0

አዲስ ሆኖ ከመቅለል አሮጌ ሆኖ መቀበር ! ከላኮመልዛ

              አዲስ ሆኖ ከመቅለል አሮጌ ሆኖ መቀበር

“ ክፉንም ደጉንም ሰምተን መጣን “ አለ አሉ ጅብ። እነዴት ቢሉት፣ ደጉ አህያ ጠፋች ሲሉ መስማታችን ሲሆን፣ ክፉው ደግሞ ሰዉ ሁሉ ጦር ያለህ ጦርህን፣ ገጀራ አለህ ገጀራህን ይዘህ ውጣ፣ እየተባባሉ ሲጠራሩ መስማታችን ነው፣ አለ ይባላል።

ምንም እንኳ ተፈጥሮ የተዋበ የነጻነትና የፍትህ ሞገስ ለሁላችንም እኩል አጎናጽፋን ሳለ፣ ዘረኞች ጠባብ የጎሰኝነትን ቡትቶ ካባ ሊደርቡብን ይታገላሉ። የሰላም ሀብታችንን እየዘረፉ መንፋሳችንን ሲያጎሳቁሉ ማየት የዕለት ተዕለት ተግባራችን ከሆነ ከረምረም ብሏል። በዚህ የጥፋት ተልእኮ ደግሞ ወያኔን የሚስተካከለው የለም። ገና ሲፈጠር ጀምሮ ሲያራምደው በነበረው ፍልስፍናና ባነገበው አቋም ሳቢያ ስህተት ውስጥ የገባ ድርጅት ነው። እነሆ ስህተቱ ዛሬ ወደጥፋት ተሸጋገሮ ሀገርንና ህዝብን በማውደም ላይ ይገኛል። ይህ ደገሞ ከእኛ አልፎ በመላው ዓለም ዘነድ የታወቀ ክስተት ነው።

ዛሬ በሀገራችን ያለው የፖለቲካ መርህ፣ እንደአዳኝ ለመብላት ሲባል መግደል፣ የሚሉት አይነት መሆኑ ነው። አምባገነኖች ጥማቸውን ለማርካት ሲሉ፣ አዲስ ከተወለደ ህጻን ጉረሮ ፈልቅቀው፣ ከአራስ  እናት የጡት ወተት የሚዘርፉ አይነት ናቸው፡፡ በደማቸው ሳይቀር አነሱንና የነሱ የሆኑትን ብቻ የሚመግቡ፣ በጨለማ ንቃቃት የሚተኩሱ፣ የህዝብ ፍቅር፣ የሀገር አንድነትና ሰላም የቀትር አቀበት የሆነባቸው፣ ለመገንባት ሳይሆን ለጥፋት የተሳሉ፣ በአይምሮ ዋሻ ውስጥ ጽልመት ሰርተው የሚናኙ፣ የሀገርና የህዝብ ጋሬጣዎች ናቸው።……read in pdfአዲሰ ሆኖ ከመቅለል አሮጌ ሆኖ መቀበር

 

Filed in: Amharic News, eMedia, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.