0

በ1965 አፍሪካ አንደነት ድርጅት ከኢትዮጵያ እንዲነሳ የቀረበው አቤቱና የኢትዮጵያ ሚንስትሮች ውጊያ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሃብተወልድና ዶክተር ምናሴ

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አስረኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ግንቦት 18/1965 አንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር አዲስ አበባ ላይ ሲያከብር የተመሰረተው ግንቦት 17/1955 ነው (25 May 1963 G. C ) ሶማሌና ሊብያ ከፍተኛ ተቃውሞ በኢትዮጵያ ላይ አንስተው ነበር:: የድርጅቱ ጽ/ቤት ከአዲስ አበባ እንዲነሳ የሊብያና የሱማሌ ባለስልጣኛት ክፉኛ ተከራክረው ነበር:: ሊብያም ሶማሌም ኢትዮጵያን ባደባባይ ተሳደቡ:: አናናቁ:: በወቅቱ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በስብሰባው ላይ ተገኝተው ነበር:: የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አክሊሉ ሃብተወልድና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ግን ጥቃቱን ሰምተው ዝም አላሉም:: ጣልያንን የሚያህል ሀገር በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ተከራክረው ያሸነፉት ስመ ጥሩው የህግ ሰው እና የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን አቋም በግልጽ አስገነዘቡ:: በመቀጠልም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴራችን በፍጹም ኢትዮጵያዊ እልህና ወኔ ይግባኛቸውን ለጉባኤው በማሰማት ድርጅቱ አዲስ አበባ ላይ እንዲቀጥል በሙሉ ሊባል በሚችል ድጋፍ አስወስነዋል::Aklilu Remembers

አፍሪካ አንድነት ድርጅት በንዲህ አይነት ትግል ነበር ኢትዮጵያ ላይ እንዲቀጥል የሆነው:: አክሊሉ ሃብተወልድ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት ህልም መሳካት ብርቱ ትግልም ያደረጉ ሰው ነበሩ:: ያለ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ተሳትፎም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታውም ሆነ እድገቱ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ነበር::

የሚደንቀኝ ግን እነዚህ ሃያላን በገዛ የሀገራቸው ልጆች ተካዱ:: ጥብቅና በቆሙላት የሃገራቸው ልጆች ታንቀውና በጥይት ተደብድበው በወታደራዊው መንግስት ተገደሉ:: አሁንም ያለው አገዛዝ የነሱ ታሪክ እና ለሃገር ያደረጉት አስተዋጾ እነዲነሳና እንዲታወስ አይፈልግም:: አፍሪካ አንድነት ድርጅት እንኳን ሃውልታቸው እንዳይሰራ በራሳችን መንግስት ተከልክሏል:: ለበጎ ስራቸው መታሰብያ እንዲሆኑ በስማቸው የተሰየሙ ነገሮች በሙሉ እንዲጠፉ ተደርገዋል:: ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወይም ለአክሊሉ ሃብተወልድ ሳይሆን ለቦብ ማርሌ ; ለሌኒን : ለማርክስ ሀውልት ሰራን!

ስጋቸው ቢሞትም : ታሪካቸው እንዳይነገር በርቱ ተጽኖዎች ቢደረግም : እውነት ግን ተደብቃ አትኖርም:: ጊዜዋን ጠብቃ ትወጣለች:: እኛም ዳዋ ለበሰውን ያባቶቻችንን ታሪክ እየፈለፈልን እናወጣለን:: የነሱ አምላክም ያግዘናል::

Filed in: eMedia, English News, News, Politics & Openion, Video & Audio

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.