0

የምን ምርጫ ምርጫ ነው? ከቦጋለ ካሳዬ

የምን ምርጫ ምርጫ ነው?

የአንድነትና የመኢአድ ከምርጫው መገለል ውጤቱን ሳይታለም የተፈታ ካደረገው ውሎ አድሮ የለም እንዴ?
ሰማያዊ መድረክና እና ሌሎች አሁንም ተፍ ተፉን ተያይዘውታል። ምናልባት ወያኔ ከ99.6% ዝቅ ብሎ ትንሽ እንጥፍጣፊ ወንበሮች ያካፍላቸው ይሆናል። ሁሉም ተቃዋሚዎች 1 መቶ ይሁን 2 መቶ መጎለቻ ወንበሮች ቢያገኙ እንኩዋን በኢትዮጵያ ፖለቲካ የፖሊሲ ለውጥ ለማምጣት አይችሉም።

… ይልቁንም ሊያሳስበን የሚገባው ድህረ ምርጫ ነው። በመጀመሪያ ይኸም ምርጫ ሆኖ ደም እንዳይፈስ ነው።
በሁለተኛ ደረጃ ይኼ አይነት ያለቀለት የቀልድ ምርጫ መራጭ አያስፈልገውም። እኔ መራጭ ብሆን ኖሮ አልመርጥም። ምክንያቴም የወሮበሎች አገዛዝ በሚረግጠው አገር ውስጥ ድምጽ መስጠት ዞሮ ዞሮ የሚያጠናክረው ወረበላውን ብቻ መሆኑ ደግሞ ተደጋግሞ ስለታየ ነው። አማራጭ የለሹ ጉዳይ… የወያኔ ምርጫ ወይም ልግጫ እንዴት ነው የሚያከትመው በሚለው ላይ ጠንክሮ መስራት ነው።
– የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የሳንቲም ስብሰባ ዘመቻ አድናቂ ነኝ። ሌላስ ተመሳሳይ የሰላማዊ ትግል አሁን ባለው ተጨባጭ የአገሪቱ ሁኔታ ማካሄድ አይቻልም ወይ? የምታውቁት እናንተው ናችሁ ።
– ጫትን ማመንዥክ እንደ ትልቅ ነውር ቆጥሮ …. ለነጻነት መታገልን እንደ ትልቅ ክብር አድርጎ መቁጠር የነጻነትን ቀን አያቀርብም ወይ?
– ወጣቶች ተምራችሁ ስራ የማታገኙበት ዋናው ምክንያት ምንድን ነው? የወያኔ አድሎአዊና ድንብርብር የፖለቲካ ፖሊስ አይደለም እንዴ? ስለዚህ የአገራችን ሀብት ክፍፍል ፍታዊ እንዲሆን እጅን አጣጥፎ አ እምሮን ቆልፎ መጎለትና ለአሰቃቂ ስደት መዳረግ አይበቁም ወይ?
አንድ አደጋ አለ ከፊታች የተደቀነ። የሻእቢያና የወያኔ ፖለቲካ ጫወታ። የሰሜን ኢሊቶች አገራችንን በጥርሳቸው ነክሰው ይዘዋል። ጥርሳቸው ነክሶናል። አድምቶናል። ገድሎናል። ለስደት ዳርጎናል። መፍትሄው መሃል አገሩ ሰብሰብና ምርር ብሎ ጥርሳቸውን ለደንቡም ቢሆን እንዲስቅ ማድረግ ነው። ለኢትዮጵያ የሚበጃት መፍትሄ ከዳርቻ ሳይሆን ከመሃል አገሩ የሚመጣ ነው… ነጻነትህን አንጋጠህ ከአስመራ መጠበቁን ማርያምን ተወኝ።
ክርስቲያንም እስላምና አላማኝም ተስፍ አይቆርጡም። አይዞን!

Source: Bogale Kassaye fb

Filed in: Amharic News, eMedia, News, Politics & Openion

Recent Posts

Leave a Reply

You must be Logged in to post comment.

© 2019 Moresh Information Center. All rights reserved.