0

ወልቃይት ላለፉት ሺህ ዓመታት በትግራይ ስር ተዳድራ አታውቅም የ700 ዓመት የታሪክ ሰነዶች፣ማስr።ጃዎች ( Ze Addis)

Page 1 of 16

ወልቃይት ላለፉት ሺህ ዓመታት በትግራይ ስር ተዳድራ አታውቅም

የ700 ዓመት የታሪክ ሰነዶች ማስረጃዎች የ700 ዓመት የታሪክ ሰነዶች ማስረጃዎች

( Ze Addis ( Ze Addis Ze Addis )

በህ.ወ.ሀ.ት የሚዘወረው የኢትዮጵያ መንግስት (ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ) አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ከወሰዳቸው ዓብይ

ኩነታት አንዱ ፣ የሀገሪቱን የፖለቲካን የአስተዳደር ካርታን መቀየሩ እንደሆነ ይታወቃል::

የጥንቱ የኢትዮጵያ ክፍላተ ሀገራት ካርታ በ1994 ዓ.ም ቢቀየርም ፣ አዲሱ ካርታ ብዙ የማንነት ጥያቄዎችንና

እሮሮዎችን አስነስቷል:: ይህ የማንነት መጨፍለቅና የዳግም መካለል ጥያቄ ከሚነሳባቸው ቦታዎች ውስጥ ከጎንደር

ተቆርሶ ወደ ትግራይ የተካለለው የወልቃይት ጸገዴና አላማጣ -ዋጃ ሕዝብ አንዱ ነው።

የወልቃይት – ጠገዴም ሆነ የአላማጣ -ዋጃ ሕዝብ ላለፉት 21 ዓመታት ያለማቋረጥ ወደ ትግራይ መካለላቸውን

በመቃወም አቤቱታ ሲያሰሙ ከርመዋል። ጥያቆውን ለማስቆምና ለመጨፍለቅ ብርቱና ዘግናኝ እርምጃዎች

በህ.ወ.ሀ.ት መራሹ መንግስት ቢካሄድም ፤ እምቢታው እስካሁን አልቆመም:: ይልቁንም የማንነት ጥያቄው

እየተጋጋለ መጥቷል:: በተለይ ላለፉት ስድስት ዓመታት በርካታ ጠንካራ እንቅስቃሴዎች እየታዩ ነው:: ይህንን

የሚያስተባብሩት የሕዝቡ ተወካይ ኮሚቴዎችም የሃምሳ ሺህ ሰው ፊርማ በማሰባሰብ እስከ ፌዴሬሽን ምክር ቤት

በመድረስ ሰላማዊ ጥያቄያቸውን እያሰሙ ነው::

ይህንንም ወቅታዊ ጥያቄ መሰረት በማድረግ ፣ ሀገር ውስጥ ያሉና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ ሚድያዎች በጉዳዩ ላይ

የተለያዩ ዘገባዎችን ና አስተያየቶችን እያስተናገዱ ነው ። ለዛሬውም ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ ፣ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ

የትግርኛው ዘርፍ የወልቃይት ጠገዴን የማንነት ጥያቄ በተመለከተ ከዶክተር ገላውዴዎስ ዓርአያ ጋር ያደረገው ቃለ

መጠይቅ ነው:: ጥያቄና መልሱ ይሄንን ይመስል ነበር:: ጋዜጠኛው አቶ በትረ ለዶክተር ገላውዴዎስ

1“ወልቃይት ከጥንቱም ጀምሮ የትግራይ አካል ሆኖ አያውቅም የሚሉ ወገኖች አሉ:: ስለዚህ

አተያይ ምን ይላሉ”ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ ዶክተር ገላውዴውስ ሲመልሱ “ወልቃይት ከጥንት ጀምሮ በትግራይ ስር አልነበረችም የሚለው አባባል የታሪክ መሰረት የለውም፣ ጌጋይ እዩ ( ስህተት ነው):: ”

1 http://tigrigna.voanews.com/a/welkite-tsegedie-historical-perspective-by-dr-geladewos- araya-part-1-and-2/3253236.html

Page 2 of 16

በማለት ከመለሱ በኋላ እንዲህ አይነት የማንነት ጥያቄ ሲነሳ ጥያቄው መመለስ ያለበት የታሪክ ሰነድን በመመርመር

መሆን እንዳለበት ገልጸዋል::

ዶክተሩ እንደተናገሩት የወልቃይት ጠገዴ መሰል የማንነት ጥያቄ በሚነሳባቸው ቦታዎች ላይ መፍትሔ መስጠት

የሚቻለው ያለፈ ታሪክን በመመርመርና ይዞታው የማን መሆኑን ፣ማን ይኖርበት እንደነበረ ፣ በመለየት ነው:: ይህ

ሁሉን የዓለም ምሁራን የሚያስማማ ሳይንሳዊ እሳቤ በመሆኑ በዚህ ላይ ጥያቄ የለኝም:: ከዶክተር ገላውዴዎስ ጋር

የማልስማማበት ጉዳይ :-

” ወልቃይት ድሮ( በተለይ በኣጼ ዮሓንስ ዘመን ወይም በጥንት ታሪኳ) በትግራይ ስር ነበረች” የሚለውን መሰረት

የሌለው አስተያየት ነው:: ወልቃይት ጠገዴ በታሪኳ በትግራይ ስር ሆና አታውቅም:: ሁላችንንም የሚያስማማን

የታሪክ ሰነድ መረጃ ነውና ታሪክን እንመርምር:: በዚህ ጉዳይ ብዙ ግዜ የሚነሱት አጼ ዮሓንስ ስለሆኑ ከሳቸው

ዘመን ልጀምር

  1. ወልቃይት ጠገዴና አላማጣ ኮረም በአጼ ዮሓንስ ዘመን በትግራይ ሥር አልነበሩም

የታሪክ ሰነድ ማስረጃ የታሪክ ሰነድ ማስረጃ

አጼ ዮሓንስ ከ 1871 ዓ.ም እስከ 1889ዓ.ም ( እ.ኤ.ኣ) ኢትዮጵያን የመሩ ንጉስ ናቸው:: ንጉሰ በንግሥና ዘመናቸው የራሳቸው

ጠንካራና ደካማ ጎን ቢኖራቸውም ፣ ከጠላት ደርቡሽ ጋር በመፋለም ለሀገራቸው ሕይወታቸውን የሰጡ ሰው ናቸው:: ብዙ

የሕወሀት አፈ ቀላጤዎች ፣ ከወልቃይትና ጠገዴ ጋር በተያያዘም የሚጠቅሱት እሳቸውን ነው::

” ወልቃይት እና ጠገዴ ፣ ጥንት በአጼ ዮሓንስ ዘመነ መንስግት በትግራይ ስር ነበረች ” በማለት እንደ ዋና መከራከርያ

ሲያቀርቡት ይደመጣል:: እውነታውን የዘገቡት የታሪክ ሰነዶች ናቸውና የታሪክ ሰነዶችን እንመርምር::በአጼ ዮሓንስ

ዘመን የነበረው የትግራይ ግዛትና ፣ አጠቃላዩ የኢትዮጵያ ግዛት ምን እንደሚመስል በዝርዝር በሀገር ውስጥና በውጭ

ሊቃውንት ተጽፏል:: አንዱም ግን ወልቃይት -ጠገዴ ወይም አላማጣ ዋጃ በትግራይ ስር ነበሩ አይልም:: ለዚህም የእውቁን

የፈረንሳዊ የጂኦግራፊ ፕሮፌሰር ኤሊስ ሬክለስ መጽሓፍን በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል::

በዩንቨርሲቲ ኦፍ ብረስልስ የኮምፓራቲቭ ጂኦግራፊ (University of Brussels, Professor of Comparative

Geography) ፕሮፌሰርና የዴፓርትመንቱ ሀላፊ የነበረው ይሄው ፕሮፌሰር ፤ በ1880 ጀምሮ በርካታ መጽሓፎችን በዓለም

ጂኦግራፊ ላይ ጽፏል:: እነዚህም መጽሓፍቱ ከለንደንና ፓሪስ ጆኦግራፊካል ሶሳይቲ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ አድርገውታል::

Page 3 of 16

ከነዚህ መጻሕፍት አንዱ በ 1880የተጻፈው The Earth and its Inhabitants 2

የሚለው ሲሆን፤ ዘጠን ተከታታይ

ክፍሎች አሉት። የዚሁ መጽሓፍ ክፍል አራት የሰሜን እና ምስራቅ አፍሪካን የወቅቱን ጂኦግራፊ በዝርዝር ይተነትናል:: በአጼ

ዮሓንስ ዘመን የነበረውንም የኢትዮጵያን ክፍላተ ሀገራት በዝርዝር ቁልጭ አድርጎ እንዲህ ጽፎታል:: 3

“The Amhara government provinces are : Dembia, Chelga, Yantangera, Dagossa, Kuarra,

Begemidir, Guna, Saint, Wadla, Delanta, Woggera, Simen, Tselemt, Armachiho,Tsegede, Kolla

Wogerra Waldiba and Wolkait”……….   read in pdf welkait_historical_notes

 

 

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.