0

ዲገላው የጎረቤታችን ድመት የገጠመው የሞት አደጋና የወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በንፅፅር ሲታዩ። በዶክተር አሰፋ ነጋሽ – (በሆላንድ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ) – 4th of September 2016

በተወለድኩበት በሂርና ከተማ ጎረቤታችን የሆኑ እማማ የልፍተለው እናት የሚባሉ ደግ ሴትዮ ነበሩ። ታዲያ አንድ እሳቸው ያሳደጉት ድመታቸው ከቤት ሸሽቶ ወጥቶ በራሱ ተዳዳሪ ሆነ። በሀረርጌ ከአሳዳሪ ጌታው ቁጥጥር ውጭ ወጥቶ ዱር ገብቶ በራሱ የሚተዳደር ድመት ዲገላ ድመት (ማለትም እንደ አውሬ ዱር የገባ ድመት ማለት ነው) የሚል ስም ይሰጠዋል። ዲገላ ቃሉ ከኦሮምኛ ቋንቋ የመጣ ሲሆን ዛሬ ግን በሀረርጌ ያሉ አማሮችም የአማርኛ ቃል አድርገውት ከላይ በገለጽኩት ትርጉሙ ይጠቀሙበታል። ይህ ድመት በራሱ ተዳዳሪ ከሆነም በኋላ በሰፈራችን ውስጥ ያሉ ጫጩቶችን እየበላ፤ ድስት እየከፈተ፤ የተሰቀለ ቋንጣ እያወረደ ወዘተ የሰፈሩን ነዋሪ በጣም አስቸገረ። ይህ ድመት የእኛንም የዶሮ ጫጩቶች በተደጋጋሚ በልቶብናል። ይህን ድመት እግዚሃብሄር ከገላገላቸውና ከገደለላቸው ለሂርና ስላሴዎች እጣን ይዘን እንመጣለን ብለው የተሳሉ ጎረቤቶቻችንም እንደነበሩ አስታውሳለሁኝ። ድመቱ ግን የሂርና ስላሴዎችም ሳይገድሉት እንደዚሁ ሰፈሩን እያወከ ኖረ። ይህ ድመት አንድ ቀን ምሽት ላይ ነፍሱን ይማረውና አባቴ፤ እናቴ፤ እንደዚሁም አንድ የቤታችን ሰራተኛ የነበረች ሴት ሰራተኛችን ከተቀመጥንበት ክፍል ዘው ብሎ ገባ። ይህን ጊዜ አባቴ ቶሎ ብሎ የተቀመጥንበትን ክፍል በር ጥርቅም አድርጎ በመዝጋት ሽመሉን አንስቶ ያንን ድመት መደብደብ ጀመረ። ድመቱ አባቴ ድብደባውን እንዲያቆም እየጮኸና በአይኑ እየተለማመጠው ብዙ ለመነው። ድመቱ የጣር ድምጹን ይበልጥ እያሰማ አባቴን ሊለማመጠው ሞከረ። ነገር ግን አባቴ የድመቱ ልመናና የጣር ጩኸት ልቡን ሳያራራው ድመቱን መደብደብ ቀጠለ። ድመቱ አባቴ በምንም ዓይነት መንገድ ምህረት እንደማያደርግለትና ሊገለው እንደ ቆረጠ ባወቀ ጊዜ ልምምጡን አቆመ። ከዚያም ድመቱ የትግል ዘዴውን ቀይሮ ልክ እንደ ነብር ወደ አባቴ ላይ መወርወርና አባቴን ማጥቃት ጀመረ። እዚያ የነበርነው ሰዎች የድመቱ ባህርይ ወደ ነብርነት መቀየር አስፈርቶን እጅግ ተጨነቅን። እኔም ሆንኩ እዚያ የነበሩት ሁሉ በጣም ፈራን። አባቴም ምንም ፍንክች ሳይልና ሳይደናገጥ ድመቱን መደብደቡን ቀጠለ። በተለይ እኔ የስምንት ዓመት ልጅ ህጻን ስለነበርኩኝ በጣም ፈራሁኝ። ከዚያን ቀን በኋላ ድመት አደጋ ውስጥ ከወደቀ እንደ ነብር የመቆጣት ክህሎት አለው ብዬ አስባለሁኝ። ያ ድመት የተቻለውን ያህል አባቴን ለማጥቃት ሞክሮ፤ አባቴም ድመቱን ክፉኛ ደብድቦትና አዳክሞት እግሩን ጎትቶ ከቤታችን ውጭ ወስዶ ራቅ ካለ አንድ ጥሻ ውስጥ ጣለው። ያ ድመት እንደዚያ ተደብድቦ ከተጣለ በኋላ በሶስተኛው ቀን እንደ ገና ህይወት ዘርቶ እያነከሰ ሲሄድ አየን። ያ ድመት እንደገና ቆሞ ነፍስ ዘርቶ ይነሳል ያለ ሰው አልነበረም። የድመትም ነፍስ ጥኑ ነች የሚለውን ብሂል ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ማመን ጀመርኩኝ።trad in pdf …ዲገላው የጎረቤታችን ድመት የገጠመው የሞት አደጋና የወቅቱ የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል በንፅፅር ሲታዩ።

Filed in: Amharic News, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2018 Moresh Information Center. All rights reserved.