0

ይህ ነው ኣማራ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ይህ ነው ኣማራ ( ሄኖክ የሺጥላ )Henok Yeshitela url

ይህ ነው ኣማራ
ከነጭ ገጥሞ ታሪክ የሰራ
የኣድዋን ጦር ከፊት የመራ
ባንዳን ከእስር ከንቁላል ሸክም
ያወጣ መሪ ፣ ያወጣ ጥበብ
ይህ ነው አማራ ፣ ያገሬ መርከብ !

አማራ ይኸው
ሞዜሩን ይዞ
ግንባሩን ቋጥሮ
ጥርሶቹን ነክሶ
ኩታ ደርቦ
ጥብቆ ለብሶ
በባዶ እግሩ ሀገር ሊያቀና
ደፋ ቀና ሲል አየሁትና

አምርሬ አዘንኩ ፣ ውስጤን ከፋኝ
የልጁ ለቅሶ ዛሬ ታይቶኝ !

እየው አማራን ፣ ገዳይ ያልከውን
በፊውዳልነት የመደብከውን !

አንተ ስትሸጥ ቅቤና እጣን
እኛ መቅደላ አፋፍ ላይ ወጣን !

እየው አማራን ፣ የጠላሃውን
በክፉ አፍህ ያነሳኸውን ።
ያንተ አባት ቁባት ፣ ገረድ ሲወሽም
አማራ አደረ ጣልያን ሲጎሽም ።
በጦሩ ወግቶ ፣ ሰቅስቆ ሲገል
ሲሞት ላገሩ ፣ እራሱን ሲጥል
ሀገር የሌለው ይሄ አማራ
ሀገር ሰጥቶሃል እንግዲህ ኩራ !

ፎክር ከምድሬ ካገሬ ውጣ
ብለህ ተናገር አንተ ቀንድ አውጣ
አንተ ያፈር ጠር ፣ ያገር ጋሬጣ
አማራ ይሙት ፣ አንተ ተቆጣ !

ወይ ጣጣ !

ያለ ክልልህ ገብተሃል ውጣ
በለው አማራን ፣ አንተ ቀንድ አውጣ ።

ግን ግን
ደሞ ጠላት ሲመጣ
አንተ ተደበቅ እሱ ይቆጣ
አንተ ተሸሸግ ፣ የሱ ነብስ ይውጣ
ሙቶ ያድንህ ፣ አንተ እንዳትመጣ

ይልቅ ቀን ሲወጣ
ጠላት በክንዱ ታሽቶ ሲቀጣ
ሃገሩን ለቆ ፣ ሸሽቶ እንደወጣ
ተመለስና ከመሸክበት
ቁባት ገረዱን ከወሸምክበት
የእንቁላል ዘንቢል ካነገትክበት
ጀግና ሁንና ፣ ትዛዙን ስጣ
ያለ ክልልህ ገብተሃል ውጣ
በለው አማራን ፣ አንተ ቀንድ አውጣ ።

ድንገት ባርነት ፣ ደግሞ ከመጣ
ድንገት መገዛት ደግሞ ከመጣ
አማራ ከንቱው ደጋግሞ ይሞታል ነጻ ሊያወጣህ
ሀገሬ ብሎ ፣ ባገር ሲቀጣ !

አማራ ንቃ
ቀና በል እንጂ
አካልህ አይሁን ፣ ማርከሻ ፈንጂ
ይልቅ ቀና በል ፣ እምቢ በል እንጂ
በቁጣህ መጠን ተናገር እንጂ
እምቢ በል ባክህ
ዞር በል በል በለው ፣ ዘር በል በል እንጂ
ይህንን ባንዳ ፣ የባንዳ ልጅ !

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.