎች
እንደተጠበቀ ሆኖ ተመልምለው የመሰረቱት ጀማሪዎች የግለሰብ ነፃነት ያልነበራቸው ወታደራዊ ምርኮኞች እንደሆኑና የአማራ
ወይም የኦሮሞ ተወላጆች እንዳልሆኑ ይታወቃል።………..read in pdf ብአዲንና ኦሕዲድ በወያኔ የሚጋለቡ ሰጋር በቅሎዎች ናቸው መሰረት ቀለመወርቅ

Filed in: Amharic News, eMedia, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.