0

የዐማራ ሕዝብ ትንሳዔ የግፍ ገፈት ቀማሽ በሆኑት የዐማራ ተወላጆች ልበ ሙሉነትና ቆራጥ የትግል ውሳኔ ላይ ያረፈ ነው። ከፈለገ-ዓሥራት

11025230_1409817589326082_4548888202015992029_nየዐማራ ሕዝብ ትንሳዔ የግፍ ገፈት ቀማሽ በሆኑት የዐማራ ተወላጆች ልበ ሙሉነትና ቆራጥ የትግል ውሳኔ ላይ ያረፈ ነው።

የትግራይ ፋሽስቶች የዐማራ ሕዝብን በፖሊሲ  ቀርጸው ማጥፋት የጀመሩት ዛሬ አይደለም።የዐማራውን  መኖርያ አካባቢዎችን ፣  ሥራ ፍለጋና ልመናን ተገን አርገው በሰብዓዊነት አስጠግቶ የርህራሄ እጁን የዘረጋለቸውን ሕዝብ  በመናቅና  አካባቢውን ተስፋፍቶ በመያዝ ትግራዊ ለማድረግ በተሰላ መንገድ  የሥራ ፈላጊና የለማኝ ግብረ ኃይል በማሰማራት  ስውር ወረራ በመፈጸም ነው።

የወልቃይት ተወላጆች እንደሚመሰክሩት  ወያኔ ተከዜን ተሻግሮ የወልቃይት ዐማራን ህዝብ ማጥፋት የጀመረው ገና ለስልጣን ከመቆናጠጡ  አሥራ አንድ ዓመት በፊት እንደ ኢትዮጵያ  አቆጣጠር  በ1972  መሆኑን ይጠቁማሉ። ከሱዳን ድንበር ጋር ያለእንቅፋት ለመገናኘት እንዲቻል በሚል ሽፋን አከባቢውን የተቆጣጠሩት የትግሬ ፋሽስቶች ይህን ዓላማቸውን ዕውን ለማድረግ እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግፍ በወልቃይት ሕዝብ ላይ ፈጽመዋል፣ ዛሬም እየፈጸሙ ይገኛሉ። የሰሞኑ የዜና አውታሮች ዘገባም ይህንኑ ያመላክታል።

ፈለገ- ዓሥራት ዋና ጥያቄ  አርጎ የዐማራ ሕዝብ ትኩረት እንዲሰጥበት የሚሻው ፣ ይህ ለምን ሆነ ? ዐማራው እንደ  ብዛቱ ፣ታሪኩና ክብሩ ለዚህ ዓይነቱ ብሔራዊ ውርደትና ውድቀት ላይ እንዴት ሊደርስ ቻለ? ዐማራው ከውርደትና ከጨርሶ መጥፋት እራሱን ለመታደግ ምን ማድረግ ይጠበቅበታል? እነዚህን ጥያቄዎች  እያንዳንዱ የዐማራው ማሕበረሰብ  አካል የሆነ ሁሉ  በጥኑ ሊመረምርና  ሚናውን ሊለይበት የሚገቡ መሠረታዊ ነጥቦች ናቸው። እንዲያው  በየግዜው በሚከሰቱ ጉዳዮች ዙሪያ ዋይ ዋይታ  የትግራይ ፋሽስቶችን የግፍ ተግባር የሚገታ አይሆንም። መፍትሄው ግፍ የፈጸሙ እጆቻቸው ና ግፍ የተናገሩ ምላሶች  ሲቀጡ፣ ግፍ መፈጸሚያ  ተቋማት ሲደመሰሱ፣ የግፉ ፈጻሚ፣ አሰፈጻሚና ተባባሪዎች አይቀጡ ቅጣት ሲቀጡ ብቻ ነው።

የዐማራ ሕዝብ ሆይ !

አያት ቅድመ አያቶችህ ደማቸውን አፍስሰውና አጥንታቸውን ከስክሰው ዳር ድንበሯን ጠብቀው ባቆዩህ አገርህ ፣በፍተህ ለመኖር አልቻልክም።ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በሰላም አርሰህና ነግደህ ለመኖር ያጋጠሙህን ችግሮች በትዕግስት ተሸከምካቸው። ከአብራክህ የወጡት ልሂቃንም  « የጨዋ ፖለቲካ » እያለሙ  ግራ እያጋቡ ባርነትን እንድትላመድ አረጉህ።ባጠቃላይ ትዕግስትህና የምትሰበከው «የጨዋ ፖለቲካ» ግን መከራህን አበራከተው እንጂ አላቃለለልህም። በሞትክላት አገር ውስጥ  ከመኖር ወደ አለመኖር ጠርዝ ደረስክ። ልጆችህ ማንነታቸውን እንዲክዱ የስነልቦናና አካላዊ ተጽዕኖ ተደረገባቸው። አሁንም ገና የተደገሰልህ መከራ በዚህ እንደማያበቃ  የወልቃይት ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በጽኑ ልታጤን ይገባል።

የመኖር ትርጉሙ ምንድን ነው? ሌሎች ሲበሉ ያውም የገዛ ዳቦህን፣ ምራቅህን እየዋጥክ ዝም ብሎ ማየት ነው? ሌሎች ባለግዜዎች አንተን እያፈናቀሉና እያሰደዱ እነሱ ግን ሁሉን ተቆጣጥረው ከብረው ሲቧርቁ አንተ አንገትህን ከጉልበትህ ላይ ደፍተህ መሬት መቆርቆር ነው? የምትከበረው ከጫማቸው  ስር ወድቀህ ሲያዩህ አይደለም ። አንገትህንም ደፍተህ እየተከዝክ በመኖርህም አይደለም። በአትንኩኝ በይነት የአንተን ሰብዓዊ ክብር አላስነካም ብለህ ከጠላቶችህ በሁሉም መስክ በልጠህ ስትታይ ብቻ ነው።

ያንተን መከራና ስቃይ የምታውቀው አንተው ብቻ ነህ። ችግርህን የሚጋራህ  የለም። ችግርህን ከተገነዘብክ ፣ምክንያቱን ከተረዳህ ፣የመከራህን ምክንያቶች ከጫንቃህ ላይ አሽቀንጥረህ ለመጣልና በሰላምና በክብር ለመኖር የሚያበቃ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረቱና ውሳኔው ያንተው ብቻ ነው።ከዚህ ውጭ  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሰቆቃህ ምክንያቶች መድህን አይሆኑህም። ነጻ አውጭ ኃይል  ከሩቅም ሆነ ከቅርብ ይመጣልኛል ብለህ በቀቢጸ ተስፋ ውስጥ መኖር ማብቃት አለብህ። ነጻ አውጭው ኃይል አንተው የመከራ ገፈት ቀማሹ ነህ።ከፊትህ ሁለት ሞት ይጠብቅሃል ፣ አንዱ ተዋርደህ ከንቱ ህይወት እየኖርክ በከንቱነት  መሞት ሲሆን ሁለተኛው  ሕዝብን  ከመከራና ስቃይ፣ አገርን ከውርደት ታድገህ የጀግና ሕይወት ኖረህ የጀግና የክብር ሞት መሞት ነው። ፈለገ-ዓሥራት ሁለተኛውን ምርጫ መርጠን የትግሉን ጎራ  እናጠናክር ይላል።  አንተም የዚህ ብቸኛ አማራጭ የትግል መንገድ እንድትከተል ጥሪ ቀርቦልሃል። ስለዚህ እዬዬው ይብቃ። የወሬ ቋንጣ መዘልዘሉ ይብቃ ።ወሬ ስንቅ አይሆንም፣ ከውድቀት በቀር የሚፈይደው ነገር የለም ።

የትግሬ ፋሽስቶችን እብሪት በተደራጀና የታጠቀ የሕዝብ አመጽ ዕልባት መስጠት የወቅቱ ዋና ጉዳይ ነው !

ታገል ታሸንፋለህ !

ፈለገ-ዓሥራት

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.