0

ጎንደር፡ ጎጃም ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ እያደረጉ ነው !!!

▼▼በውስጥ መስመር የደረሰን መረጃ ነው ፡-
እባካችሁ ሼር አዲርጉ
……..
“ጎንደር ሙሉውን ከወያኔ ነብሰ በላ ጋር እየተናነቅን እንገኛለን መውጫ መግቢያ መንገድ በሙሉ በህዝባችን እየተዘጋ ነው። ትግሉም ከፍ ወደ አለ ደረጃ በማድረስ አጋዚዎችን እየደመሰሰ ህዝቡ የአጋዚን መሳሪያ እየታጠቀ ይገኛል። ጎንደር የገባ አጋዚ ወታደር መውጫ ቀዳዳው ጠፍቶት በየቦታው እየተበተነ ይገኛል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወደ ህዝቡ እየተቀላቀለ ይገኛል። ጎንደር ገበሬውን በሙሉ መሳሪያውን ታጥቆ በየተራራው ላይ በመሰባሰብ ነቅቶ እየጠበቀ ነው። ትግሉ የመኖር ያለመኖር ጉዳይ ሆኗል! ወይ ወያኔ ወይም ደግሞ እኛ እንኖራለን በማለት ከፍተኛ ፍልምያ ውስጥ ነው። በጣም ብዙ የአጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል። በጣም ብዙ ቆስለዋል። የጎንደር ህዝብ ታጣቂው የጎንደር ገበሬ በአድነት የነጻነት ትግል እያደርግን ነው። ከአጋዚ የተማረኩ መሳሪያዎች ህዝብ እየታጠቀ ወደ ትግሉ ጎራ በቁርጠኝነት እየገባ ነው።

በጎንደር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ መኪናዎች በሙሉ እየተለያዩ የወያኔ መገልገያ እና የወያኔ ሰራዊት የሚያገለግሉት ላይ ህዝባችን እርምጃ እየወሰደባቸው ነው። ትግሉ የህዝብ ትግል ከሆነ ቆይቷል የታሰሩ ወገኖቻችንን እስር ቤት ታጣቂው እየሰበረ እያስፈታ ይገኛል። ጎጃም ባህር ዳር እና የተለያዩ የጎጃም ዞኖች ቻግኒን ጨምሮ ታላቅ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል። ባህር ዳር ከቤት ያለመውጣት አድማ በመደረግ ላይ በነበረበት ሰዓት አጋዚ ህዝባችንን አድኖ ለመውሰድ ሙከራ ሲያደርግ ህዝብ ግልብጥ ብሎ በመውጣት ወደ አደባባይ አመጽ ተቀይሯል። ከህዝቡ ወገን መስዋዕትነት የሆኑም ሲኖሩ ከአጋዚም እንድሁ መሃላችን ሆነው ህዝባችንን ከሚያስበሉ አቃጣሪዎች ብዙዎቹ ተገድለዋል። ንብረታቸውም ወድሟል። ያመለጡም እንዳሉ ተነግሯል። እግር በግር እየተከልናቸው ነው። በመሃላችን የተሰገሰጉትን ሰላዮች እያጸዳንና ንብረታቸውን እያወደምን እንገኛለን። ህዝቡ እና የታጠቀው ገበሬ ተቀናጅቶ እየሰራ ነው።

በዚህ ምክንያት ባህር ዳር የገባው ፌዴራል ፖሊስ መፈናፈኛ በማሳጣት እርምጃ እየተወሰደበት ይገኛል። ህዝቡም በሚማረከው መሳሪያ እራሱን እያስታጠቀ ይገኛል።
የጎጃም ህዝብ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጥሪ አድርጋል። ማሸነፍ ከማትችሉት ህዝብ ጋር መጋጨት የለባችሁም!!! የህዝብ ጠላት የወያኔ ጦር አጋዚ እንጅ ሌላው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አይደለም! እኛ እናንተን ስንገድልም ሆነ ስናቆስል ደስተኛ አይደለንም። ግን እራሳችሁን መለየት ባለመቻላችሁ በሚደርስባችሁ ጉዳት የጎጃም ህዝብ ሊጠየቅ አይገባም። ይልቁንም የህዝብ አገልጋይ እንደመሆናችሁ ወደ ህዝብ ተቀላቀሉ የሚል ጥሪ እያስተላለፉ ይገኛል። ህዝባችን የጀመረውን ትግል ዳር ሳያደርስ ወደ ኋላ እንደማይል ተማምሏል።

ወያኔ ከመንበሩ ነቅለን ካላጠፋነው ከእንግዲህ በኋላ እንዲያገግም ካደረግነው የአማራን ዘር በሙሉ አድብቶ እንደሚያጠፋና የአማራን ወጣት እየለቀመ ወደ አልታወቀ ስፍራ በማጋዝ የዘር ማጥፋት እንደሚያደርግ ህብረተሰቡ ስለተገነዘበ ከወያኔ ጋር የሚደረግ ምንም አይነት ድርድር የለም። አማራ ለአገሩ እና ለእውነት ሟች እንደሆነ እና ጀግና የጀግና ዘር እንደሆነ ጎጃም ለነጻነት በመነሳት እያስመሰከረ እንደሆነ በውስጥ መስመር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
ጎንደር፡ ጎጃም ከወያኔ ጋር ትንቅንቅ እያደረጉ ነው፡

አባቶች ሲናገሩ #ጎጃምእናጎንደር የገባ የጠላት ሰራዊት በሰላም መውጣት አይቻለውም ብለው ይናገሩ ነበር አሁን ግዜው ደረሶ በተግባር እያየነው በመሆኑ የጀግኖች ምድር ተጋድሎአቸውን በታላቅ ቁርጠኝነት እና ድል እያከናወኑ ይገኛሉ። ሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍላተ አገሮች ትግሉን በመቀላቀል አገሪቱ ከነብስ በላው ወያኔ ነጻ የማድረግ የሁላችንም አላፊነት ስለሆነ ሁሉም በያለበት በመነሳት አኩሪ ገድል ይሰራ ዘንድ ያስፈልጋል።

ሞት ለወያኔ !! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ይሁን !!!”

Nigiste Saba-Ethiopia's photo.
Nigiste Saba-Ethiopia's photo.
LikeShow more reactions

Comment

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.