0

ፈርዖናዊው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሲደገም ምን ይመስላል?

ፈርዖናዊው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ሲደገም ምን ይመስላል?
በ24 አመታት ውስጥ በተለያዩ የኢትዮጵያ አከባቢ ጥቂት የሚባሉ መልካም ለውጦች ቢኖሩም እንኳ ጀግናው የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አይደለም የመልካሙን ለውጥ ሊያጣጥም እንዲያውም በተቀነባበረ ሁኔታ የዛሬ 24 አመት ከነበረበት የህልውናና ኑሮ ብዙ እጥፍ አሽቆልቁሎ ተምዘግዝጎ ወርዶበታል፤ ወያኔ አሰቃይቶታል፤ ህይወቱና አኗኗሩ አመሰቃቅሎበታል፤ ለብዙ መከራና ስቃይ ሞትና እንግልት መታሰርና ደብዛ መጥፋት መሰደድና መሸማቀቅ ዳርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ከ1972 ጀምሮ የወያኔ መርዝ የተርከፈከፈበት ህዝብ ነው። አሳዛኙ ነገር ወያኔ የፈጠረው ችግር በሁሉም የኢትዮጵያ መርዙን ከመትፋቱ ጋር ተያይዞ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወገኑ የየራሱን ህመም ሲያዳምጥ ስለኖረ ከህመም ሁሉ ህመም፣ ከእልቂት ሁሉ እልቂት ሲፈጸምበት፣ በእስራኤላውያን ላይ በኦሽዊትስ ካምፕ በናዚዎች የተቀነባበረው የዘር ማጥፋት በ21ኛው መ.ክ.ዘ በወያኔዎቹ በግልጽና በድብቅ ሲደገም የሚዲያ ሽፋን ስለማይደርሰው ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ሊያውቁለትና ሃይ ሊሉት አልቻሉም መከራዉን ከ1972 አ/ም ጀምሮ ወገኖቹ ሳይደርሱለት ብቻውን ሲጎነጭ ኖሯል።
እዚህ ላይ ለማሳሰብ እምፈልገው ዋና ነጥብ በአማራነታችን እየደረሰብን ያለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ህወሃት በመልካም አስተዳደር ስም ለማስተባበል መሞከር በፍጹም አይቻልም፤ የመልካም አስተዳደር ችግርማ አሜሪካም ውስጥ ቢሆን ይኖር ይሆናል። እኛ አንደላቃችሁ አኑሩን አይደለም እያልን ያለነው። ዋናው ጥያቄያችን የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና መሬት አማራ ስለሆነ ወደ እናት አገራችን ወደ ጎንደር ወደ አማራነታችን መልሱን የሚል ነው። ሰላምን ፈልገው ከመለሱን እጅግ ደስ ይለናል ካልሆነ ደግሞ የእነርሱ ፈቃድና ምስክርነት ሳያስፈልገን በራሳችን ራሳችንን አማራነታችንን አስረግጠን እንመልሳለን።በቃ ይሔው ነው!!! ይህ በትግራይ ተስፋፊና ነጻ አውጭ ቡድን፣ በትግራይ ፖሊስ፣ በትግራይ ልዩ ሃይል፣ በአጋዚ ወታደር፣ በትግራይ አስተዳደር አመራሮችና ካድሬዎች ማዳፈን የማይቻል የሚፋጅ ረመጥ ጥያቄ ነው።ፈርዖናው የወያኔ አገዛዝ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ welqait……….read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.