0

“ዴምሕት” የሻእቢያ የትሮይ ፈረስ! ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ።

“ዴምሕት” የሻእቢያ የትሮይ ፈረስ!
ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ።
እንደምን ከረማችሁልኝ ክቡራትና ክቡራን አንባቢዎቼ። ይኽው በቀጠሮዬ ብቅ ብያለሁ
እንደገና።
“በሚቀጥለው ፅሁፌ በ“ድምሕት”ና በአወቃቀሩ ላይ እመጣበታለሁ ብዬ ነበር “ሻእቢያ
ለምን?” የሚለውን ቁጥር 1 ፅሁፌን የዘጋሁት።
የግሪክን አፈ-ታሪክ ታስታውሱ እንደሆነ ግሪኮች ትሮይን ወረሩ። ትሮይ የግሪኮችን ጥቃት
ገትራ ተቋቋመች። ምሽጓን መስበር አልተቻለም። ትሮይ የማትደፈር መሆኗን ለማስታወስ
በአቴና የጦርነት አምላክ ስም፤ግሪኮች ትልቅ የእንጨት ፈረስ ሰርተው ከትሮይ መግቢያ
በር ላይ ጥለውት በርቀት የሸሹ መስለው ተደበቁ ። ምንም እንኳ የትሮይ ዜጎች የሆኑት
ላኦኮንና ካሳንድራ፤ ፈረሱ የትሮይን በር አልፎ እንዳይገባ ቢከራከሩም፤ የትሮይ ሰዎች
የጦርነት አምላካቸው መታሰቢያ የሆነውን ይህን የግሪኮች የእንጨት ፈረስ ስጦታ
በራቸውን ከፍተው አስገቡት። ሌሊት ላይ በእንጨቱ ፈረስ ሆድ ውስጥ፤ ተደብቀው
የነበሩት ግሪኮች ወጥተው የትሮይን ቅጥር በር ከፈቱት። በርቀት ተደብቀው የነበሩት
ግሪኮችም በፍጥነት ተመልሰው በተከፈተላቸው በር ገብተው ትሮይን ደመሰሷት። ጠላትን
በውስጡ ተሸክሞ የነበረውን ፈረስ በፈቃዳቸው ወደ ከተማቸው ያስገቡት ማስተዋል
የተሳናቸው የትሮይ የራሷ ዜጎች ነበሩ።  tpdm_the_trojan_horse_of_shabia……read in pdf.

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.