0

የቤኒሻንል ጉምዝ መንግስት ያፈናቀለውን አማራ ገበሬ መልሶ አሰረው!

የቤኒሻንል ጉምዝ መንግስት ያፈናቀለውን አማራ ገበሬ መልሶ አሰረው!
June 12, 2015
አቶ አቻም ደምሴ በ2004 ዓ.ም ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከ5400 አማራ ገበሬዎች ጋር ተፈናቅሎ ነበር፡
http://quatero.net/amharic1/wp-content/uploads/2015/06/image455.jpg
በጊዜው ሙሉ ንብረቱ ወድሞበታል፡፡ አሁን ከ3ልጆቹ እና ባለቤቱ ጋር በባህር ዳር ከተማ አካባቢ ካለች መሸንቲ ከተማ በቀን ስራ
ይተዳደር ነበር፡፡የብዙ አማራ ገበሬዎች ፋይል በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት በአሁኑ ወቅት ለቅሶ ለመድረስ ቡለን ወረዳ በመሄዱ ከክልሉ
ያለ ፈቃድ ለምን ገባህ በሚል ሰበብ ትናንት ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ታስሯል፡፡
አቶ አቻም ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የአዝርእትና የእንስሳት ህብቱ ሙሉ በሙሉ ወድሞበታል፡፡
አማሮች ወደ ክልሉለመግባት የማይችሉት ምክንያት እስካሁን የተደነገገ ህግ ባይኖርም በተደጋጋሚ ለምን መጣችሁ በሚል ሰበብ ይታሰራሉ፡፡ አቶ አቻም
በአሁኑ ሰዓት በቡለን ወረዳ ፓሊስ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ከታች የምትመለከቱት ፎቶ በተፈናቀሉ ወቅት ተዘርፎ የተዘጋ ቤት ነው፡፡
(ይህ ገበሬ መታሰሩን የሰማሁት ትናንት ምሽት ከአካባቢው ተደውሎ ነው፡፡ ሚዲያው የሚጮኸው ለታወቁ ሰዎች ነው፡፡እኛ ደግሞ ለወላጆቻችን እንዲህ እናላዝን እስኪ!)
Source: http://quatero.net/am
Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.