0

ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት መግለጫ

                               ዳግማዊ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት

                                                            መግለጫ:

AAPO II emblem 2016

    ስማኝ ሕዝቡ ፣ ስማኝ አገሩ !

   ታገል ታሸንፋለህ ! ያለያ ባሪያ ትሆናለህ !-

በኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት ሃያ አምስት የሰቆቃ ዓመታት፣ በዘረኛው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባርና
አባሮቹ በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጸሙት ግፍና በደል የሰው ልጅ ሊሸከመው ከሚችለው ያለፈ ሆኗል።
በፖሊሲ ተቀርጾ፣ ደረጃ በደረጃ በሚፈፀም የዘር ማጥፋት ዘመቻ ዐማራው እየተጠቃ ይገኛል።
በተለያዩ ግዚያት በበደኖ ፣ በአርባጉጉ ፣ በወተር ፣ በአርሲ ፣ በነጌሌ ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በአሶሳ ፣ጎንደር
በአደባባይ እየሱስ፣ በወልቃይት ፣ በጠገዴ፣ በጌዲኦን፣ በጉጂ ፣በምስራቅ ወለጋ ፣በጅጅጋ፣ በጉሙዝና
በቤንቺ ማጂ ዞን፣ በጉራ ፈርዳ ወረዳና በሌሎችም አካባቢዎች ዐማራውን ዒላማ ያረገ ኢሰባዊ
ጭፍጨፋ ተካሂዶ ከፍተኛ እልቂት ተፈጽሟል።
በዐማራ ሕዝብ ላይ የተፈፀመውንና እየደረሰ ያለውን የግፍ አይነትና በደል ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም
። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ለረሃብና ለልመና ተዳርገዋል። ሠራተኞች ዐማራ በመሆናቸው
ብቻ በስርዓቱ አቀንቃኞች ብጣሽ ወረቀት ተባረዋል። የዐማራ ገበሬዎች ለም መሬቶቻቸውን
እየተነጠቁ ሲባረሩ፣ የተቀሩት መክፈል በማይቻል የአፈር ማልሚያ ዕዳ ለችግር ተዳርገዋል ። የዐማራ
ነጋዴዎች በተናጠል፤ ምክንያት ባሌለው እዳ ትርፋቸውን ብቻ ሳይሆን ዋናቸውንም ጭምር እያጡ
ኪሳራ ላይ ወድቀዋል። በአጠቃላይ በሁሉም አቅጣጫ ዐማራው ተከላካይ እንዳይኖረው በማፈን የግፍ
እርምጃቸውን ቀጥለው ከአገሪቱ የተለያዩ ከፍሎች እያፈናቀሉ ከዐማራ የጸዳ አካባቢ እየፈጠሩ ናቸው ።
እንደሚታወቀው፣ ይህን በደልና ግፍ ለመግታት፣ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት መሪ ፣ ሠመዓቱ
ክቡር ፕሮፌሠር አስራት ወልደየስ ህይወታቸውን ሰውተዋል። የዐማራ ህልውና ጉዳይ የሰበአዊነት
መከበርና የመኖር ጥያቄ እንጂ፣ የየትኛውም የፖለቲካ ፍልስፍናም ሆነ የፖለቲካ ድርጅት አጀንዳ ጥያቄ
ሊሆን ባልተገባው ነበር ። የዐማራ ሕዝብ በአገሩ እንደሰው የትኛውም ክፍል የመኖር መብቱን ማንም
በችሮታ የሚሰጠው ወይም የሚነሳው ሳይሆን ተፈጥሯዊ መብቱ ነው።
ኋላ ቀርነት ወይንም አለማስተዋል ካልሆነ በስተቀር ጥያቄው ነግ በኔነት ነው። በሕዝብ ላይ ግፍና
በደል ሲፈጸም፣ ሰብዓዊነት ሲደፈር ፣ ሰላም ሲደፈርስ ፣ ለግልም ይሁን ለጋራ ዕድገትና ብልጽግና
የአገዛዙ ስርዓት ደንቃራ ሲሆን፣ የግልና የወል ነጻነት ሲገፈፍ ለህሊናቸው ያደሩ ሰዎች አምረው
ሊቃወሙትና ሊታገሉት ይገባል።
በመላው ዐማራ ሕዝብ ላይ የደረሰው በደልና ሰቆቃ ያንገበገባቸው ዐማሮች፣ ሁኔታውን በጥሞና
በመመርመር ዘላቂ መፍትሄ ሊሰጥ የሚችል የድርጅታዊ አቅም መገንባት ጊዜ የሚሰጠ አለመሆኑን
በመረዳት ፣ ሰፊ የምክክርና የሃሳብ ልውውጥ ሲያካሂዱ ቆይተው፣ ሕዝባችንን ለመታደግ የሚያስችል
ድርጅት መስርተዋል።AAPO II March 2016…….read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.