0

በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ ፣ ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ

በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሠተው ጉዳይ ላይ የሕዝባዊ ማስታወቂያ ጥሪ
ከአቤቱታ አቀነባባሪ ኮሚቴ
ከኢትዮጵያ ውጭ የሚኖሩ የሰብእና [humanities]ና፣ የማኅበራዊ[social sciences]፣ እንዲሁም የሳይንስ [sciences] ጥናቶች ሊቃውንትና ምሁራን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ባገራችን ውስጥ የተፈጠሩት አንገብጋቢ የፖለቲካ፣ የሰብኣዊ መብት፣ የምጣኔ-ሀብትና የማኅበራዊ ኑሮ ከፍተኛ ቀውሶች እንዲፈቱና ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ለማድረግ፣ ለተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሓፊ አቤቱታ ለማቅረብ፣ ከላይ የተጠቀሰው ኮሚቴ ፊርማ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ኮሚቴው በውጭ የምትኖሩት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንትና ምሁራን የሆናችሁ በሙሉ ከዚህ በታች በሚገኘው ድረ-ገጽ ገብታችሁ ፊርማችሁን በማስፈር ላገራችሁና ለወገኖቻችሁ ስትሉ ድጋፋችሁን በማበርከት በአቤቱታው እንድትተባበሩን በአክብሮት ይጠይቃል። የአቤቱታው ቅጂ፣ እንዳስፈላጊነቱ ተስተካክሎ፣ ለአሜሪቃ ፕሬዚደንት [USA President]፣ ለአውሮጳ አንድነት ሸንጐና[European Union Parliament] ለአውሮጳ አንድነት የሰብኣዊ መብቶች ጉዳይ ወኪል [European Union Commission for Human Rights] ይላካል። ቅጹን አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ በሚከተለው መልክ እንድትሞሉት በጥብቅ እናሳስባለን።

Sign this petition [እውነተኛ ሳይሆን ለምሳሌነት/ለናሙና ብቻ የተሰጠ] Full Name፡ [Dr., Professor etc ] Gabremaryam Paulos, [PhD, JD,MD etc] ማዕርግዎን እንዳስፈላጊነቱ ከፊት ወይንም ከኋላ ያስገቡት።] Location: University of Manchester, UK [ያገር ስም ሳይሆን፣ የሥራዎን ድርጅት/ተቋምና ያለበት ቦታ/አገር።] Email : gpaulos@manchester.edu [የድርጅትዎን/የተቋምዎን ኢሜይል ቢያስገቡ ይመረጣል።]

የድረ-ገጹ አድራሻ እንደሚከተለው ነው።

http://www.petitionbuzz.com/petitions/appeal-to-the-un-secretary-general

for further information please read the pdf file………Petition Prologue

Filed in: Amharic News, eMedia, English News, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2018 Moresh Information Center. All rights reserved.