0

የት ነው ያለሁት እንዲሁ ይጨንቀኛል! ነፃነት ዘለቀ

የት ነው ያለሁት? እንዲሁ ይጨንቀኛል!
ነፃነት ዘለቀ
ሰሞኑን ልክ አይደለሁም፡፡ መላ ሰውነቴ ልከ አይደለም፡፡ እጅግ ይጨንቀኛል፡፡ ያ ደደብ ደም ብዛት የሚሉት በሽታ ሊይዘየኝ ይሆን እያልኩም እጨነቃለሁ፡፡ የጭንቀት ጥበቴን መነሻ ግን አውቀዋለሁ፡፡ መፍትሔ የሌለው መሆኑ ስለሚሰማኝ ግና እየባሰብኝ እንጂ እየቀለለኝ ሲሄድ አይታይም፡፡ በተረቱ ‘‘የጨው ተራራ ሲናድ ብልህ ያለቅስ፣ ሞኝ ይስቅ’’ ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ የቁም ሞት የምንበሳጭና ተበሳጭተን የበኩላችንን አስተዋፅዖ የምናደርግ በጣም ጥቂቶች ነን – እኔን ሳይጨምር፤ ለኔ መጨነቄ ብቻ ይበቃል፡፡ ሀገር ቤት በተለይም አዲስ አበባ ላይ ያለን ዜጎች ከቁጥራችን በላይ የሆነ የሰላይና የሆድ አደር ግሪሣ ስለከበበን ጥላችንንም እንፈራለን – ስለዚህም ማድረግ ቀርቶ ለማድረግ ማሰባችን ራሱም የሚታወቅብን እየመሰለን ከማሰብም ተቆጥበናል – (የጆርጅ ኦርዌል ‹1984› መጽሐፍ ጨርሶታል)፡፡ ደርግ አመቻችቶት የሄደው የፈሪነት መንፈስ ሀገር ምድሩን አጥልቶበት የወንድነት ምልክታችን ሁሉ ወዳንጀታችን ገብቶ አንዳንዶቻችን ለመሽኛ እንኳን ፈልገን ልናገኘው አልቻልንም፡፡ ‘‘አንዳንዶቻችን’’ እያልኩ ባይሆን አባዘራፎችን ላግባባ እንጂ፡፡ ከየጎራው አኩራፊው በዝቶ ተቸገርን እኮ፡፡
በአሁኑ ወቅት ሀገር አለችኝ አልልም፡፡ ዘረኝነቱ፣ አድልዖው፣ መታሰር መገረፉ … አይደለም የአሁኑ ችግር፡፡ እነዚህ የጠቃቀስኳቸው ችግሮች የዱሮ ናቸው፤ በጣም የተለመዱ፡፡ የአሁኑ የባሰ ነው፡፡
ደርግ ሥጋን ይገድል ነበር፡፡ ወያኔ ግን ሥጋን መግደል ብቻውን ስለማያረካው ከዚህ ደረጃ አልፏል፡፡ እናም ወያኔ የሚገድለው መንፈስን ነው – የሰይጣን ዋና ጠባይም ይሄው ነው፡፡ ወያኔ የሚገድለው ቅስምን ነው፡፡ ወያኔ የሚገድለው ኅሊናን ነው፡፡ ወያኔ ቢገድል ደስ የሚለው ነፍስንም ጭምር ነበር – ይህ ግን የማይቻል ሆኖበት ተቸግሯል፡፡ ስለዚህም መግደል የሚችለው የኛነተቻን ክፍል ተፈቅዶለት አለርህራሄ እየገደለን ነው፡፡
ሥጋን መግደል ቀላልና እርካታውም ጊዜያዊ መሆኑን ሰይጣናቱ ወያኔዎች በሚገባ ያውቃሉ፡፡ አንድን ሰው በጥይት ደብድበው በደቂቃዎች ውስጥ መግደል ቢችሉም ያን አዘውትረው አያደርጉትም፡፡ በርሀብ ወይም በበሽታ ወይም በሥነ ልቦናዊ ጭንቀት ቀስ ብሎ እንዲሞት በማድረግ መዝናናትን ነው የሚወዱት፡፡ ድመት በግዳይዋ ተዝናንታና ሰውነቷን አሟሙቃ ዐይጥን እንደምትበላት ወያኔም በጠላትነት የሚፈርጀውን አካል ወይም ግለሰብ አመንምኖና አክስቶ በማሰቃየት ይገድላል፡፡ ይህ ደግሞ የፈሪዎች ፈሊጥ ነው፡፡ ጀግና በምክንያ የጀብድ ተግባር እንጂ በዕብሪት አይኩራራም፡፡ ጀግና በርህራሄ እንጂ በጭካኔ አይገድልም፡፡ የርህራሄ ግድያን ለማወቅ ወያኔዊ አገዳደልን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከእሥር የተፈቱ ግን በቁማቸው የሞቱ እነ እንትናን በማየት ወያኔ በቁም በመግደል ዲያብሎሳዊ ‘‘ጥበብ’’ እንዴት እንደተራቀቀ ማጤን ይቻላል፡፡ ጉድ ነው! ወያኔ በዚህች ዓለም የእስካሁንም ይሁን የወደፊት ታሪክ ያልታየና ሊታይም የማይችል የመጀመሪያው ትንግርተኛ ፍጡር ነው፡፡ መጥኔ ለመጨረሻ ዕጣው! እንደዚህም ክፋትና ተንኮል አለ?የት ነው ያለሁት እንዲሁ ይጨንቀኛል!…….read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.