0

ሎጋው ፈረሰኛ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ሎጋው ፈረሰኛ ( ሄኖክ የሺጥላ )
ድግር ተሸክሜ
ወገል በጀርባዬ
ኩታው ጭቃ መስሎ
እጄ አረም ገሎ
ቁምጣዬም ርሶ
ማዳፌ ጉልበቴ ፣ ላንተ አፈር ልሶ
ላይዳ ና ሞፈሩ
አየሩ እና አፈሩ
መንደሩና ሃገሩ
ስለ አውድማዬ ፣ ቆመው ሲናገሩ
ወፎች ከማሳዬ፣ ዘልቀው ሲዘምሩ
ከማማው ላይ ሆኘ
ወንጭፌን ጠቅልዬ
ሽመሌን ሸምልዬ
ጅራፌን ገርፌ
ገመዴን ጠልፌ
ማሲንቆየን ባፌ
ሎሚየን በቅፌ
እኔ ባላገሩ
የቡሃቃ አውጋሩ
የአንጀትህ ምሰሶ
ዛሬ ክብሬ ፈርሶ
ቤቴ ተደርምሶ
ቀና ስል ብቻዬን
ስሰደድ ብቻዬን
ስገፋ ስዋረድ
ልጆቼ የት ገቡ
ከብቶቼም አልረቡ
ተጋዙ ተገፉ
ቀየውን አለፉ
ወጣሁ ተጠርቼ
ካቀናሁት ሀገር
ገፍተርተር ተር ተር ተር ።

ሂድ ወደ ክልልህ
ማን እዚህ ና አለህ ።

ይህ ያንተ ሀገር አይደልም ሰፈሩ
ሰብሉም ያንተ አይደለም ፣ አይደለም አየሩ
ሂድ አሉኝ ካገሬ
ዴፉኝ በግንባሬ
ወገሌም ወደቀ ፣ ከትከሻዬ ላይ
ድግሩም ተነቀለ ፣ ተሰካ ግቻ ላይ
ይህንን እያዩ
ልጆቼ ዝም አሉ
አረ ኑ አረ ኑ
ያባታችሁን ቤት
የአየዋን መሬት
ሎጋው ፈረሰኛ
በደኖ ላይ ስጋው ፣
ቁልቁል ተወርውሮ
ተቆራርሶ ተኛ
አረ እኛ አረ እኛ !

Henoke Yeshetlla's photo.
Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.