0

MORESH WEGENIE AMARA ORGANIZATION ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለአውሮፓ ፓርላሜንት፤ ጉዳዩ፦ የአውሮፓ ፓርላማ በቁጥር 2016/2520/RSP ያሳለፈውን ውሣኔ ይመለከታል።

moresh-logoቀን: የካቲት ፲ ፩/፪ሺህ፰ ዓም

ቁጥር: ሞወዐድዉጪ-0020-2008

MW-EXT-0020-2016

ለአውሮፓ ፓርላሜንት፤

ጉዳዩ፦ የአውሮፓ ፓርላማ በቁጥር

2016/2520/RSP ያሳለፈውን ውሣኔ ይመለከታል።

በቅድሚያ ለአውሮፓ ፓርላማ አባላትና ለዓለም ሕዝብ አምላካችን፣ ሰላም፣ ጤና፣ ዕድገትና ብልጽግና እንዲቸረን እንመኛለን። ለተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ ፣ ይህን አቤቱታ የሚያቀርበው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰኘ፣ መሠረቱን የተባበሩት የአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ ሜሪላድ ግዛት ያደረ፣ በሕጋዊነት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሲቪክ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በመላው ዓለም በሚገኙ ከተሞች መሠረቱን ጥሎ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ ድምፅ አልባ ለሆነው የዐማራ ነገድ ድምፅ በመሆን እየሠራ ያለ ሲቪክ ድርጅት ነው። የተቋቋመበት መሠረታዊ ዓላማም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩት ነገዶች በቁጥር ከፍተኛ ከሆኑት በመጀመሪያው ረድፍ የሚሰለፈው የዐማራ ነገድ፣

«ትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር» በሚመራው «የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራስያዊ ግንባር(ኢሕአዴግለሚፈጸምበት የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ድምፅ በመሆን፣ ከሚፈጸምበት የሕይዎት፣ የኢኮኖሚና የመብት ነጠቃ መታደግ የሚችልበትን ዘዴ ማፈላለግ ነው። ዐማራው ከፈጽሞ ጥፋት እንዲድን ጉዳዩን ለዓለም ማኅበረሰብና ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ማሰማት ነው።

ድርጅቱ ከተቋቋመ ሦስት ዓመታት አስቆጥሯል። በነዚህ ዓመታት የትግሬ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር በዐማራው ነገድ ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች የሚያሳዩ ከ

80 በላይ መግለጫዎችን በማውጣት የሚመለከታቸው ወገኖች እንዲያውቁት ጥረት አድርጓል። ከሁሉም በላይ ባለፉት 25 ዓመታት የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር በዐማራው ነገድ ላይ ያደረሰውን የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በተጨባጭ የሚያሳዩ፣ የሰነድ፣ የድምፅ፣ የቦታ፣ የቃል፣ የፎቶ ግራፍ፣ የቪዲዮና መሰል መረጃዎችን አሰባስቦ ለሚመለከታቸው ሁሉ ለማሰራጨት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

የተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ፣ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ መዝኖ፣ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ፣ ዝምታውን ሰብሮ፣

«የኢሕአዴግ መንግሥት በገዛ ሕዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ግድያ፣ እስራት፣ ድብደባና አፈና ምን ያህል የከፋና የሰፋ መሆኑን ተረድቶ፣ ከዚያ አድርጎቱ እንዲቆጠብ ያሳለፈው ይህ ውሣኔ፣ ፓርላማው ለሕዝቦች መብት መከበር የቆመ እንደሆነ ያሳየበት አንዱ አጋጣሚ እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህም የአውሮፓ መንግሥታት ከታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ገንብቶት ለኖረው የመንግሥታትና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት በተሻለ መልኩ መቀጠል የራሱን በጎ ሚናይ ይጫዎታል ብለን እናምናለን። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተከበረው የአውሮፓ ፓርላማ ለዚህ ዓይነቱ ውሣኔ እንዲደርስ ጥረት ያደረጉትን ወገኖች ሊያመሰግን ይወዳል።

ሆኖም፣ ከእያንዳንዱ መልካም ነገር፣ ይብዛም ይነስም የራሱ የሆኑ ችግሮች ወይም ሕፀፆች አጣያም። በመሆኑም ከላይ በጉዳዩ ሥር የተጠቀሰው የፓርላማው ውሣኔ፣ በፊደል ተራ

«E» ሥር የተገለጸው ማለትም «ኢትዮጵያ በሃይማኖት 2

እና በባህል የተለያየ ማኅበረሰብ የሚኖርባት አገር ሆና፣ታላቆቹ ነገዶች ፤በተለይም ኦሮሞ እና የኦጋዴን ሶማሊዎች፣ በአማራውና በትግሬው ወደ ዳር ተገፍተዋል፣ በፖለቲካ ያላቸው የውክልና ተሳትፎ ትንሽ ነው

»

«E. whereas Ethiopia is a highly diverse country in terms of religious beliefs and cultures; whereas some of the largest ethnic communities, particularly the Oromo and the Somali (Ogaden), have been marginalized in favour of the Amhara and the Tigray, with little participation in political representation»

ሲል የደረሰበት መደምደሚያ ከዕውነት የራቀ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ፍጹም ስሕተት ስለሆነ፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማር ድርጅት ይህ እንዲታረም ለማስገንዘብ ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ግድ ብሎናል። ነገሩ እንዲህ ነው…….European parliarment appeal-Amharic-Final(1)……read in pdf

 

Source. Moresh Wegenie

 

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.