0

ኢትዮጵያ የኦሮሞዎችም ናት!! ከብስራት ኢብሳ (ሆላንድ)

በዚህ ርዕስ ላይ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት፣ አቶ ጆሃር መሃመድ “ኦሮሞ የኦሮሚያ ናት” ብሎ በቅርቡ ያወጣውን መጣጣፍ ተመልክቼ፣ እኔም የበኩሌን አስተያየት ሳቀርብ፣ የጆሃር አጀንዳ በትክክል ገብቷቸውና መንገዱ ይጠቅመናል ብለው አቅዋም የወሰዱትን ለማሳመን ሳይሆን፣ የግል አስተያየቴን ለአንባቢዎች ለማካፈል ነው፡፡
በኔ አስተያየት የዘር የፖለቲካ መሪዎች ብዙ ጊዜ እንደዚህ አይነት ከፋፋይና አጨቃጫቂ አጀንዳ ሆነ ብለው የሚመርጡት፣ ሳያውቁ ወይም ሳይገባቸው ቀርቶ ሳይሆን፣ በተለያየ ዕርከን ሊያስፈጽሙ የሚፈልጉትን “ግልጽና ህቡዕ” አጀንዳዎቻቸውን ለማራመድ ይጠቅማል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡
ለተሳሳተ ጥያቄ ትክክለኛ መልስ አይገኝለትም፡፡ ምክንያቱም ጥያቂው የተዘጋጀው፣ መላሹ እንዲሳሳት እንጂ እንዲመልሰው ስላልሆነ፡፡ የጆሃርም ትንኮሳ(ፕሮቮኬሽን)፣ ሊያስከትል የሚችለውን እሰጥ እገባ ቀድሞ ስለሚያውቀው፣ ለዛ በሚመልሰው መልስ “ትርፉን” አስልቶ ስለሆነ፣ ባጭሩ በቀውስ ውስጥ የራሱን ሥራ እየፈጠረ፣ እኔ እያደርኩት እንዳለው፣ ብዙ ሰዎች ለጆሃር መልስ ይሰጣሉ፡፡ ጆሃርም የመልስ መልስ እየሰጠ እይታ ውስጥ ይቆያል ማለት ነው፡፡
ጆሃርም “ኦሮሚያ የኦሮሞዎች ናት” ብሎ ያልጨረሰው የሌሎችንም ባለቤትነት እረስቶት ወይም ሳያውቅ ቀርቶ ሳይሆን፣ ሆን ብሎ ማጨቃጨቂያ ክፍተት ለመፍጠር ነው፡፡ አለበለዚያ ቀና አመለካከት ቢኖር? ኢትዮጵያ የኦሮሞዎችም ናት ወይም ኦሮሚያ የኢትዮጵያውያን ናት ብሎ ሰፊ ሕዝብና ትልቅ ግዛታችን ሆኖ ያለውን እውነታ በጠቀሰ፡፡ በሱ አቀራረብ እንዲመለስለት መስማት የፈለገው፣ “ኦሮሚያ የሚባል ሀገር የለም” ተብሎ ተመልሶለት፣ በዛ የተለመደ ጉንጭ አልፋ ክርክርና እንዲጀመርና፣ ጆሃርም በዛ “የኦሮሞ ሕዝብ ሆይ! ማንነትህን ካዱህ! ሀገርህ ያንተ አይደለም አሉህ!”…ወዘተ እያለ ኦሮሞው ከሌላው ወገኑ ጋር ቆሞ፣ ባጠቃላይ ሀገራችን ላይ እየደረሰ ባለው፣ የፍትህ የዲሞክራሲና ኢ ሰባአዊ ድርጊት ላይ ላይ እንዳያተኩርና የሱን ዕቅድ እንዳያደበዝዝ ነው፡፡ኢትዮጵያ የኦሮሞዎችም ናት!!…..read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.