0

ለወልቃይት ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ !!ወያኔ በዐማራ ላይ መዝመት የጀመረው በወልቃይት ነው።

AAPO II emblem 2016ለወልቃይት ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ
ወያኔ በዐማራ ላይ መዝመት የጀመረው በወልቃይት ነው።
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በ1972 ዓ ም አድህርዲ በምትባል ትንሽ ከተማ 12 ንጹሃን ቤተሰቦችን ገድሎ 18 አቁስሏል። በ1973 ዓ ም በሃምሌ ወር አዲ ጎሹ አካባቢ፣ ሌሊት የገበሬ ቤቶችን ወሮ 20 የወልቃይት ዐማራ ልጆች ደብዛቸው ጠፍቷል። እስከ 1983 ዓ ም፣ በ10 ዓመት ውስጥ “ባዶ ስድስት” የተባለ የምድር ውስጥ እስር ቤት ከ20000 በላይ የሚሆኑ ንጹህ ወገኖቻችን በግፍ አልቀዋል።
ወልቃይትና ጠገዴ በተፈጥሮ ለም ስለሆኑ፣ በቀደምት ታሪካቸው፣ ከደረቃማው የትግራይ ክልል የሚመጡ ተጠቃሚዎችን፣ ህብረተሰቡ ተቀብሎ፣ አስተናግዶ፣ መሬቱን እንዲአርሱ ፈቅዶ ምርታቸውን ይዘው ክፍለ አገራቸው ትግራይ ይመለሱ ነበር። የዚህ ዐይነቱን መልካም የዐማራ ባህል ውለታ፣ የትግራይ ልጆች የሚመልሱት ትግሬ ካልሆንክ ብሎ በማሰቃየት፣ በእስራት፣ ሴቶቻቸውን አስገድዶ በመድፈር፣ የትግሬ ልጆች በማስወለድ፣ በመግደል ነው። ጭካኔ የተሞላበት ይህ አረመኔአዊ ርምጃ ስልጣኔ ያልነካው ወይንም የእንሰሳ ጠባይ መሆኑ አያጠራጥርም። የሚደንቀው ግን የትግራይ ሕዝብ እየሰማ እንዴት ዝም አለ!
የወልቃይት ጠገዴ ህብረተሰብ ከቀረው ወገኑ ርዳታ ባያገኝም፤ ከ1972 ዓ ም ጀምሮ ህልውናውን ለማስከበር የሞት የሺረት ትግል ማድረጉን አላቋረጠም። ባሁኑ ጊዜ እንዳውም የህብረተሰቡ ቁጣ ከዳር እስከዳር ተቀጣጥሏል። መላው የዐማራ ሕዝብ ለዚህ ወገኑ መድረስ አለበት። በያለበት መብቱን አስከብሮ፣ የወያኔን ጥፋት ለመከላከል ትግሉን ማስተባበር ተቀዳሚ ተግባሩ ነው።
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር በ 1968 ዓ ም በቀረጸው ማኒፌስቶ መሰረት፣ በዐማራውና በዖርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ መውሰድ ያለበትን ቀደምት ርምጃ አገባዷል። በአማራው ላይ ጅምላ ግድያ ፈጽሟል። ከዐማራ የጸዱ አካባቢዎችና ቢሮክራሲዎች ፈጥሯል። የዖርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ተቆጣጥሯል።ገዳሞችን አፍርሷል። የዕምነት ተቋማት በወያኔ ካድሬዎች ተወስደዋል።
ላለፉት 25 ዓመታት ኢትዮጵያዊያንን በጎጠኝነት አናክሶ፣ በአገራችን የኢኮኖሚ ጉልበት፣ መከላከያ ሳይቀር ትግራይ ራሷን እንድትችል አድርጓል። በፈጠረው ጎጠኘነት ምክንያት ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻለ ወደ መጨረሻ ግቡ “ትግራይ ትግርኝ” መንግስትን ወደ ማቋቋሙ ይቀጥላል። በጊዜ ይህን አጥፊ ቡድን ማስቆም ካልተቻለ፣ የኤርትራው ሻቢያም በፈጠረው መርዝ መመረዙ አይቀሬ ነው።   ለወልቃይት ከዳግማዊ መዐሕድ የተሰጠ መግለጫ…..read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.