0

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፡- አማራ የሌለው የት ሄዶ ነው? ከምስጋነው አንዱአለም (መለክ ሐራ)

ከምስጋነው አንዱአለም (መለክ ሐራ)
(ከ17 ወራት በፊት ይሄንን ጽፌላቸው ነበር፡፡ በወቅቱ ዘሀበሻ ላይ ወጥቶ ነበር፡፡ ከዚህ በታች አስቀምጨዋለሁ፡፡ እስኪ ደግሞ ከሰሞኑ ጊዜ ሲገኝ ትንሽ እመርmesganaw-andualemቅላቸዋለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፡- አማራ የሌለው የት ሄዶ ነው?
እኔ ልናገረዎ የማይገባ ብላቴና ነኝ፡፡ በብዙ ነገር አድናቂዎ እና ብዙዎችን ጽሁፎችዎን ያነበብኩ ነኝ፡፡ አሁን ለያዝኩት ማንነትም የእርስዎ አስተዋጽኦ አለበት፡፡ ይሁንና በአማራ ጉዳይ ላይ ባለዎት አቋም ላይ ከረር ያለ ልዩነት አለኝ፡፡ ሰው መሆን አቅቶኝ እና የጎሰኝነት ስሜት አጥቅቶኝ ሳይሆን ይህ የለም እየተባለ መከራ የሚወርድበት ህዝብ ረፍት ስላጣና ዜግነቱን ስለተነጠቀ እንዲሁም አለሁልህ የሚለው ስላጣ አቅሜ በፈቀደው ሁሉ ልሟገትለት ራሴን ስላዘጋጀሁ እርስዎንም አሻቅቤ ለመናገር ተገድጃለሁ፡፡ ስለራሴ ስል የእርስዎ እምነትና ፍልስፍና ነው ያለኝ፡፡ ስለህዝቤ ስል ግን ከዚህ ሸሽቻለሁ፡፡ እንዳይቀየሙኝ፡፡
የክህደት ቁልቁልት በተባለው መጽሀፍዎ ምእራፍ 11 ላይ ያተቱት የአማራ አለመኖር
አማራ ማለት ሀይማኖት ነው ስላሉ በአለም ላይ ያሉ ትናንሽና ትላልቅ እምነቶች ውስጥ ዝርዝሩን ለማግኘት ብዙ ደክሜ ሳላገኘው ቀረሁ፡፡ አማራ ማለት ክርስቲያን ከሆነ አገው ለምን አማራ እንዳልተባለ እንዲያብራሩልኝ እጠይቃለሁ፡፡ ሁለቱም ቅዱስ ላሊበላ የምትሄዱ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ እያሉ ለዘመናት በአንድ የክርስትና ማእድ ሲሳተፉ ኖረዋል፡፡ አንዱ አገው አንዱ አማራ ሆነው፡፡ አማራው ታዲያ ለምን ሁለት የክርስትና ስም አስፈለገው–አማራ እና ክርስቲያን የሚል? ከተለያዩ ጸሀፍት እንደጠቃቀሱትም አማራ ማለት ነጻ የወጣ ህዝብ (ከአረማዊነት የተመለሰ) ማለት ነው፡፡ ታዲያ አገው ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ትግሬ ነጻ አልወጣም ማለት ነው? ወይስ የተለያየ አይነት ክርስትና ነው ያለው–አንዱን ነጻ የሚያወጣ ሌውን ነጻ የማያወጣ? እንደገና በአማራ መሀል የሚኖሩት አርጎባዎች እስላም ናቸው፡፡ ከሌላው እስላም ተለይተው ለምንድን አርጎባ የሚል ስም የያዙት? እነሱ የአርጎባ ጎሳ እስላሞች ሲሆኑ ከአርጎባ ውጭ ያለው ምን ሊሆን ነው?
የጠቀሷቸው ጸሀፍት ወደሀይማኖታቸው የሚያደሉ እንጅ ቁሳዊ ምሁራን እንዳልሆኑ እርስዎ ያውቃሉ፡፡ ከዛም የተነሳ ለእምነታቸው ያደላሉ፡፡ አማራ የሚለውንም የእምነታቸው ዘብ አደረጉት፡፡ ይሁንና አማራ ነጻ ህዝብ የሚለው ራሱ ከጠቀሷቸው ጽሁፎች መረዳት እንደሚቻለው ሀይማኖታዊ ይዘት ብቻ አይደለም ያለው፡፡ ሁለት አንድምታ ነው ያለው፡፡ ወደክርስትና የገባ እና ጦረኛ ሆኖ በነጻነት የሚኖር የሚል፡፡ እርስዎ ግን ጦረኛነቱን ሊያተኩሩበት አልፈለጉም፡፡ ለምን ቢባል ጦረኛነት ክርስትና ከሚለው ትርክትዎ ሊየስወጣዎ ስለሚችል፡፡ እንደሚታወቀው ሰው ወደክርስትና ሲገባ የጎሳ ጦረኝነቱ ይቀንሳል፡፡ እርስዎ የጠቀሷቸው ምንጮች የሚሉት ግን ጦረኛ የሆነና ራሱን ከሌላ ጎሳ ይሁን ከምንም ነገር አስከብሮ የሚኖር ማለት ነው፡፡ እዚህ ላይ ጥያቄው ታዲያ ይህ ህዝብ እርስዎ እንደጠቀሱት ከየነገዱ ጦረኛው ተሰብስቦ አማራ ተባለ ወይስ መጀመሪያውንም አማራ የተባለ ጦረኛ ነገድ ነበር የሚለው ነው፡፡ የእርስዎን ትርክት ብንቀበል እንኳ ቤተ አምሐራ የሚለው ነገር ያፈርሰዋል፡፡ ለምን ላስቴዎች ናቸው ይህን የተሰባሰበ ህዝብ አምሐራ ያሉት፡፡ እናም ይህንን አምሐራ ላስታ………..read in pdf   amarawyethade.

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2018 Moresh Information Center. All rights reserved.