0

ማንነትን ፍለጋ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ታጅቦ አዲሱ የአማራ ትውልድ በጎንደር ከተማ ጎራው እያለ ነው!! <<<< በኃያል ሰው>>>>

ማንነትን ፍለጋ በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ታጅቦ አዲሱ የአማራ ትውልድ በጎንደር ከተማ ጎራው እያለ ነው!!

<<<< በኃያል ሰው>>>>

ይህን ኩሩ ህዝብ፣ ይህን ባለታሪክ ህዝብ፣ ይህን የእምነትና የፍቅር ባለፀጋ የሆነ ህዝብ፣ ይህን ለእምዬ ኢትዮጵያ አንድነትና ክብር በዘመናት የተዋደቀ ህዝብ ማሸነፍ ፈፅሞ እንደማይቻል ታሪክ ምስክር ነው። የአማራ ትዕግስት፣ የአማራ ማስተዋል፣ የአማራ አርቆ አሳቢነት ለባንዳዎችና ለአገር ሻጮች ፍርሃት መስሎ ከታያቸው በእውነትም ተሸውደዋል። አማራ ፈጥኖ አይነሳም፣ ከተነሳም ድል ሳያደርግ ወደ ቤቱ በጭራሽ አይመለስም። አንዱ ጀግና ኮሎኔል ደመቀ የለኮሰው የነፃነት ሰደድ እሳት መላውን አማራ በቁጣ ሞልቶታል፣ በቁጭትና በእልህ እንዲነሳም ምክንያት ሆኖታል።
አማራነት ትናንትም፣ ዛሬም፣ ወደፊትም አሸናፊነት ነው። አማራን አንበርክኮ ባርያ አድርጎ ለመግዛት መሞከር በዓለም ትልቁን የህንድ ውቅያኖስ በባልዲ እየቀዱ ለማድረቅ እንደ መሞከር ያለ ከንቱ ቅዠት ነው። ዛሬ በእልህ፣ በማንነት ጥቃት ቁጭት፣ በወያኔ ንቀት ቁጭት የተሞላው የአባ ታጠቅ ካሳ የቴወድሮስ ትውልድ የሰይጣኒዝም አርማ ያለበትን ባንዲራ አሽቀንጥሮ የአባቶቹ ክብር የሆነችውን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ይዞ ጎንደርን በአማራ መንፈስ አድምቋታል።
አማራነት ለዘላለም ይኑር!! ወልቃይት አማራ ነው!! ሁመራ አማራ ነው!! ራያ አዘቦ አማራ ነው!! መተከል አማራ ነው!! አባቶቻችን ያቆዩልን ዳር ድንበር በልጆቻቸው ተጋድሎ ይከበራል!! ብአዴን ለአማራ ህዝብ ህልውና ይቁም!! የአማራ ህዝብ አሸባሪ አይደለም!! የወልቃይት የማንነት ጥያቄ በአስቸኳይ መልስ ያግኝ!! በሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ጎንደር በጩኸት እየተናወጠች ነው።
አዎ ይህን ሳይ፣ ይህን ስመለከት አይኖቼ በእምባ ተሞሉ፣ ተንበርክኬም ፈጣሪዬን አመሰገንኩት፣ በእርግጥ የአማራ ትንሳኤ ዛሬ ተበስሯልና በዓለም ዙሪያ የተበተናችሁና በአገር ቤት ያላችሁ የጊዮን ልጆችና እልል በሉ። ወያኔ ዳግም በአማራ ላይ የጥላቻ አንደበቱን እንዳያላቅቅ ትውልዱ የመጨረሻ መልዕክቱን በጀግንነት መንፈስ እያሰማ ይገኛልና።

ክብር ለአማራ ትንሳኤ ዋጋ እየከፈሉ ላሉ ጀግኖች!!
ክብር አማራነትን ለማስከበር ዋጋ እየከፈለ ላለው አዲሱ የአማራ ትውልድ!!
ክብር የአማራን የማንነት ሰንደቅ በሁሉም ቦታ እያውለበለቡ የትንሳኤ ከዋክብት እየሆኑ ላሉት የጊዊን ወጣቶች ንቅናቄ!!

ድል ለአማራ ህዝብ!!
ድል ለዳግማዊ መዐሕድ!!
ድል ለአገራችን ህዝቦች!!

Hayal Sew's photo.
Hayal Sew's photo.

 

Filed in: Amharic News, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.