0

ተዕግሥት ሠላም ወዳድነት እንጅ ፍርሃት አይደለም ! ከዳግማዊ መዐሕድ

AAPO II emblem 2016

      ተዕግሥት ሠላም ወዳድነት እንጅ ፍርሃት አይደለም !
አገራችን ኢትዮጵያ ታላቅ ሕዝብና አኩሪ ታሪክ ያላት አገር ነች። ታላቅነቷም በታሪክ የተረጋገጠ ነው። በዚህ ኢትዮጵያ ባላት ቀደምት ታሪክ ውስጥ ዐማራው የተጫወተው ሚና ከፍተኛ መሆኑ አሌ የማይባል ሐቅ ነው። ይሁን እንጅ በየዘመናቱ አገሪቱን ይገዙ የነበሩ መንግሥታት፣ አማርኛን የቤተ መንግሥትና የሥራ ቋንቋቸው በማድርጋቸው የተነሣ ዐማራው ለረዥም ዘመናት እንደ ገዥ መደብ ሲታይ ቆይቷል። ይህ አስተሳሰብ በሌሎች ዘንድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበር መጥቶ የኋላ ኋላ ተቀናቃኞቹና ታሪካዊ ጠላቶቹ ቂም ቋጥረው ፣ ዘመን ቆጥረው እንዲዘምቱበት አስችሏቸዋል።
በተለይም ወታደራዊው የደርግ ኮሚኒስት መንግሥት የኢትዮጵያን ሕዝብ የንብረቱና የአገሩን የባለቤትነት መብት በሦሻሊዝም ስም በኃይል በመንጠቅ እንዲከስም አድርጎ በመውደቁ፤ የኢትዮጵያ ጉዳይ “ወና ቤት በቁንጫ ይወረራል” አይነት ሆነና የትግራይ ጽንፍኞች ያገኙትን ይህን ክፍተትና መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ መላውን የአገሪቱን ሕዝብ በቋንቋ በመከፋፈል ፤ ሕዝቧን ለመከራ! አገሩን ለውድቀት ከመዳረጋቸው በተጨማሪ ፤ የትግራይ ሕዝብ ዋና ጠላት የዐማራ ገዥ መደብ ነው። የትገራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር የወል ምኞት ደግሞ ጨቋኙን ዐማራ (ደርግ) መንግሥት መጣል ነው።በሚለው ጭፍን ጸረ ዐማራ ጥላቻና ጽንፈኛ አቋማቸው በመግፋት ባደረጉት ዐማራን የማጥፋት መጠነ ሠፊ ዘመቻ፣ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የዐማራው ነገድ በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲያልቅ ተደርጓል።
ስለሆነም፣ ዛሬ በሕይወት ያለው የዐማራው ሕዝብ ከምንግዜም ባላይ ውድቀቱን ሲጠብቁ በነበሩ ታሪካዊ ደመኛ ጠላቶቹ እጅ እዲወድቅ ተደርጓል። በትግራይ መራሹ ጎጠኛ ህወሐት አስተባባሪነት፣ እየተፈጸም ያለው እና “ኢትዮጵያ ለማጥፋት ዐማራን ማጥፋት” የሚለው ጸረ-ኢትዮጵያዊንት የጥፋት ተለዕኮ፣ አድማሱን አስፍቶ፣ እነሆ ዐማራውን አገርና
ታሪክ የለሽ ለማድረግ በሠፊው እየተሠራበት ይገኛል። በዚህ ረገድ እየተፈጸመ ያለው መጠነ-ሠፊ የዐማራን ነገድ የማጥፋትና የማጽዳት ዘመቻ አካል የሆነው፣ አስከፊ የጅምላ ጭፍጭፋና ከሚኖርበት ቀየውና ሥፍራ ማፈናቀል፤ ባንድ በኩል ታሪክን በመካድና በመበረዝ፣ ዐማራውን ከኢትዮጵያ ሕዝብና ከኢትዮጵያዊነት ለመገንጠልና በሎም የታሪክ
ሠለባና አገር አልባ ለማድረግ እየተደረግ ያለው መጠነ ሠፊ ርብርብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥር እየሰደደና እየተባባሰ ነው።

በጎንደር ሕዝብ ላይ ወያኔ የከፈተውን ቀጣይና መጠነ ሠፊ ጭፍጨፋና አፈና በማውገዝ የተሠጠ መግለጫ…..read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.