0

አድዋ መታወቂያችን፤ ምኒልክ ታዳጊያችን ! የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን እይታ በ ፕሮፌስር ኃይሌ ላሪቦ

haile-larebo              አድዋ መታወቂያችን፤ ምኒልክ ታዳጊያችን

የአድዋ ጦርነት በኢትዮጵያውያን እይታ

በዚህ ወር መግቢያ ላይ ኢትዮጵያዉያን የአድዋን መቶ ኻያኛውን ያመት በዓል በያሉበት በአድናቆት አክብረውታል። በየሬድዮ ጣቢያዎቹ፣ በየፓልቶኮቹ፣ በየማኅበራዊ ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን በየተሰበሰቡበት ሁሉ ስለአድዋ ያልተናገረ፣ ያላሰበ፣ ወኔው ያልተቀሰቀሰ የለም ማለት ይቻላል።
እንደታላቅነቱና ታሪክነቱ ከሆነ፣ የአድዋ ድል ያንድ ቀን ብቻ በዓል መሆን የለበትም። የትም አገር ሂደን ታሪክ ብንመረምር፣ መዛግብታቸውን ብንገለባብጥ፣ የአድዋን ዐይነት ታሪክ የሠራ ሕዝብም አገርም የለምና። የአድዋ ድል አሜሪቃ ነፃነቷን ካገኘችበት ድል፣ ከፈረንሳይና ከሩሲያ አብዮት፣ የደቡብ አፍሪቃ ጥቊሮች በጨቋኞቻቸው ነጮች ላይ ካገኙት የእሪና ድል እጅግ ይበልጣል። ጦርነቱ ከውጩ ሲታይ በሁለት ራሳቸውን በቻሉ ነፃና ልዑላን በሆኑ አገሮች መካክል ቢሆንም፣ ጥያቄው ቀጥለን እንደምናየው ስለሰው ዘር መብትና እኩልነት ነው።

ለኢትዮጵያውያን የአድዋ ድል የማንነታቸው መግለጫ፣የልዕልናቸውና የነጻነታቸው ማረጋገጫ ነው ሊባል ይገበዋል። ግን እንደአብዛኛው ድል፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን ብቻ አይመለከትም። ለሌላውም ዓለም ሁሉ ይትረፈርፋል። በዚያን ዘመን ጨቋኝ ለነበረው ለነጩ ዘርም ሆነ ለተጨቋኙ ያለም ሕዝብ የነፃነት ፋና ነበር። ድሉን ተከትሎ ጥቁር ሕዝብ በያለበት ሁሉ “ኢትዮጵያዊነት” ለተባለ ለብርቱ የሃይማኖትና የፖሊትካ እንቅስቃሴ መሠረት ሁኖ አገልግሏል። ለነጩ ከኢስብአዊነቱ ጭካኔ፣ ነጭ ላልሆነው ዘር ደግሞ ከሚማቅቅበት ከነጭ የባርነት ቀንበር፣ ሁለቱም ነፃ የሚወጡበት ጊዜ ሩቅ እንዳልሆነ ያበሠረ ድል ነው። የድሉ ወሬ እንደደረስው በእንግሊዝ መናገሻ በሆነችው በለንደን ከተማ የሚታተመው ዘታይምስ ጋዜጣ ይኸንን በማያወዛግብ ሁኔታ ጥርት አድርጎ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል።

“ኢጣልያኖች በጀብድነትም ሆነ በጦር ስልት ከሌሎቹ አውሮጳውያን አያንሱም። .. ድሉ የመላ [ጥቊር] አፍሪቃ ድል መሆኑ አይካድም። ይኸም አስተያየት ወደፊት እያየለ ሄዶ በግልጽ የሚታይ ነው። ወሬው በነፋስ ክንፍ በረኻውን አቋርጦ እየበረረ በመጓዝ በነዚህ አገሮች ከጫፍ እስከጫፍ ተዛምቶ ሲያበቃ፣ አፍሪቃውያን አውሮጳውያንን ማሸነፋቸው አይቀርም የሚለውን ስሜት አነቃቅቷል። ነገሩ አስጊ በመሆኑ በኢጣልያኖች መሸነፍ መደሰት [ለነጮች] ተገቢ አይደለም። ሽንፈቱ የሁላችንና የሌሎችም ጭምር ሽንፈት ነው። ዛሬ ቅኝ ገዢ የሆነችውና ከዚያም ባሻገር የነገይቱ አውሮጳ ሽንፈት ነው።”  read in pdf  ….THE BATTLE OF ADWA AND ITS DIMENSIONS 3-15-2016

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.