0

ስለ አማራ ሳወራ ( ሄኖክ የሺጥላ )

ስለ አማራ ሳወራ ( ሄኖክ የሺጥላ )

በይሉኝታ ተተብትበው ፣ በዝምታ ተለጉመው ፣ ቅድሚያውን ለኢትዮጵያዊነት በመስጠት፣ እንደ ሌሎች ማነስ አቅቷቸው እየጠፉ ያሉት የአማራ ልጆች ናቸው ። የአማራ ልጆች ፣ የአማራ ልጅነታቸው ሁሌም ሁለተኛ ወይም መጨረሻኛ ሃሳብ ነው ። ይህ ግሩም ስብእና ነው ። ይህ የሁሉም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ጎሳ ሃሳብ ና መረዳት ቢሆን የት በደረስን ። አማራ ዘር አይደለም ከሚሉት እስከ አማራ ጨቋኝ ነው እስካሉት ፣ ሀገር ወዳድ እና የሀገር መንፈስ አልባ ፖለቲከኞች ድረስ ፣ ለምን አማራን ማሳነስ ፣ ወይም ማሰይጠን ፈለጉ ብዬ ራሴን ስጠይቅ ፣ መልሱ እንደሚከተለው ሊቀርብ ይችላል ።

፩) አማራ በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምን ስለሆነ ፣ ሃሳቡ ወደ ብዙሃን ኢትዮጵያውያኖች ከተዛመተ የአንድነት ጥያቄ ስለሚያስነሳ ። የአንድነት ጥያቄ ከተነሳ ፣ አናሳ ዘረኞች የመኖር ሕልውናቸው አደጋ ላይ ስለሚወድቅ

፪) አብዛኛው የአማራ ልጅ የተማራ ብቻ ሳይሆን ፖለቲካዊ ንቃተ ሕሊናውም በተወሰነ ደረጃ ከሌሎች (ሌሎች ማለት አማራ ካልሆነው ማለት ነው ) የተሻለ ስለሆነ ። እባካችሁ አማራ የተሻለ ስለሆነ ማለት አይደለም ። ( ምሳሌ የከምባታ ፣ የሃድያ እና ወዘተ ኢትዮጵያውያኖች ፣ ብዙ የተማሩ ሰዎች አሏቸው ፣ ግን ብዙዎቹ ፖለቲካው ላይ የማይሳተፉት ለምንድን ነው ?) እምነት ( የአምልኮ ስርዓታቸው ) እንደ ምክንያት ሊቀርብ ይችላል ፣ በአብዛኛው ወንጌላውያን ናቸው ፣ ግን ወንጌሉ የሄደላቸው እኛ ከምንኖርበት አማሪካ ነው ። ስለዚህ ችግሩ የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ማነስ ( አለመጎልበት ) ይሆን ይሆናል ። ይህንን ጉዳይ አቶ አሰፋ ጨቦ ፣ ወይም ዶ/ር በየነ ጴጥሮስ ወይም አቶ ዔፍሬም ማዴቦ ሊያብራሩልን ይችላሉ ። “የነቁ ስለሆኑ !”

፫) አማራ በአማራነት ስብእና ውስጥ ብቻ እንዲገባ በማድረግ ፣ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ ፈጽሞ እንዲጠፋ ለማድረግ ላንግላታ ያሉት አለቆቻችን ጨክነው ስለሚሰሩ ። ለዚህም ምክንያቱ እነ () ጣልያን ያሸነፈው አማራ ነው ብለው ስለሚያስቡ ።

፬) አማራን መጥላት ከዘንድሮ ፖለቲካዊ ጥቅም አንጻር ስለሚያዋጣ ። ለምሳሌ ዛሬ የኤርትራ መንግስት ( ሻቢያ ) ለአማራ ያለውን ጥላቻ ፣ የአንዲት ሉዓላዊት ሀገር የፖለቲካ መብት አስመስሎ በማቅረብ ፣ የወረደ ዲስኩር የሚደሰኩሩት እራሳቸው የአማራ ልጆች መሆናቸው ። እና አለማፈራቸው ብቻ ሳይሆን ሊያስፈራሩ ማሰባቸው ። አይገርምም ?

ለዚህም ነው ትናንት አማራን በአደባባይ ሲጠሉ ወይም እንደሚጠሉ በአግድም ሲናገሩ የሰማናቸው ሰዎች ዛሬ አምቦ ላይ ሕዝብ አውጥተው ስለተናገሩ በየ ዜና ማሰራጫዎቹ ስለነሱ የምንለፍፈው ። ለዚህ እንደ ትልቅ ምሳሌ የምወስደው ዶ/ር መራራ ጉዲናን ነው ። መራራ ድሮ ሳይሆን በቅርቡ ( ምናልባት የዛሬ 5 ወይም ስድስት ወር ገደማ በኢሳት ላይ ቀርቦ ቃለ መጠይቅ ሲሰጡ ) ስለ ቅንጅት ሲናገሩ ፣ “ቅንጅት የአማራ ነው” ነበር ያሉት ። ይህ የፈሪ ሰው አስፈሪ አስተሳሰብ ፣ ነገ ከነ ወረደ እና ዘቀጠ አመለካከቱ ስልጣን ላይ ቢወጣ ” የጠገበ ዝንብ አባሮ የተራበ ዝንብ መጥራት ” እንደሆነ ያልተረዳን ፣ የ ዶ/ር መራራን ትግል ወያኔን ከማውረድ ጋ ብቻ አያይዘን ፣ ስናሽቃብጥ ሰንብተናል ። ለምን ? አማራ ለኛም ጠላት ስለሆነ ። ለምን? ያንን ንግግር የተናገረው አማራ ስላልሆነ ። ለምን ? አማራ ስለሚያስፈራን ። ለምን ? እንደ አማራ ማሳብ የልቻሉ ፣ ማሰብ የጀመሩ ለት የኛን ኩርማን እና ደቃቃ ቦጠሊቃ ጠራርገው ስለሚወስዱት ። ለምን ?አማራን መጋፈጥ የሚችል አቅማችን ፣ ባለፈ እና ጉራማይሌ በሆነ የበደል ታሪክ ላይ የተመሰረተ ስለሆነ ። ለምን ? ስለ ጥላቻችን መልስም ጥሩ መንፈስም ስለሌለንለን። ለምን ? ሰው ስላልሆንን !!!

አማራ ጨቋኝ ህዝብና ስርዓት ነው የምትሉ ፣ እስኪ ወደ ሸዋ ፣ ጎንደር ፣ ጎጃም ፣ ወሎ ውረዱና እናንተ በምትሉት የአማራ ስርዓት ዘመኖች ለአማራ ብቻ የተገነቡትን ሆስፒታሎች ፣ የትምህርት ቤቶች ፣ መድሃኒት ፋብሪካዎች ፣ እና ሌሎች ነገሮች አንድ ሁለት ብላችሁ ቁጠሩልኝ ።

አማራ ግፈኛ ስርዓት ነው የምትሉ፣ በደርግ ጊዜ ( እንደ እናንተ ደርግ የአማራ ስርዓት ነውና ) በቀይ ሽብር በግፉ የተገደሉት አብዛኛዎቹ የአማራ ልጆች አይደሉምን ? በቀዳማዊ ሃይለስላሴ ወኔ በደርግ ጊዜ ቁልፍ የሆኑ የፖለቲካ ተሳትፎዎች ላይ ጉልህ ሚና የነበራቸው ፣ የሌላ ብሔር ሰዎች አልነበሩምን ? አረ ለመሆኑ የዳግማዊ ሚኒሊክ የጦር አዛዦች ፣ ፊት አውራሪዎች ፣ ቀኝ አዝማቾችች አማራዎች ብቻ ነበሩ ? ( ይህንን ከ መቶ አስራ ሶት ዓመት በሗላ ፍትህ እና ርትዕ አመጣሁ ከሚለው የወያኔ ስርዓት ጋ አወዳድሩልኝ እና ንገሩኝ )።

አማራ ያስፈራናል ፣ ስለዚህ እንጠላዋለን ። የምንፈራው ደሞ በግፉ ወይም ባደረሰብን በደል ሳይሆን ፣ በኢትዮጵያዊ ስሜቱ ነው ። እነ ኮነሬል ታደሰ ሙሉነህ ፣ የኔ ወዳጅ እና ጏደኛ ፣ እነ የአማራ ንቅናቄ እና ወዘተ በዔርትራ ምድር የውሃ ሽታ የሆኑት ለምን እንደሆነ እናውቅ ይሆን ? የሚያውቁ ካላሳወቁ ፣ ማስወቃችንን እንቀጥላለን ። ትግሉ በዚህ ሃሳብ የሚዳከም ከሆነ ይዳከም !!!!! ዋናው ቁም ነገር ግን አማራ ጠላት ነው ያለ የሀገር መሪ አለ ፣ አማራ ጠላት ነው ብሎ ግን በአማራ ልጆች ደም ጦር የመሰረተ ተቃዋሚ ድርጅትም አለ ። ይሄን እንደ ሰው ማስቆም ያለብን ይመስለኛል።

ኢትዮጵያን የምንወድ ግን አማራን የምንጠላ ፣ የትግል መንገዳችን ምን ያማራ ፣ እና የሰመረ ቢመስልም ፣ እንኳን አማራን ያህል ትልቅ ታሪክና ባህል ያለው ዘር ፣ እንኳን የኢትዮጵያን ማንነት ያቆሙ ዋልታዎች የተፈጠሩባት ማህጸን የወለደች ዕናት ይቅርና ፣ እኛም በዘር ትብታብ ፣ በጠባብነት ልሳን ስንናገር የነበርን እና ያለን ደቃቃ ድኩማኖችም ከሌለንበት ፣ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር የለችም ( አትኖርም !)። “የማን በት ፈርሶ ለማን ሊበጅ የአውሬ መውለጃ ይሆናል እንጂ ” የሚለውን ነገር የአማራ ሕዝብ በፍጹም የማያስበው ጉዳይ ስለሆነ እንደሆነ እስከዛሬም የኖራችሁት ምን ያ ህል ታውቁ ይሆን ?

Source: Henok Yeshitla fb

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.