0

ለውድ ወንድሜ ፕሮፌሰር ዓለማንተ ገብረሥላሴ፤ አንዱዓለም ተፈራ

ለውድ ወንድሜ ፕሮፌሰር ዓለማንተ ገብረሥላሴ፤

እንደምን ስንብተሃል? በጣም በቅርብ እንተዋወቃለን። አብረን በልተን ጠጥተናል። ለብዙ ዓመታት በተለያዩ የፖለቲካ ስብስቦችና ድርጅቶች አብረን ሠርተናል። እስከዛሬ ያደረግከውን ጥረትና የከፈልከውን አስተዋፅዖ በደንብ አውቃለሁ። የሕግ ምሁር ብቻ ሳትሆን፤ ስሙ በዓለም በጣም በሚደነቅ ዪኒቨርሲቲ ውስጥ መምህር ሆነ ለብዙ ዓመታት አገልግለሃል። በትናንት ወዲያው የወገናችንን ብሶት ለማሰማት በተደረገው የዋሺንግተን ዲ.ሲ. ሰላማዊ ሰልፍ ላይ፤ የጎንደር ኅብረትን ወክለህ ያቀረብከውን መልዕክት ተመለከትኩት። በጣም ደስ ያላለኝ ግንዛቤ አለኝ።
በጎንደር እየተካሄደ ያለው ሕዝባዊ አመጽ፤ በጣም በከፍተኛ ደረጃ ማስተዋልን የሚጠይቅና፤ በተለይም ምሁራንን አጣብቆ የያዘ ጉዳይ ነው። ይህን ጉዳይ ምሁራን መረዳትና ይዘቱን ሆነ እንደምታውን ተመልክቶ፤ ሂደቱን በመመርመር፣ ቅርጽና የአደረጃጀቱን ትምህርት በመሥጠት መሪዎችን መርዳት፤ ኃላፊነታቸው ነው። ይህ፤ ዛሬ በአሁኑ መልኩ ያለው የጎንደር ወገናችን በአማራነቱ መነሳት፤ ነገ ከባድ የሆነ ፈተና የሚገጥመውና ሁላችንም የያዝነውን አቋም የምንፈትሽበትና ተሳትፏችን የሚጠየቅበት ነው። ነገ የትግሬዎች መንግሥት፤ መንግሥታዊ ሙሉ መዋቅሩን በመጠቀም ፍጅት የሚያስከትልበት ሀቅ ከፊታችን ተጋርጧል። ነገ ቀሃና አንገረብ ቀለማቸውን የሚቀይሩበት ሀቅ አንዣብቧል። አማራ ካሁን በኋላ አማራነቱን ያስከብራል። ወልቃይቴ የአማራ ማንነቱን እስከ የመጨረሻዋ የደሙ ጠብታ ድረስ ቆሞላታል። ወራሪው የትግሬዎች መንግሥት ደግሞ ፍጹም ወልቃይትን አሳልፎ ለባለቤቶቹ አይመልስም። ይህ ግብግብ የማንነት፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የአስተዳደር፣ የሀገርና የትውልድ መሆኑን እኔ ላንተ አልነግርህም። ከኔ የበለጠ ታውቀዋለህ።
የፖለቲካ ትግል ወደፊት የሚነዳው፤ ማታገያ ሆነው በገሃድ በአደባባይ በሚቀርቡ የጥሪ ፉካሬዎች ነው። እኒህ መፈክሮች ሆነው፣ ዘፈን ሆነው፣ መሸላይና ማቅራሪያ ሆነው ታጋዩን ያነሳሳሉ። ታጋዩን ክፍል አቅፈው ያስራሉ። እኒህ የጥሪ ፉከራዎች የትግሉን ምንነት ይናገራሉ። እኒህ የጥሪ ፉከራዎች የትግሉን ዳር ደንበር ያካልላሉ። እኒህ የጥሪ ፉከራዎች የታጋዩን ማንነት ይገልጻሉ። በኢትዮጵያ የ “አማርኛ ተናጋሪዎች” ማለት፤ አማርኛ እንደ የሀገሪቱ የመንግሥት ቋንቋ፤ ማንንም የማይለይ ትርጉም የለሽ ባዶ የሆነ ግላጼ ነው። ለዚህ ባዶ ለሆነ ማካለያ ግንዛቤ መነገር፤ ምናልባት ምክንያቱ፤ ባንድ ጊዜ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት ከመፈልግ የመጣ ይመስለኛል፤ ባንድ በኩል ባለጉዳዩን አማራነትን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያዊነትን ያነገተውን ሁሉን አማራኛ ተናጋሪ ለማቀፍ።ለወንድሜ ለጵሮፌሰር ዓለማንተ ገብረሥላሴ……read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.