0

”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ” ከድጡ ወደ ማጡ ፣ በነፃነት ናፈቀ 2015-11-03

”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ” ከድጡ ወደ ማጡ
ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ለፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌና ለሌሎችም በማለት ያስነበበውን ይቅርታ መሰል መጣጥፍ በፌስቡክ ተለቆ ስላየሁት ደጋግሜ አነበብኩት። በመጀመሪያ ”ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ እለት” እንዲሉ የፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ምርጥና አፋጣኝ ፅሁፍ ምን ይህል ቅጥፈት ቢበዛም ቁጥራቸው ትንሽም ቢሆን ውነተኞች እንዳሉ አስመስክረዋልና ምስጋናየ ይድረሳቸው። አንባቢዋቼ ለነገሩ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በማሰብ መንስዔውን ለመጠቆም እሞክራለሁ።
ባለፈው የሳምንቱ እንግዳ በተባለ የኢሳት ፕሮግራም የታሪክ ተመራማሪ በሚል ሽፋን ጋዜጠኛ ፋሲል ዶክተር ላጲሶን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ አማራን እንዳይበላ እንዳይዘራ አድርገው ይዘልፋሉ ያጣጥላሉ። እሳቸውም እንደ ታሪክ ምሁር ሳይሆን እንደ አንድ አማራን አጥብቆ የሚጠላ ጎጠኛ አማራው የሰራውን፣ ታሪኩን፣ የፃፈውን ሁሉ በማዋደቅና በማናናቅ ታሪክ አልባ ከማድረጋቸውም በላይ አዲስ ታሪክ ሊሰሩ እንዳሰቡ አሳውቀውናል። እንግዲህ የሄ የቀረበው ”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ነኝ” በሚለው ኢሳት ነው። ያኔ ታዲያ ጋዜጠኛ ፋሲል ተጠያቂው የተጠየቁትን ትተው ማለት የፈለጉትን ሲቀባጥሩ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሏል። ኢሳትም እንደልማዱ አማራና ኢትዮጵያዊነት ሲወቀጥ በጀ ብሎ አለፈው። ምክንያቱም እራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ነኝ የሚለው ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሳን ብሎም በዘር የተደራጁና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ አጥብቀው የሚተጉ ቡድኖች ጠበቃ በመሆኑ ነው።
ስለሆነም በኢትዮጵያ አንድነት የማያምኑና አማራውን በሀሰት በጡት ቆራጭነት በበዳይነት የሚወነጅሉት እነ ተስፋየ ገብረ አብና አያሌ አገር አጥፊዎች ሲስተናገዱ ለሀገርና ለወገን የሚያስቡ ውነቱን ውነት ሀሰቱን ሀሰት በማለት የሚታወቁት እነ አቶ ጌታቸው ረዳና ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ፕሮፌሰር ሀይሌ ላሬቦ ወዘተ የመሰሉ ምርጥ የቁርጥ ቀን ልጆች በኢሳት አካባቢ ዝር እንዳይሉ በጥብቅ ይከለከላሉ።    ayin ena gjoro…..read in pdf

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.